ሰላም ፌስቲቫል
ዝግጅት፡- በሰላም ፌስቲቫል የትዝታው ንጉሥ መሐሙድ አህመድን ጨምሮ በርካታ የአገር ውስጥና የውጭ አርቲስቶች ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡ ፀሐይ ዮሐንስ፣ ሞኒካ ማንክር፣ ዲጄ እንደገና ሙሉ፣ አዝማሪ ሲንተሲስና ዳዊት ጽጌ እንዲሁም ዝነኛው አሜሪካዊ ራፐር ያሲን ቤ፣ ጌል ፋይ፣ ማርከስ ፕራይስና ሌሎችም ይገኙበታል
ቀን፡- ታኅሣሥ 30 እና ጥር 1 ቀን 2008 ዓ.ም.
ቦታ፡- ግዮን ሆቴል
አዘጋጅ፡- ሰላም ኢትዮጵያ
መጻሕፍቱ
በሔርሜላ ሰለሞን የተጻፈው ‹‹የፍሬሿ ማስታወሻ›› ባለፈው ሳምንት ተመርቋል፡፡ በጸሐፊቷ የአራት ዓመት የዩኒቨርሲቲ ቆይታ ላይ ያተኮረው መጽሐፍ በ47፡50 ለገበያ ቀርቧል፡፡ በተያያዥም በዶ/ር ሞገስ አየሁ የተጻፈውና የሥነ አእምሮና ሥነ ልቦና ጉዳዮችን የሚዳስሰው መጽሐፍ ‹‹ድፍርስ›› በ85 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ በአክሊሉ ረታ የተጻፈው ‹‹የሕይወት መንገድ›› የደራሲውን የሕይወት ተሞክሮ የሚያሳይ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ተመርቆ ለገበያ በቅቷል፡፡
‹‹የጥበብ አንድነት››
‹‹የጥበብ አንድነት›› በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በተካሄደው የፋሽን ትርዒት በአራት ወጣት ዲዛይነሮች የተዘጋጁ ባህላዊና ዘመናዊ አልባሳት ቀርበዋል፡፡ ታኅሣሥ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ በካሌብ ሆቴል በተካሄደው ዝግጅት ላይ ኮሜዲያን ልጅ ያሬድ ሥራዎቹን አቅርቧል፡፡ በባላገሩ አይድል ውዝዋዜ አሸናፊ የሆኑት የባህል ቡድን ኢትዮጵያዊነት ውዝዋዜ አቅርበዋል፡፡