Sunday, August 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  መንግሥት በቅርቡ ላቋቋማቸው ኮርፖሬሽኖች ዋና ሥራ አስኪያጆችን ሾመ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  መንግሥት በቅርቡ ላቋቋማቸው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን አቶ ኃይለ መስቀል ተፈራን፣ ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ኮርፖሬሽን ዶ/ር ነገደ አባተን ዋና ሥራ አስኪያጆች አድርጎ ሾመ፡፡

  አቶ ኃይለ መስቀል ቀደም ሲል የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ዴኤታ ነበሩ፡፡ አሁን ደግሞ መንግሥት በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላቋቋመው ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተሹመዋል፡፡ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ መንገድ ሥራዎች ኮርፖሬሽንና የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝን በሥሩ ያቀፈ ነው፡፡

  ዶ/ር ነገደ ደግሞ ቀደም ሲል የውኃ ሥራዎች ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ነበሩ፡፡ ዶ/ር ነገደ ይመሩት የነበረው ይህ ኢንተርፕራይዝ፣ የትራንስፖርት ኮንስትራክሽን ዲዛይን ኢንተርፕራይዝና የሕንፃ ዲዛይን ኢንተርፕራይዝ ተዋህደው የኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ኮርፖሬሽን ተቋቁሟል፡፡ ዶ/ር ነገደ የዚህ ግዙፍ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው መሾማቸው ታውቋል፡፡ በሁለቱም ኮርፖሬሽኖች ሥር ሆነው እንዲተዳደሩ የተደረጉትና ቀደም ብለው ራሳቸውን ሲያስተዳድሩ የቆዩትን ተቋማት ሲመሩ የነበሩ ዋና ሥራ አስኪያጆች፣ የየኮርፖሬሽኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው እንዲሾሙ መወሰኑም ታውቋል፡፡

  በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ኮርፖሬሽኖች በበላይነት የሚመሩ ሥራ አመራር ቦርድ አባላት በመሾም ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ለኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ኮርፖሬሽን ሥራ አመራር ቦርድ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ አቶ ዓብይ አህመድና የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዓለማየሁ ጎጆን ጨምሮ ስድስት ባለሥልጣናት የቦርድ አባላት ሆነው ተሹመዋል፡፡ አቶ ዓብይ ቦርዱን እንደሚሰበስቡ ታውቋል፡፡

  የኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ሥራ አመራር ቦርድ አባላት እስካሁን አልታወቁም፡፡ ቀደም ባሉት ዓመታት ከፍተኛ በጀትና ውስብስብ በሆኑ ግንባታዎች የአገር ውስጥ ኩባንያዎች ብዙም ተሳታፊ እንዳልነበሩ ይታወቃል፡፡

  መንግሥት ይህንን አሠራር ለማስቀረት የአገር ውስጥ የግንባታ አቅም መፍጠር ያስፈልጋል በሚል ምክንያት፣ በቀጣዮቹ ዓመታት ለውጥ ያመጣል ያለውን አዲስ መዋቅር ዘርግቷል፡፡

  እነዚህ ሁለት አዳዲስ ኮርፖሬሽኖች በጨረታ፣ በድርድርና በትዕዛዝ ትልልቅ የመስኖና የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድቦችን ጨምሮ የተለያዩ ግንባታዎችን ያካሂዳሉ ተብሏል፡፡ 

  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -spot_img

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች