Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ሥነ ፍጥረትየባሕር አቆስጣ

  የባሕር አቆስጣ

  ቀን:

  በመዝገበ እንስሳት እንደተጻፈው፣ አጥቢ  እንስሳት የሚባሉት የጀርባ አጥንት ያላቸው ናቸው፡፡  ከነዚህም መካከል በባሕር ውስጥ የሚኖረው አቆስጣ ይጠቀሳል፡፡ አቆስጣን ጨምሮ በቀዝቃዛ ውኃ ውስጥ የሚኖሩ በርካታ አጥቢ እንስሳት ከቆዳቸው ሥር ብርድ ለመከላከል የሚረዳ ወፍራም ስብ አላቸው። እንደ የመጠበቂያ ግንብ ድረ ገጽ ዘገባ፣ የባሕር አቆስጣ ግን ለየት ያለ የብርድ መከላከያ አለው ያሰኘው  ሰውነቱ  ጥቅጥቅ ባለ ፀጉር መሸፈኑ ነው።

  የባሕር አቆስጣ ፀጉር ከሌሎች አጥቢ እንስሳት ይበልጥ ጥቅጥቅ ብሎ የበቀለ ነው፤ ይህ እንስሳ በአንድ ካሬ ሴንቲ ሜትር ውስጥ 155 ሺሕ ፀጉሮች አሉት። አቆስጣው በሚዋኝበት ወቅት ሰውነቱን የሸፈኑት ፀጉሮች አየር አፍነው ያስቀራሉ። በፀጉሮቹ ውስጥ የታፈነው አየር ደግሞ ቀዝቃዛው ውኃ የእንስሳውን ቆዳ በቀጥታ እንዳይነካውና የሰውነቱን ሙቀት እንዳያሳጣው ይከላከልለታል።

  ሳይንቲስቶች የባሕር አቆስጣን ፀጉር በመመልከት ብዙ ነገሮችን መማር እንደሚቻል ያምናሉ። እነዚህ ሳይንቲስቶች ብርድ በሚከላከሉ ፀጉራማ ኮቶች ላይ ያሉትን ፀጉሮች ቁመትና በመካከላቸው ያለውን ክፍተት በመቀያየር የተለያዩ ሰው ሠራሽ ኮቶችን ለመሥራት ሞክረዋል። ተመራማሪዎቹ ባደረጉት ጥናት የሚከተለው መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል፦የፀጉሮቹ ቁመት በጨመረና ፀጉሮቹ ይበልጥ ጥቅጥቅ ባሉ ቁጥር በፀጉር የተሸፈነው ክፍል ያለው ውኃ የመከላከል አቅምም እየጨመረ ይሄዳል።በእርግጥም የባሕር አቆስጣዎች ብርድን በሚገባ የሚከላከል ምርጥ ፀጉራማ ኮት አላቸው ሊባል ይችላል።

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...