Monday, August 8, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  ​የፋይናንስ ተቋማትን ውህደት በተመለከተ የንግድ ውድድር ባለሥልጣንና ብሔራዊ ባንክ እየተነጋገሩ ነው

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  የፋይናንስ ተቋማትን ውህደት በተመለከተ የኢትዮጵያ የንግድ ውድድርና የሸማቾች ባለሥልጣን የፋይናንስ ተቋማት ተቆጣጣሪ ከሆነው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋር መነጋገር መጀመሩን ባለሥልጣኑ ገለጸ፡፡

  የባለሥልጣኑ የውህደት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ነብዩ በለጠ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በቅርቡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ የመዋሀድ ፍላጎት ይፋ ከሆነ በኋላ ባለሥልጣኑ ኃላፊነቱን ለመወጣት፣ ጉዳዩ ከሚመለከተው ሌላው ባለድርሻ አካል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋር በመነጋገር ላይ ነው፡፡

  የንግድ ተቋማት ውህደትን በተመለከተ ሥልጣን የተሰጠው ለንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለሥልጣን መሆኑን የጠቀሱት አቶ ነብዩ፣ በተሰጠው ኃላፊነት መሠረትም የውህደት ዓይነቶችን በሦስት ከፍሎ እየተመለከተ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

  እነዚህም ቀላል፣ መካከለኛና ከፍተኛ ውህደት ተብለው የሚጠቀሱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

  ቀላል ውህደት የሚመለከተው የውህደቱ መጠን በአጠቃላይ ከ30 ሚሊዮን ብር በታች ያለውን ሲሆን፣ ከ30 ሚሊዮን ብር እስከ 300 ሚሊዮን ብር መካከለኛ ውህደት ምድብ ውስጥ እንደሚወድቅ፣ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ያለው ደግሞ ከፍተኛ ውህደት እንደሚባል ገልጸዋል፡፡

  ከ30 ሚሊዮን ብር በታች ያሉ ውህደቶችን የሚያከናውኑ ተቋማት ለባለሥልጣኑ ሳያሳውቁ ውህደቱን ቢፈጸሙ ችግር የሌለው መሆኑን የሚጠቅሱት አቶ ነብዩ፣ ባለሥልጣኑ ግን በማንኛውም ጊዜ በዚህ ውህደት ላይ ትንተና መሥራት እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

  መካከለኛና ከፍተኛ የንግድ ውህደቶች ከመፈጸማቸው በፊት ግን ውህደቱን መፈጸም የሚፈልጉ ተቋማት ለባለሥልጣኑ ማሳወቅ እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡ ባለሥልጣኑ ውህደቱን ሳይቀበል ውህደቱን የማፅደቅና ፈቃድ የመስጠት ሕጋዊ ሥልጣን ማንኛውም የመንግሥት አካል እንደሌለው ጠቅሰዋል፡፡ ባለሥልጣኑ የውህደት ጥያቄውን ከንግድ ውድድር አንፃር፣ ማለትም ውህደቱ ሌሎች ኩባንያዎች እንዳይወዳደሩ ተፅዕኖ የሚፈጥር አለመሆኑን ወይም ሞኖፖሊን የሚያስፋፋ አለመሆኑን፣ እንዲሁም ከሕዝብ ጥቅም አንፃር ገምግሞ ውሳኔ የሚያሳልፍ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ለመፈጸም የፈለጉት ውህደት ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታልን የሚፈጥር በመሆኑ፣ ውህደቱ በንግድ ውድድርና የሻጮች ጥበቃ ባለሥልጣን መታየት ይኖርበታል፡፡

  በአሁኑ ወቅት የሁለቱ ባንኮች ውህደት ለሚዲያ ተገለጸ እንጂ ተግባራዊ አልሆነም የሚሉት አቶ ነብዩ፣ ጉዳዩን በተመለከተም ከብሔራዊ ባንክ ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የፋይናንስ ዘርፉን የመቆጣጠር ኃላፊነት የባንኩ በመሆኑ በጋራ ለመሥራት ንግግር ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ይሁንና የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ስንታየሁ ወልደ ሚካኤል በቅርቡ ውህደቱ በመንግሥት መወሰኑን መናገራቸው አይዘነጋም፡፡

  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች ፈቃድ የመስጠት እንዲሁም የመቆጣጠር ኃላፊነት ቢኖረውም፣ ውህደትን በተመለከተ ግን ምንም ዓይነት መቆጣጠሪያ የሕግ ማዕቀፍ የሌለው በመሆኑ፣ በውጭ ኩባንያ ‹ጋይድ ላይን› (መመርያ) ለማውጣት እያስጠና መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

    

  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -spot_img

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች