Sunday, August 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  የኢትስዊች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ ሁሉንም የአገሪቱን ባንኮች ባለአክሲዮን በማድረግ የተቋቋመው ኢትስዊች አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብዙነህ በቀለ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ፡፡

  የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ አቶ ብዙነህ ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ የሥራ መልቀቂያ ጥያቄያቸውን ለኩባንያው ቦርድ ካቀረቡ በኋላ ቦርዱ ጥያቄያቸውን ተቀብሎታል፡፡

  በእሳቸውና በቦርዱ እንዲሁም ከአንዳንድ ባንኮች ጋር ተግባብተው ለመሥራት አለመቻላቸው ከኃላፊነታቸው እንዲለቁ ምክንያት መሆኑን ምንጮች የሚጠቅሱ ሲሆን፣ በደብዳቤያቸው  ላይ ግን ለሥራ መልቀቃቸው እንደ ምክንያትነት ያቀረቡት ነገር መኖር አለመኖሩ አልታወቀም፡፡

  ሆኖም ቦርዱ ለጥያቄያቸው ወዲያው አዎንታዊ ምላሽ መስጠቱና እንዲሰናበቱ መወሰኑ፣ በመካከላቸው አለ የሚባለውን ችግር አሳይቷል የሚል አስተያየት ይደመጣል፡፡

  ኢትስዊች ዘመናዊ የባንክና የክፍያ አገልግሎቶችን ለማስፋፋት ታስቦ የተቋቋመው ሲሆን፣ ኩባንያው በተለይ የሁሉንም ባንኮች ኤቲኤሞች በማስተሳሰር የባንክ ደንበኞች በየትኛውም ባንክ ኤቲኤሞች እንዲገለገሉ የሚያስችለውን አሠራር በመተግበርና በማዕከል መምራት ከሥራዎቹ መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -spot_img

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች