Sunday, August 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊ​የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል በተመረጡ ዘርፎች ላይ ምርምር እያካሄደ ነው

  ​የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል በተመረጡ ዘርፎች ላይ ምርምር እያካሄደ ነው

  ቀን:

  ከተመሠረተ ሁለት ዓመት የሞላው የኢፌዴሪ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል፣ በዋና ዋና የተመረጡ የመንግሥት ዘርፎች ላይ ምርምር እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ፡፡

  ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር የሆነውና በአቶ ዓባይ ፀሐዬ የሚመራው ይኼው የምርምር ተቋም፣ በርካታ የኢሕአዴግ ነባር አመራሮች ይሠሩበታል፡፡ በመንግሥት የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር በማድረግ ክፍተቶችን ለማየት፣ አማራጭ ሐሳቦችና መፍትሔዎችን ለመጠቆም የተቋቋመ ነው፡፡

  በቅርቡ በአራቱ ዋና ዋና ትልልቅ ክልሎች (ማለትም በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በደቡብና በአማራ) በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ባካሄደው ጥናት ላይ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣኖች እንዲወያዩበት ያደረገ ሲሆን፣ ይኼም በኢቢሲ ተላልፎ የተለያዩ አስተያየቶችን ከበርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎች መጋበዙ ይታወሳል፡፡

  ሕዝቡ በእጅጉ የተማረረበት የመልካም አስተዳደር ዕጦት ግንባር ቀደም ምርጫ በማድረግ ምርምሩን የጀመረው የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ተቋም በአሁኑ ወቅት በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በከተማ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች በራሱና ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ምርምር እያደረገ መሆኑን፣ የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓባይ ፀሐዬ ተናግረዋል፡፡

  አቶ ዓባይ ዓርብ የካቲት 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በማዕከሉ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት፣ በአገር ውስጥ ከሚገኙት ተመሳሳይ ተቋማትና ከውጭ አገሮች (ደቡብ ኮሪያ፣ ቻይናና ጀርመን ጨምሮ) ትብብር በመፍጠር ተቋሙ ምርምሩን እያካሄደ ይገኛል፡፡

  አቶ ዓባይ ማዕከሉ የሰው ኃይል እጥረት እንዳጋጠመው ገልጸው፣ ክፍተቱን ለመሙላት ከዩኒቨርሲቲዎችና ከተለያዩ የምርምር ተቋማት ጋር አብሮ ለመሥራት ማቀዱን አስረድተዋል፡፡

  ከተመሠረተ ሁለት ዓመታት የሞሉት የፖሊሱ ጥናትና ምርምር ማዕከል፣ እያከናወናቸው ያሉ ጥናቶች በአገሪቱ በየዘርፉ ያሉ የፖሊሲ አፈጻጸም ችግሮችን ለመፍታት እንደሚያስችሉ አቶ ዓባይ አስታውቀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አዳዲስ ፖሊሲዎችን ለመቅረፅና በየዘርፉ መሻሻል ያለባቸውን ፖሊሲዎች ለመንግሥት ሐሳብ ለማቅረብ እንደሚረዳም አክለዋል፡፡ በተጨማሪም ቀደም ሲል በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ የተሠራው ጥናት ውጤታማ መሆኑን፣ መንግሥትም ችግሮቹን ለመፍታት እየሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

  በአሁኑ ወቅት ማዕከሉ ስድስት መሪ ተመራማሪዎች፣ ሰባት ከፍተኛ ተመራማሪዎች፣ አሥር ጀማሪ ተመራማሪዎችና 32 ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በድምሩ፣ 55 ሠራተኞች ቀጥሮ በማሠራት ላይ ይገኛል፡፡ 

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በዓለም ጂኦ ፖለቲካ መድረክ የኢትዮጵያ ተፈላጊነት

  የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሦስት የአፍሪካ አገሮች...

  በአገር ጉዳይ አንዱ ባለቤት ሌላው ባይተዋር መሆኑ ይብቃ!

  ኢትዮጵያ የታፈረችና የተከበረች አፍሪካዊት አገር ናት፡፡ ለመላው የዓለም ጥቁር...

  ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2015 የሒሳብ ዓመት ተቀማጭ ገንዘቡን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ለማሳደግ እንደሚሠራ አስታወቀ

  በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በተለያዩ ክንውኖቹ ከዕቅድ በላይ ውጤት ማስመዝገቡን...