Monday, August 8, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀደ የሥራ ዘርፍ ላይ በድብቅ ተሰማርቶ የተገኘ የቻይና ድርጅት ታገደ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  ‹‹ኮሚሽኑን ጠይቀን ውሳኔ እየተጠባበቅን ነው››

  ሀኦነንግ ፓኬጂንግ

  ‹‹ፈቃድ ከሌለው ድርጅት ጋር ውል የፈጸሙ ድርጅቶች በሕግ ይጠየቃሉ››

  የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

  የፀና ፈቃድ ሳይኖረውና ለሌላ ሥራ የተሰጠውን ፈቃድ በመጠቀም፣ ኢትዮጵያውያን ብቻ እንዲሰማሩበት በተፈቀደ የሥራ ዘርፍ ላይ ተሰማርቶ የተገኘ የቻይና ኩባንያ ታገደ፡፡

  ሀኦነንግ ፓኬጂንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተባለው ድርጅት ለፓኬጂንግ፣ ለወረቀት፣ ለሶፍትና ለናፕኪን ሥራዎች በወሰደው ንግድ ፈቃድ፣ ያልተፈቀደለትንና ለኢትዮጵያውያን ብቻ የተፈቀደውን፣ የተለያዩ የንግድ ስያሜዎች የያዘ ሌብል (ስቲከር) ማምረት ሥራ ውስጥ ገብቶ በመገኘቱ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እንዳስቆመው ሪፖርተር ለማወቅ ችሏል፡፡

  ድርጅቱ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ቀበሌ አንድ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ ከተፈቀደለት ሥራ ውጪ ተሠማርቶ በመገኘቱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት የሌብል ማምረት ሥራው መታገዱን ለሪፖርተር የገለጹት፣ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ተካ ገብረየሱስ ናቸው፡፡ አቶ ተካ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ለድርጅቱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፡፡ በተሰጠው ፈቃድ መሠረት የፓኬጂንግ፣ የወረቀት፣ የሶፍት፣ የናፕኪንና የሌብል ወረቀት ማምረት አለበት፡፡ ከዚህ ውጪ ሲሠራ ከተገኘ የተሰጠው ፈቃድ ተሰርዞ ድርጅቱን እንዲዘጋ ይደረጋል፡፡ የድርጅቱ ባለቤትና ኃላፊዎች ወደ ኮሚሽኑ መጥተው ከዋና ኮሚሽነሩ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸውም አቶ ተካ አስረድተዋል፡፡

  ባልተፈቀደላቸውና የፀና ንግድ ፈቃድ በሌላቸው ዘርፍ ውስጥ ተሰማርተው ቢያመርቱም መሸጥ እንደማይችሉ የገለጹት ምክትል ኮሚሽነሩ፣ ውል ፈጽመው ያሳተሙ ድርጅቶች ከተገኙም በሕግ እንደሚጠየቁ ተናግረዋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ሥራው ኮንትሮባንድ በመሆኑና ቫትም ስለማይከፈልበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

  ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ከሌለው ድርጅት ጋር ውል ፈጽሞና ሌብል እንዲመረትለት አዝዞ የተገኘ ድርጅት ተጠያቂ እንደሚሆንም አቶ ተካ አክለዋል፡፡ ኮሚሽኑ በደረሰው ጥቆማ መሠረት ባለሙያዎቹን ወደ ድርጅቱ ልኮ ድርጊቱ መፈጸሙን ማረጋገጣቸውን የተናገሩት አቶ ተካ፣ አሁንም በድጋሚ ሌላ ቡድን ለመላክ እየተዘጋጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በሕገወጥ መንገድ ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀደ የሥራ ዘርፍ ተሠማርተው በተገኙ በርካታ ድርጅቶች ላይ ኮሚሽኑ ዕርምጃ መውሰዱንና እየተወሰደም መሆኑን አቶ ተካ አክለዋል፡፡

  ድርጅቱ ሥራ ከጀመረ አምስት ወራት አካባቢ መሆኑን ጠቁመው፣ ሥራቸው ሕገወጥ ባለመሆኑ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን ጠይቀው ውሳኔ እየጠበቁ መሆኑን የሀኦነንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ተወካይ ለሪፖርተር ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ድርጅቱ የሐበሻ ቢራንና የሜታ ቢራን ሌብል ለማምረት የናሙና ምርት ከመሥራት ውጪ ሌላ ሥራ እንዳልሠራና ውልም እንዳልፈጸመ ተወካዩ አስረድተዋል፡፡  

  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -spot_img

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች