Saturday, August 13, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየፌዴሬሸን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት መጋዘን ተዘረፈ

  የፌዴሬሸን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት መጋዘን ተዘረፈ

  ቀን:

  የኢሕአዴግ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት ግዙፉ ቅጽር ግቢ ውስጥ የሚገኘው፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት መጋዘን ላይ ዘረፋ መካሄዱ ተሰማ፡፡

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ዕቃዎች ማከማቻ መጋዘን ዝርፊያ፣ የካቲት 19 ወይም 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ሳይከናወን እንዳልቀረ ተገልጿል፡፡ መጋዘኑ ተሰብሮም በርካታ ኮምፒዩተሮች መዘረፋቸው ታውቋል፡፡

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ገብሩ ገብረ ሥላሴ መጋዘኑ ሥራ በሌለባቸው የእረፍት ቀናት ተሰብሮ አሮጌ ኮምፒዩተሮች መዘረፋቸውን ለሪፖርተር አረጋግጠው፣ ዕቃዎች መጥፋታቸው የታወቀው የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም ሠራተኞች ወደ ሥራ በሚገቡት ወቅት መሆኑ ጠቁመዋል፡፡

  ‹‹ጉዳዩ በፖሊስ የተያዘና በመጣራት ላይ ያለ በመሆኑ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት አይቻልም፤›› ብለዋል፡፡ የኢሕአዴግና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት፣ እንዲሁም ፊት ለፊት የሚገኘው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚገኙበት ግዙፍ ቅጽር ግቢ፣ በፌዴራል ፖሊስ ጥብቅ ጥበቃ የሚደረግበት እንደሆነ ይታወቃል፡፡

  ነገር ግን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ይህ ጥበቃ እየተደረገለት እንዴት ሊዘረፍ እንደቻለ ግርምት እንደፈጠረባቸው ሪፖርተር ያነጋገራቸው ሠራተኞች ተናግረዋል፡፡ ጥብቅ ጥበቃ ከሚደረግበት ግቢ አሮጌ ኮምፒዩተሮችን መዝረፍ በራሱ አነጋገሪ ከመሆኑም በላይ፣ ምናልባት ከኮምፒዩተሮቹ ሐርድ ዲስክ ውስጥ መረጃዎችን ለማሸሽ ሊሆን ይችላል የሚል መላ ምት እየተሰነዘረ ይገኛል፡፡

  የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጉዳዩ በመጣራት ላይ ስለሆነ መረጃ ለመስጠት  ጊዜው አይደለም ብሏል፡፡ 

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት ጀመረ

  ሦስተኛ ዙር ሙሌት በዛሬው ዕለት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ...

  የክላስተር አደረጃጀት ፖለቲካዊ ውዝግብ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይባል የነበረውን አደረጃጀት...

  በወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው ከፍተኛ ሀብት ጥቅም ላይ እየዋለ አይደለም ተባለ

  በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው የተቀማጭ ገንዘብ መጠን...