Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየወላይታ ዞን ባለሥልጣናት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቀብለው ከኃላፊነት ለቀቁ

  የወላይታ ዞን ባለሥልጣናት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቀብለው ከኃላፊነት ለቀቁ

  ቀን:

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ግጭት በተከሰተባቸው የደቡብ ክልል የሲዳማ፣ የወላይታ፣ የወልቂጤና የቀቤና የዞንና የወረዳ አስተዳዳዎች ከኃላፊነታቸው እንዲለቁና ለደረሱ ጥፋቶች ኃላፊነት እንዲወስዱ ማሳሰቢያ ከሰጡ በኋላ፣ የወላይታ ዞን አምስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከኃላፊነታቸው ተነሱ፡፡

  ‹‹ይህ ሙሉ በሙሉ አዎንታዊና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚደረጉ ለውጦችን ለመደገፍ የሚረዳ ነው፤›› ብለው እንደሚያምኑ የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ጌታሁን ጋረደው (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

  ምክትል አስተዳዳሪው እንደገለጹት ኃላፊዎቹን የሚተኩ ሰዎች እስከሚሾሙና ቦታቸውን እስከሚረከቡ ድረስ፣ ሁሉም ኃላፊዎች በሥራ ላይ እንደሚቆዩና የመፍትሔው አካል ለመሆን እንደሚሠሩ አስታውቀዋል፡፡

  ሥራቸውን በፈቃደኝነት የለቀቁ የሥራ ኃላፊዎች የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አስራት ጤራን ጨምሮ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ፣ የዞኑ የደኢሕዴን/ኢሕአዴግ የድርጅት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ የገጠርና የከተማ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊዎች ናቸው፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...