ይኼ የእኔ ግጥም ፍቅር ካልጨመረ፣
ይኼ የእኔ ግጥም ጥላቻ ካልሻረ፤
ይኼ የእኔ ግጥም ውበት ካላሰሰ፣
ይኼ የእኔ ግጥም ፋኖስ ካልለኮሰ፤
ተስፋ ካላሸተ – ሰላም ካላወጀ፣
ይኼ የእኔ ግጥም ድልድይ ካላበጀ፤
ባይተዋር ልቦችን ቀርቦ ካልዳበሰ፣
ያዘኑ ነፍሶችን ስቃይ ካልፈወሰ፣
የፈርኦን ቅጥርን ካልደረማመሰ፣
ይኼን የእኔን ግጥም ፤ ይኼን የእኔን ስንኝ፣
በሚነደው እሳት ዶግ አመድ አ’ርጉልኝ፡፡
– ሰሎሞን ሞገስ (ፋሲል) ‹‹የተገለጡ ዓይኖች›› (2009)