ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ቅዳሜ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በተካሄደው ሰልፍ ላይ የደረሰው የቦምብ ፍንዳታ የተጠናና በሙያተኛ የታገዘ ነበር አሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥቂት የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውንና ይህ ለለውጥ ሲባል የተከፈለ መስዋዕትነት ነው ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ባደረጉ ሰዎች ላይ ማዘናቸውንና የሞቱት ነፍሳቸው እንዲማር፣ የቆሰሉት እንዲታከሙ፣ ቤተሰቦች እንዲጽናኑ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡