Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፓርትየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ገበና በአትሌቶቹ

  የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ገበና በአትሌቶቹ

  ቀን:

  የኢትዮጵያ አትሌቲክስና አትሌቶች በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በውጤት ማጣት ሳቢያ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ የሚያደርጓቸው ተሳትፎዎች እየቀነሱ መምጣታቸው ይነገራል፡፡ ለዚህ በሰበብነት ከሚጠቀሱት ምክንያቶች ውስጥ በስም ‹‹ተቋም›› የሚመስለው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፈዴሬሽን እንደሆነ ሰሞኑን የኢትዮጵያ አትሌቶች ማኅበር ረቡዕ ሰኔ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ወጣቶች ስፖርት አካዴሚ በጠራው የውይይት መድረክ የአትሌቲክሱ ገበና በራሳቸው በአትሌቶቹ የእርስ በርስ ሙግት ሲገለጽ ተደምጧል፡፡

  የማኅበሩ አመራሮች በጠሩት የውይይት መድረክ የአትሌት ማናጀር ተወካዮችና አሠልጣኞች እንዲሁም አትሌቶች በወቅታዊው የአትዮጵያ አትሌቲክስ የመምረጫ መሥፈርት፣ ማዘውተሪያ ሥፍራና በአጠቃላይ በተቋሙ መዋቅራዊ አደረጃጀት ላይ ሲናገሩ እንደተደመጠው ከሆነ፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በስም ትልቅ ውስጡ ሲፈተሽ  ግን፣ እጅግ በውስብስብ ችግሮች የተተበተበ፣ ተቋማዊ ቁመና የሌለው፣ የአትሌቶቹን ጥቅምና ተሳትፎ በማስከበር ረገድ ይህ ነው የሚባል ድርሻና ሚና እንደሌለው ጭምር በድፍረት ሲናገሩ ተደምጧል፡፡

  በግንባታና መሰል መሠረተ ልማቶች የተነሳ የልምምድ ሥፍራዎች እየጠፉ አትሌቶች አስፋልት ላይ ከመኪናና መሰል ግዑዝ ነገሮች ጋር እየተጋፉ የሚያደርጓቸው ልምምዶች ለአደጋ የሚጋለጡበት ዕድል እየሰፋ መምጣቱና ለዚህ የሚመለከተው ፌዴሬሽን የመፍትሔው አካል ሊሆን አለመቻሉ ጭምር በአትሌቶች ሲነገር ተደምጧል፡፡ በዚህ የተነሳ በርካታ አትሌቶች ለልምምድ በሚሮጡባቸው ጎዳናዎች የመኪና አደጋ እየደረሰባቸው እንደሚገኙ፣ በዚህ ላይ ለዓለምና ለአኅጉር ውድድሮች የሚያበቁ የአትሌቶች መምረጪያ መሥፈርት እንዲሁም በውጭ ለውድድር ሲሄዱ ከአትሌቶቹ ይልቅ ተጠቃሚዎቹ የውድድር አዘጋጆችና ወኪሎች ስለመሆናቸው ተነግሯል፡፡

  ኢትዮጵያ ከመካከለኛ ርቀት እስከ ማራቶን ባሉት የውድድር መድረኮች ለዓመታት የዘለቀ አኩሪ ታሪክ እንዳላት በማኅበሩ ፕሬዚዳንት ስለሺ ስህን የመግቢያ ንግግር በተጀመረው በዚሁ የውይይት መድረክ፣ በፌዴሬሽኑ ባለቤትነት ለሁለት አሠርታት ያህል ተይዞ፣ ምንም ዓይነት ግንባታም ሆነ አገልግሎት ሳይሰጥ የቆየው የሰንዳፋ አትሌቲክስ መንደር ለመሬት ባንክ ገቢ የሆነበት ሁኔታና ምክንያት ተነስቶ ትችትና ወቀሳ ቀርቦበታል፡፡ በአትሌቲክሱ እየታየ ያለው የማዘውተሪያ ዕጦት እንደተጠበቀ፣ ‹‹በእንቅርት ላይ . . .›› እንዲሉ በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዳሉበት፣ የማናጀሮች ተወካይና አሠልጣኝ በሆኑት በአቶ ገመዶ ደደፎ ተቋሙ ሲብጠለጠል ተደምጧል፡፡ የአሠልጣኙን አስተያየት ሌሎችም የመድረኩ ታዳሚዎች አንፀባርቀውታል፡፡

  አሠልጣኙ አስተያየታቸውን ሲቀጥሉ፣ ‹‹ማኅበሩስ ቢሆን እስከዛሬ የት ነበር? ምክንያቱም የአትሌቶች መምረጫ መሥፈርቱን ጨምሮ የማዘውተሪያ ችግሮች እንዳሉ የአትሌቶች ቅሬታና ብሶት ሲደመጥ ዓመታት ተቆጥረዋል፤›› በማለት የችግሩን ዘርፈ ብዙነት ተናግረዋል፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑን በመወከል በውይይቱ የተገኙት የቴክኒክ ዳይሬክተሩ አቶ ዱቤ ጅሎና የጽሕፈት ቤት ኃላፊው አቶ ቢልልኝ መቆያ በበኩላቸው፣ የቀረቡት አስተያየቶችና ትችቶች የአትሌቲክሱን ዕድገት ከመመኘት እንደሆነ፣ ሆኖም ግን  የሚፈለገው ዕድገትም ሆነ ለውጥ ሊመጣ የሚችለው አንዱ በሌላው ጣት በመቀሰር ሳይሆን፣ ተቀራርቦ በመሥራትና የጋራ ተጠያቂነት ሲኖር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

  የማኅበሩ አመራሮች በበኩላቸው፣ ‹‹ማኅበሩስ የት ነበር?›› ለሚለው ቅሬታ፣ ‹‹ችግሮቹ መፍትሔ ያገኛሉ በሚል ካልሆነ በስተቀር፣ ማኅበሩ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ቅሬታውን ያላቀረበበት ወቅት የለም፡፡ በአሁኑ ወቅት ይህን መድረክ ለማመቻቸት ያነሳሳው ችግሮቹ መፍትሔ ማግኘት ባለመቻላቸው ነው፤›› ብለዋል፡፡ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቦርድ አመራሮች መካከል ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ፣ በአትሌቶች ማኅበርም ሆነ በአትሌቶቹ የቀረበውን ቅሬታ ሙሉ በሙሉ እንደምትጋራው ገልጻለች፡፡ ችግሮቹ እሷም ተወዳዳሪ በነበረችባቸው ጊዜያት ጀምሮ የነበሩ ስለመሆናቸውም ተናግራለች፡፡

  በውይይቱ የተገኙት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ‹‹በአትሌቲክሱ መቀለድ በአንድ ዓይን እንደ መቀለድ ይቆጠራል፤›› ብለው፣ ችግሮቹን በጋራ ለመፍታት ተቀራርቦ መነጋገርና መወያየት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡            

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...