ቅዳሜ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) ለመደገፍ የተደረገው ሰልፍ ላይ ከደረሰው የቦምብ ጥቃት ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርን ጨምሮ ዘጠኝ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባልደረቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡
በሰልፉ ላይ በተወረወረ ቦምብ 154 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውና አንድ ግለሰብ መሞቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
ማምሻውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ከሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር በመሆን በአደጋው የተጎዱ ሰዎችን በሆስፒታሎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡