Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናከፍተኛ የሕግ ምሁራን የተካተቱበት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ ተቋቋመ

  ከፍተኛ የሕግ ምሁራን የተካተቱበት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ ተቋቋመ

  ቀን:

  ‹‹የፍትሕ ተቋማት የገዥዎች ዱላ መሆን የለባቸውም››

  የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ

  ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ፣ ፕሮፌሰር ዘካርያስ ቀነዓ፣ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ፣ አቶ ሰለሞን አረዳ፣ አቶ ማሞ ምሕረቱ፣ በላቸው መኩሪያ (ዶ/ር)፣ አቶ ሊቁ ወርቁ፣ አቶ ታደለ ነጊሾ፣ ወ/ሮ መሠረት ሥዩም፣ ወ/ሮ ሰምሃል ጌታቸው፣ አቶ ዓሊ መሐመድ፣ አቶ ታምሩ ወንድማገኘሁና ዘውድነህ በየነ (ዶ/ር) የተባሉ ታዋቂ የሕግ ምሁራን አባል የሆኑበት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ ተቋቋመ፡፡

  የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ የጉባዔውን መቋቋም አስመልክተው ዓርብ ሰኔ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለምክር ቤቱ ሪፖርት ሲያቀርቡ ጉባዔው እንደሚቋቋም መናገራቸውን አስታውሰዋል፡፡ የጉባዔው ዋና ተግባር ሙያ፣ ዕውቀትና ክህሎትን መሠረት በማድረግ የሕግና የፍትሕ ሥርዓቱን ማሻሻል በመሆኑ፣ በሕግ ከፍተኛ ዕውቀትና ልምድ ያላቸውን ምሁራን በማካተት ምክር ቤቱ መቋቋሙን አስታውቀዋል፡፡

  ‹‹ሕግ ራሱን የቻለ ልዕልና ያለው ሊሆን ይገባል፡፡ ተቋማቱም ለፍትሕ የታመኑ መሆን ይጠበቅባቸዋል፤›› ያሉት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ብርሃኑ ሕግ መሣሪያ፣ የፍትሕ ተቋማቱም የገዥዎች ዱላ እየሆኑ ከሄዱ መበላሸታቸው አይቀሬ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ለአብነት ያህል የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ሕግና የሚዲያ ሕግ፣ በማኅበረሰቡ ላይ በተለያዩ ጊዜያት በይዘታቸውና በአፈጻጸማቸው ላይ የተለያዩ እሮሮዎች ሲሰሙባቸው መቆየታቸውን ጠቁመዋል፡፡

  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹የሕግ የበላይነትና ፍትሕ ከተነጣጠሉ፣ ሕግ የጭቆና መሣሪያ ይሆናል፤›› ማለታቸውን ያስታወሱት አቶ ብርሃኑ፣ ችግሮችን ለመፍታት ሠራተኛንና አመራርን መቀየር ብቻ በቂ አይደለም ብለዋል፡፡

  ረዥም ልምድ፣ ብቃትና ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት ያላቸውን ባለሙያዎችንና ማኅበረሰቡን በበቂ ሁኔታ በማሳተፍ በተገቢው ልክ መረጃና ሙያን መሠረት አድርጎ መፍትሔዎች በበቂ ሁኔታ ተለይተው አለመተግበራቸውን አቶ ብርሃኑ ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም አማካሪ ጉባዔውን በመመሥረት የሚጀመረው ማሻሻያ ፕሮግራም የነበሩትን ልምዶችና ውስንነቶች ግምት ውስጥ በማስገባት፣ መሠረታዊ ለውጥ ይመጣል የሚል እምነት እንዳላቸው አክለዋል፡፡ አማካሪ ጉባዔው በጽሕፈት ቤት በሚደራጁ የሙሉ ጊዜ ሠራተኛ ባለሙያዎች እንደሚታገዝ፣ ለጊዜው አምስት የሥራ ቡድኖች ተዋቅረው የመነሻ ሥራዎችን እያከናወኑ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡  

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...