Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዝንቅፓንዶራና አፈታሪኳ

  ፓንዶራና አፈታሪኳ

  ቀን:

  በጥንታዊ የግሪክ አፈታሪክ ፓንዶራ በምድር ላይ የመጀመሪያዋ ሴት ነበረች። የአማልክት አምላክ ዜዑስ፡ የጥበብ አምላክ የሆነችውን ሔፋስቱስ፡ ፓንዶራን ከምድር አፈርና ውኃ አድቦልቡላ ትሠራት ዘንድ አዘዛት። ሌሎች አማልዕክትም እንደየችሎታቸው ለፓንዶራ ስጦታ አበረከቱላትአፍሮዳይት ቁንጅናን፣ አፖሎ ሙዚቃ፣ ሔርመስ ደግሞ የንግግር ችሎታን ሰጧት። ስሟ ፓንዶራም ትርጉሙ ‹‹ሁሉየተሰጣት›› ማለት ነው።

  ፕሮሚትየስ ከገነት እሳትን በሰረቀ ግዜ፣ ዜዑስ ተቆጣ፤ ብቀላም ይሆን ዘንድ ፓንዶራን አሳልፎ ለፕሮሚትየስ ወንድም ሰጠ። ፓንዶራም በማንኛውም ሁኔታ ቢሆን እንድትከፍት ያልተፈቀደላት ትንሽ ሳጥን ተሰጣት። ይሁን እንጂ በተፈጥሮ አለቅጥ የተቸራት ጉጉቷ በዛና ፓንዶራ ያንን ሳጥን ከፈተችው። ነገር ግን በሳጥኑ ተከድኖ ተቀምጦ የነበረው ‹‹ክፋት›› ከሳጥኑ አምልጦ ወጣ፤ በመላው ምድርም ተሰራጨ። ፓንዶራ ተቻኩላ ሳጥኑን ለመዝጋት ሞከረች፤ ነገር ግን በሳጥኑ ውስጥ የነበረው ሁሉ ድሮ ወጥቶ አልቋልከአንድ ነገር በስተቀር። ያም ‹‹ተስፋ›› ነበር። ፓንዶራ በሠራችው ሁሉ አዘነች፤ ተጸጸተችም። የተጣለባትንላፊነት በአግባቡ ባለመወጣቷ የዜዑስን የቁጣ ውርጅብኝ በፍርኅት መጠባበቅ ጀመረች። ዜዑስ ግን አልቆጣትምይህ እንደሚሆን ያውቅ ነበርና።

  ቴዎድሮስ ሸዋንግዛው ‹‹ቡክ ፎር ኦል››

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...