ኢትዮጵያና ኤርትራ ዕርቅና ሰላም ባወረዱበት ማግስት ከተለያየ የኅብረተሰብ ክፍል የተውጣጣና በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሚመራው 456 ሰውን የያዘው የሕዝብ ለሕዝብ ቡድን፣ ሐምሌ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. አስመራ ከተማ ገብቷል። የልዑካን ቡድኑን በአስመራ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት በመገኘት አቀባበል ያደረጉለት የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኡስማን ሳልኽ ናቸው፡፡ ፎቶዎቹ የአቀባበሉን ሥነ ሥርዓትና ለ20 ዓመታት ተለያይተው የነበሩ ቤተሰቦች ሲገናኙ የተፈጠሩትን ስሜቶች ያሳያሉ፡፡
- ፎቶ ከድረ ገጽ