Sunday, August 14, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  ክቡር ሚኒስትር

  [የክቡር ሚኒስትሩ ሚስት በጣም ተቆጥተዋል]

  • ምን ሆነሻል?
  • ጋዜጣው ላይ የተጻፈውን አንብበኸዋል?
  • ምንድን ነው የተጻፈው?
  • ለመሆኑ ምን እየሠራችሁ ነው?
  • ሥራችንን ነዋ የምንሠራው፡፡
  • እኮ ሥራችሁ ምንድን ነው?
  • አገር ማልማት ነዋ፡፡
  • ማጥፋት ማለትህ ነው?
  • ሴትዮ ምንድን ነው የምታወሪው?
  • ዘመኑ የኢንፎርሜሽን መሆኑን ረሳችሁት እንዴ?
  • ዘመኑማ የኢሕአዴግ ነው፡፡
  • ለመሆኑ ሕግ የምታወጡት ምንን መሠረት አድርጋችሁ ነው?
  • የሕዝብን ጥቅም ነዋ፡፡
  • ኧረ አይመስለኝም፡፡
  • ታዲያ ምንን መሠረት አድርገን ነው?
  • ምቀኝነትን፡፡
  • ምን እያልሽ ነው?
  • በኢንተርኔት ስልክ መደወል ልትከለክሉ ነው አይደል?
  • ታዲያ መንግሥት በሠራው መሠረተ ልማት ኒዮሊብራሊስቶች ኪሳቸው ሲደልብ ዝም ብለን እንይ?
  • መወዳደር ነዋ፡፡
  • ከኒዮሊብራሊስቶቹ ጋር?
  • ታዲያ ሥራ እንድፈታ ነው የምትፈልገው?
  • ለምን ትፈቻለሽ?
  • ሥራዬን የምሠራው በስልክ እንደሆነ ታውቃለህ?
  • ስልክሽ ተቋረጠ እንዴ?
  • ስልክ እኮ የምደውለው አገር ውስጥ ሳይሆን ውጭ ነው?
  • ታዲያ መደወል ነዋ፡፡
  • ሰውዬ የአንተን ስልክ እኮ መንግሥት ስለሚከፍልልህ ምንም ላይመስልህ ይችላል፡፡
  • የአንቺን ስልክ ራስሽ የምትከፍዪ ትመስያለሽ?
  • ስማ ውጭ ካሉት ዕቃ አቅራቢዎች ጋር በየቀኑ በኢንተርኔት ነው እኮ የምደዋወለው?
  • እና አሁን ማን ከለከለሽ?
  • ይኸው ሊቆም አይደል እንዴ?
  • ምኑ?
  • What’s up?
  • እሱማ መቆም አለበት፡፡
  • ለምን?
  • ባህላችን አይደለም፡፡
  • ምንድን ነው ባህላችን?
  • የእኛ ባህል እንዴት ዋልሽና እንዴት አደርሽ ነው? የምን What’s up ነው?
  • ሰውዬ ስለቴክኖሎጂ ምንም አታውቅም እንዴ?
  • ቴክኖሎጂንና What’s up ምን አገናኘው?
  • በኢንተርኔት ስልክ መደወያ አፕሊኬሽን ነው እኮ?
  • ነው እንዴ?
  • አይ የአንተ ነገር?
  • በViber ተጠቀሚያ፡፡
  • እሱም ሊከለከል ነው፡፡
  • ግን እኮ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጐበታል አይደል?
  • ለመሆኑ ማን ነው ባለድርሻ አካል?
  • እ…
  • በዚህ ጉዳይ እኮ ባለድርሻ አካሉ ተጠቃሚው ሕዝብ ነው፡፡
  • እና Viber ተጠቃሚ ሁላ እንዲወያይ ትፈልጊያለሽ?
  • እንደዛ ካልሆነ መተው ነዋ፡፡
  • ምኑ ነው የሚተወው?
  • ክልከላው!

  [የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ቢሯቸው ገባ]

  • ክቡር ሚኒስትር በጀቱ ተፈቅዷል፡፡
  • የምን በጀት?
  • ያቀረብነው ፕሮፖዛል በዶነሮቹ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡
  • የትኛው ፕሮፖዛል ነው?
  • የምርምር ተቋም ለመገንባት ያስገባነው ፕሮፖዛል፡፡
  • ስንት ነበር የጠየቅነው?
  • ሁለት ሚሊዮን ዶላር፡፡
  • ይቺ እኮ አንድ ኮንቴይነር ዕቃም አትጭን፡፡
  • የምን ኮንቴይነር ነው?
  • ይቅርታ ከሌላ ነገር ጋር ተጋጭቶብኝ ነው፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ዕቃ ያስመጣሉ የሚባለው እውነት ነው እንዴ?
  • የምን ዕቃ?
  • እንደሚባለውማ የማያስመጡት ዕቃ የለም አሉ፡፡
  • ሰው መቼም የሚሠራ ሰው አይወድም፡፡
  • ሰውማ የሚጠላው ሌላ ነገር ነው፡፡
  • ምንድን ነው የሚጠላው?
  • የሚሰርቅ ሰው!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ውጭ ያለ ዘመዳቸው ጋ ደወሉ]

  • አቤት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ስማ አንድ ሥራ እልክልሃለሁ፡፡
  • የምን ሥራ ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • ለአንድ ፕሮጀክት ዶነሮች ፈንድ ለቀዋል፡፡
  • በጣም ደስ ይላል ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ፕሮጀክቱን ደግሞ የውጭ ኩባንያ ቢሠራው እነሱ ለመቀበል ይቀላቸዋል፡፡
  • ለዚህ አይደል እንዴ እዚህ ይኼን ኩባንያ የከፈትነው፡፡
  • ስማ ፕሮጀክቱ ለእኛ መሥሪያ ቤት የምርምር ተቋም ማቋቋም ነው፡፡
  • በጀቱ ምን ያህል ነው?
  • ሁለት ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡
  • ምነው ክቡር ሚኒስትር ያለመደብዎትን?
  • ምነው?
  • ሁለት ሚሊዮን ምን አላት ብዬ ነዋ?
  • እሱስ ልክ ነህ፡፡
  • ከቪ8 እና ከቤት ዕቃ አታልፍም እኮ፡፡
  • ያው ዶላሯ ትጠቅማለች ብዬ ነው፡፡
  • ለነገሩ የተረፈው የልጆች ትምህርት ቤትና ለቤተሰቡ መዝናኛም ይሆናል፡፡
  • እኔም እሱን ብዬ ነው፡፡

  [ክቡር ሚኒስትሩ ሼር ያላቸው ኩባንያ ባለቤት ጋ ደወሉ]

  • አቤት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ለአንድ አዲስ ቢሮ ሙሉ የቢሮ ዕቃ ይዘጋጅ፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ዕቃ የለም፡፡
  • ለምን ተብሎ?
  • ኤልሲ የለም፡፡
  • ስለእሱ አታስብ፡፡
  • ታዲያ ምን ላስብ?
  • ኮሚሽኔን!

  [ፕሮጀክቱን ፈንድ ያደረገው ድርጅት ኃላፊ ክቡር ሚኒስትሩ ጋ ደወለ]

  • ሄሎ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ሄሎ ፈንደር፡፡
  • ምን እየተሠራ ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • ሥራ ነዋ፡፡
  • ፕሮጀክቱ ሳይጠናቀቅ ገንዘቡን አጠናቀቃችሁት እኮ?
  • የአቅም ግንባታ ላይ ብዙ ስላወጣን እኮ ነው፡፡
  • የማን አቅም ነው የተገነባው?
  • የሠራተኞቹ ነዋ፡፡
  • እኔ ግን የደረሰኝ ሪፖርት ሌላ ነው፡፡
  • የምን ሪፖርት ነው የደረሰህ?
  • የተገነባው አቅም የሠራተኞቹ አይደለም፡፡
  • የማን አቅም ነው የተገነባው ታዲያ?
  • የእርስዎ!

  [አንድ ደላላ ለክቡር ሚኒስትሩ ደወለ]

  • ምን እየተሠራ ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • ምንድን ነው የምታወራው?
  • ጡረታ መውጣት ፈለጉ እንዴ?
  • ኧረ የጡረታ ዕድሜ 80 መሆን አለበት እያልኩ ያለሁት እኔ አይደለሁ እንዴ?
  • እስከ ሰማንያ ዓመትዎ ሥልጣን ላይ ሊቆዩ?
  • ሰማንያ ስደርስም ማስጨመሬ አይቀርም፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር አዲሱ ሕግ ከወጣ እኮ ሥራ ልናቆም ነው፡፡
  • የምን ሕግ?
  • ቴሌ የሞባይል ስልኮች ካልተመዘገቡ እያለ ነው፡፡
  • ይመዝገቡዋ ታዲያ ምን ችግር አለው?
  • ታክስ ያልተከፈለበት ስልክ አገሪቷ ውስጥ መሥራት አይችልማ፡፡
  • እ…
  • ክቡር ሚኒስትር ከሥራ መፈናቀላችን ነው፡፡
  • ለመሆኑ ስንት ኮንቴይነር ስልክ ነው መጋዘን ያለው?
  • አራት ኮንቴይነር፡፡
  • እና አራት ኮንቴይነር ያልተሸጠ ስልክ አለ እያልከኝ ነው?
  • አዎን ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • የድለላ ሥራውን አቆምክ ልበል?
  • ክቡር ሚኒስትር እንቅስቃሴው እኮ ተቀዛቅዟል፡፡
  • አሁን ቴሌ የሚመዘገብ ነገር ጠፍቶ ነው ስልክ የሚመዘግበው?
  • የሚመዘገብ ነገር ምን አለ ብለው ነው?
  • ለምሳሌ የባለሥልጣን ሀብት፡፡
  • እሱማ ሲመዘገብ አብዛኞቻችሁ የምትገኙት አንድ ቦታ ነው፡፡
  • የት ነው የምንገኘው?
  • እስር ቤት!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ቴሌ ስልክ ሲደውሉ በአንድ ጥሪ ገባላቸው]

  • አቤት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እናንተ ጋ ለመደወል 25 ጊዜ ነው የሞከርኩት፡፡
  • ምን አሉኝ?
  • ኔትወርኩን ለምን አትሠሩትም?
  • ኧረ ይሠራል ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • የኔትወርኩን ሥራ ትታችሁ ሌላ ነገር ለምን ትፈተፍታላችሁ?
  • ምን ፈተፈትን ክቡር ሚኒስትር?
  • ሞባይል ስልክ ልትመዘግቡ ነው አሉ?
  • አዎን ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ባትመዘግቧቸው ምን አለበት?
  • ታክስ ያልከፈሉትን ለመለየት ነዋ፡፡
  • ለመሆኑ ታክስ ያልተከፈለባቸው ስልኮች ምን ይደረጋሉ?
  • እዚህ አገር መሥራት አይችሉማ፡፡
  • ታዲያ የት ልንሸጣቸው ነው?
  • ምኖቹን ክቡር ሚኒስትር?
  • ማለቴ ታክስ ባይከፍሉ ምን ችግር አለው?
  • ክቡር ሚኒስትር ታክስ ከፍለው ስልክ የሚያስገቡት እየተጐዱ ነው፡፡
  • ነፃ ገበያ አይደል እንዴ?
  • እሱማ ነፃ ገበያ ነው፡፡
  • ይወዳደሩዋ ታዲያ?
  • ምን ነካዎት ክቡር ሚኒስትር?
  • ወደ ቁም ነገሩ እንምጣና አራት ኮንቴይነር ስልክ ያለው ሰው ምንድን ነው የሚደረገው?
  • እሱማ እጁን ቢሰጥ ይሻለዋል፡፡
  • እጅህ ይቆረጥ!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ደላላው ጋ ደወሉ]

  • ምን አገኙ ክቡር ሚኒስትር?
  • አፋጣኝ መፍትሔ ያስፈልጋል፡፡
  • ሕጉ እንዳይወጣ ማድረግ አይችሉም?
  • እሱ የሚቻል አይመስለኝም፡፡
  • ምን ይደረግ ታዲያ?
  • ሞባይሎቹን መልሰን ኤክስፖርት ማድረግ አለብን፡፡
  • እንዴት አድርገን?
  • ሌላ አገር መሸጥ አለባቸው፡፡
  • ኤክስፖርት ለማድረግ እኮ እዚህ አገር እሴት መጨመር አለበት፡፡
  • ከዚህ በላይ እሴት እንዴት ይጨመርበት?
  • አልገባኝም ክቡር ሚኒስትር?
  • ኢትዮጵያ እኮ የተቀደሰች አገር ናት፡፡
  • ስለዚህ?
  • ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ በመውጣቱ ብቻ እሴት ተጨምሮበታል ማለት እንችላለን፡፡
  • እንዴት ሆኖ?
  • ኢትዮጵያ እኮ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠራች አገር ናት፡፡
  • ለነገሩ ከዚህ በላይ እሴት መጨመር ምን አለ?
  • እሱን እኮ ነው የምልህ፡፡
  • ስለዚህ ምን ይደረግ?
  • ፈቃድ ይውጣ፡፡
  • የምን?
  • የሪኤክስፖርት!  

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  በወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው ከፍተኛ ሀብት ጥቅም ላይ እየዋለ አይደለም ተባለ

  በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው የተቀማጭ ገንዘብ መጠን...

  የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት ጀመረ

  ሦስተኛ ዙር ሙሌት በዛሬው ዕለት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ...

  በቴሌ ብር የማይሠሩ ማደያዎች ቀነ ገደብ ተቀመጠባቸው

  ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ለመሥራት እየመከረ ነው በኢትዮጵያ...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...

  ለኬንያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሸጥበት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገበት

  በቅርቡ ሙሉ ለሙሉ ስምምነቱ የተጠናቀቀው የኢትዮጵያና የኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሥራ አጥነት ችግሮችን የመፍታት ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም በዋና ጽሕፈት ቤቱ ሕንፃና ቢሮዎች ላይ ያደረገውን ዕድሳት መርቀው በመክፈት ጉብኝት እያደረጉ ነው]

  እጅግ ውብ ዕድሳት ያደረጋችሁት! በእውነቱ በጣም ድንቅ ነው፡፡ አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። በጣም ድንቅ ነው። ዕድሳቱን ያከናወነው ድርጅት ጥሩ ልምድ ያለው ይመስላል? ተቋራጩ ማን እንደሆነ አልነገርኩዎትም እንዴ? የትኛው ተቋራጭ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ በስንዴ የተሸፈኑ ሰፋፊ እርሻዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመገምገም ከስንዴ ምርት ድጋፍና ክትትል ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር እየመከሩ ነው] 

  ክቡር ሚኒስትር እንደነገርክዎት በሁሉም ስንዴ አብቃይ አካባቢዎቻችን ያሉ አርሶ አደሮች ጥሪያችንን ተቀብለው መሬታቸውን በኩታ ገጠም አርሰው በስንዴ ዘር ሸፍነዋል። በጣም ጥሩ ዜና ነው። በጣም እንጂ። የሚገርምዎት...

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሚመሩት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ አጀንዳ አድርጎ በያዘው ወቅታዊ የፀጥታና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት ቢጀመርም በስተመጨረሻ አጀንዳውን ስቶ ስለ መዋደድ እየተጨቃጨቀ...

  በዛሬው መደበኛው መድረካችን አጀንዳ የተለመደው የፀጥታና ደኅንነት ጉዳይ ይሆናል። ሌላ አጀንዳ የምታስይዙት አጀንዳ ከሌለ በቀር ማለቴ ነው። ክቡር ሚኒስትር... እሺ ...ቀጥል አመሰግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። መደበኛ አጀንዳው እንደተጠበቀ...