Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሁለት ሲኖዶሶች አንድ ሆኑ

  የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሁለት ሲኖዶሶች አንድ ሆኑ

  ቀን:

  ቃለ ውግዘቱን ለማንሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ይጠበቃል

  በኢትዮጵያና በአሜሪካ በሚገኙትና በኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያን ስም የሚጠሩ ሲኖዶሶችን ወደ አንድ ለማምጣት፣ ለበርካታ ዓመታት ሲደረግ የነበረው ጥረት እልባት አገኘ፡፡

  በ1983 ዓ.ም. ከተደረገው የመንግሥት ለውጥ በኋላ አራተኛው ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ መንበራቸውን መልቀቃቸውን ተከትሎ፣ ከተወሰኑ አባቶች ጋር ከአገር በመውጣትና በስደት ሲኖዶስ በማቋቋም መለያየታቸው ይታወቃል፡፡

  በአዲስ አበባና በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኙ ሲኖዶሶች መካከል ዕርቀ ሰላም ለማውረድ የተደረገው ተደጋጋሚ ጥረት ዕልባት ያገኘው፣ ከሁለቱ ሲኖዶሶች ብፁዓን አባቶች እንዲሁም ከካህናትና ምዕመናን በተውጣጣው የሰላም ኮሚቴ አማካይነት ከሐምሌ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ባካሄደው ውይይት ስምምነት ላይ ተደርሶ ነው፡፡

  በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ወተርጌት ሆቴል ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ይፋ እንደተደረገው፣ ሁለቱም ፓትርያርኮች በእኩል ክብር ቤተ ክርስቲያኒቱን ያገለግላሉ፡፡

  በዚህም መሠረት የአገር ቤትና የውጭ አገር ሲኖዶስ የሚለው ስም ቀርቶ አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ እንዲሆን ሲወሰን፣ በሁለቱም ሲኖዶሶች የተላለፈው ቃለ ውግዘት በጋራ ምልዓተ ጉባኤ ይፈታል ተብሏል።

  በውሳኔው መሠረት ‹‹ስደተኛውን ሲኖዶስ›› ሲመሩ የቆዩት አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ  አቡነ መርቆሬዎስ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመለሱና ጸሎትና ቡራኬ በማድረግ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያገለግሉ ሲወሰን፣ ስድስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በአስተዳደር ሥራ ቤተ ክርስቲያንን በመምራት ጸሎትና ቡራኬ በማድረግም  ቤተ ክርስቲያንን ያገለግላሉ፡፡

  ከልዩነት በፊት የተሾሙ ነባር ሊቃነ ጳጳሳትን በተመለከተ በሁለቱ ሲኖዶስ የተላለፈው ቃለ ውግዘት በጋራ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተፈቶ ስማቸውና ክብራቸው ተጠብቆ በውጭም ሆነ በአገር ቤት በሀገረ ስብከት እንዲመደቡና እንዲያገለግሉ፣ ከልዩነት በኋላ በሁለቱም ወገኖች የተሾሙትም ስማቸውን እንደያዙ ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲቀበላቸውና በውጭም ሆነ በአገር ቤት ተመድበው እንዲያገለግሉ፣ ስም አጠራራቸውንም አስመልክቶ እንደ ሹመት ቅደም ተከተላቸው ቀዳማይ፣ ካልዓይ፣ ሣልሳይ እየተባሉ እንዲጠሩ ጉባዔው በአንድ ድምፅ ወስኗል።

  በተጨማሪም በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል የተደረገውን የዕርቀ ሰላም ስምምነት ለመተግበርና የሁለቱንም ውህደት ፍጹም ለማድረግ፣ እንዲሁም በስደት የሚገኙ ብፁዓን አባቶች ወደ አገራቸው ተመልሰው በአንድ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚተዳደሩበትን ቅድመ ሁኔታ የሁለቱም ቅዱስ ሲኖዶስ ተወካዮች  እንዲያዘጋጁና  እንዲከታተሉ  መወሰኑን የወጣው መግለጫ ያመለክታል፡፡

  የሁለቱ ሲኖዶሶች አባላት በመስማማታቸው ለኢትዮጵያ ሕዝብ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት በአንድነት መድረኩ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ባደረጉት ንግግር፣ ‹‹ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አንድ ስትሆን እኛም አንድ እንሆናለን፤›› ብለዋል። ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገር ነች፤›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ቤተ ክርስቲያኗ ታላቅ ታሪክ፣ ስም፣ ዝና እና ትውፊት ባለቤት ስትሆን ኢትዮጵያ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውጭ አትታሰብም ብለዋል።

  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በራሷ ፓትርያክ መመራት ከጀመረችበት ከ1951 ዓ.ም. ጀምሮ ስድስት ፓትርያርኮች በመንበሩ ተቀምጠዋል፡፡ ሁለተኛው ፓትርያርክ (1963-1968) የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ተላልፈው ለሞት ከተሰጡበት ጊዜ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያን ቀኖና ጥሰት መፈጸሙ ይነገራል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...