Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ

  የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ

  ቀን:

  ምክትል ከንቲባው ካቢኔያቸውን ይፋ ያደርጋሉ

  የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ለዓርብ ነሐሴ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ፡፡ የዕለቱ አጀንዳ ቀጣዩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) አዲስ ካቢኔ ማፅደቅ ነው፡፡

  አቶ ታከለ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ከተሾሙት ከወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስና ከሰለሞን ኪዳኔ (ዶ/ር)፣ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ጋር በመሆን ቀጣዮቹን የካቢኔ አባላት ሲመለምሉ ቆይተዋል፡፡

  ምንጮች እንደጠቆሙት ምክትል ከንቲባው አብዛኞቹን የቀድሞ ካቢኔ አባላት በአዲስ ይተካሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

  በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ምርጫ ባለመካሄዱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዕድሜ ማራዘሚያ የሰጠው የአዲስ አበባ ምክር ቤት፣ በቋሚ ኮሚቴዎቹ አማካይነት ከአዲሶቹ ካቢኔ አባላት ጋር ተጠያቂነትን በሚመለከት ስምምነት ለመፈራረም ራሱን  የቻለ ዝግጅት እያካሄደ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

  የፌዴራል መንግሥት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር በጀመረው የተጠያቂነት አሠራር ቅርፅ በአዲስ አበባ ይኸው አሠራር የሚጀመር ሲሆን፣ የካቢኔ አባላት የሚመሯቸው ቢሮዎችም ሆኑ የከተማው ሥራ አስፈጻሚዎች በሙሉ ከቋሚ ኮሚቴዎች ጋር ስምምነት ይፈጽማሉ ተብሏል፡፡

  ይህ ስምምነት የሚያጠነጥነው እያንዳንዱ መሥሪያ ቤት በዕቅድ የያዛቸውን ሥራዎች፣ የኦዲት ሪፖርቶችና የምክር ቤት አባላት የሰጧቸውን አስተያየቶች ተግባራዊ መደረጋቸውን መመርመር ነው፡፡

  በዚህ መንገድ መሄድ ያልቻለ ሥራ አስፈጻሚ ተጠያቂ የሚሆንበት አሠራር ይዘረጋል ተብሏል፡፡ በስድስቱ የከተማው ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎችና በሥራ አስፈጻሚዎች መካከል ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ስምምነት ቀን ባይቆረጥለትም፣ አዲሶቹ የካቢኔ አባላት ኃላፊነታቸውን ከተረከቡ በኋላ የሚካሄድ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚካሄዱ የካፒታል ፕሮጀክቶችም ሆኑ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት የነዋሪዎችን ፍላጎት ከማርካት ይልቅ፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች የተንሰራፉባቸው መሆናቸው ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

  ምክትል ከንቲባ ታከለ ሥልጣን በተረከቡበት ወቅት የከተማውን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ ሥራዎች ይከናወናሉ ማለታቸው ይታወሳል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...