Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየመከላከያ ሠራዊትን አደረጃጀትና የሚገኝበትን አድራሻ አሳልፎ በመስጠት የተጠረጠሩ ወታደሮች ተከሰሱ

  የመከላከያ ሠራዊትን አደረጃጀትና የሚገኝበትን አድራሻ አሳልፎ በመስጠት የተጠረጠሩ ወታደሮች ተከሰሱ

  ቀን:

  የተጣለባቸውን አገራዊ አደራ ወደ ጎን በመተው፣ ራሱን አግአዴን (አርበኞች ግንቦት ሰባት) ለሚባለው ድርጅት፣ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊትን አደረጃጀትና የሚገኝበትን አድራሻ አሳልፈው በመስጠት የተጠረጠሩ ሁለት ወታደሮች የሽብር ተግባር ወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

  የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ወንጀል ችሎት በተከሳሾቹ ምክትል አሥር አለቃ አጃናው ታደሰና ምክትል አሥር አለቃ ቻሌ ነጋ ላይ ያቀረበው ክስ እንደሚያስረዳው፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የዘመቻ መምርያ ኃላፊ ለሆነው ክፈተው አሰፋ ወይም ዶክተር ከኤርትራ ኦማጆር አካባቢ ስልክ እየተደወለላቸው መረጃዎችን ማቀበላቸውን ገልጿል፡፡

  ተከሳሾቹ የመከላከያ ሠራዊት 6ኛ እና 25ኛ ክፍለ ጦር የሚገኙ ሬጅመንቶችን ብዛትና የት እንደሚገኙ፣ የራሳቸው የተከሳሾቹ ክፍለ ጦር ስንተኛ እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሲጠየቁ፣ እያንዳንዱ ክፍለ ጦር የት እንደሚገኝ አካባቢውንና የክፍለ ጦሩን አድራሻና ምድብ ቦታ ማሳወቃቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡ ከአንደኛው ዕዝ ወደ ሌላኛው ሠራዊት እየተቀላቀለ ወደ ሌላኛው ዕዝ እንደሚዘዋወር፣ በስልክና በቫይበር ግልጽ ማስረጃዎችን ተከሳሾቹ ለድርጅቱ ማሳወቃቸውን አስታውቋል፡፡

  በአጠቃላይ ተጠርጣሪዎቹ በተለይ የአገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር የገቡትን ቃል ኪዳን ወደ ኋላ በመተውና የአግአዴን/አርበኞች ግንቦት ሰባት ድርጅትን ተልዕኮ በመቀበል፣ የመከላከያ ሠራዊትን አደረጃጀትና የሚገኝበትን አድራሻ መረጃ አሳልፈው ለመስጠት፣ ከድርጅቱ ታጣቂዎች ጋር ለመቀላቀልና የድርጅቱ ተስፋ በመሆን በፈጸሙት በሽብር ቡድን በማንኛውም መልክ መሳተፍ ወንጀል እንደተከሰሱ ዓቃቤ ሕግ በክሱ አስረድቷል፡፡

  ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ አቅም እንዳላቸውና እንደሌላቸው ሲጠይቃቸው አቅም እንደሌላቸው ስለገለጹ፣ ተከላካይ ጠበቆች ጽሕፈት ቤት እንዲያቆምላቸው ትዕዛዝ ሰጥቶ ክስ ለመስማት ለግንቦት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...