Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየአዲስ አበባ ከተማ ሹም ሽር ወደ ታችኛው መዋቅር ሊሸጋገር ነው

  የአዲስ አበባ ከተማ ሹም ሽር ወደ ታችኛው መዋቅር ሊሸጋገር ነው

  ቀን:

  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ የሚገኘው የአመራሮች ሹም ሽር፣ ከማዕከል ወደ ክፍላተ ከተሞችና ወረዳዎች ሊሸጋገር ነው፡፡

  በዚህ ሳምንት በአሥሩም ክፍላተ ከተሞችና በ116 ወረዳዎች በዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚና በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊነቶች ላይ ሹም ሽር እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡ በኃላፊነት ቦታ ላይ በሚገኙ አመራሮች ላይ ከሚካሄድ ሹም ሽር በተጨማሪ፣ ሠራተኞችም እንደ አዲስ መንገድ እንደሚደራጁ ተገልጿል፡፡

  ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ቅዳሜ ነሐሴ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደገለጹት፣ በከተማ (በማዕከል) ደረጃ የተጀመረው ለውጥ እስከ ወረዳ ድረስ ይዘልቃል፡፡

  ‹‹አመራሩን ብቻ ሳይሆን ሠራተኛውንም በድጋሚ እናደራጃለን፤›› ያሉት ምክትል ከንቲባው፣ ‹‹በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለውን የሥራ መደራረብና ለእንግልት የሚዳርጉ አሠራሮችን በጥናት በመለየት አስፈጻሚውን አካል በድጋሚ እናደራጃለን፤›› ሲሉ ቀጣዩን የከተማ አስተዳደር ትኩረት አመላክተዋል፡፡

  እንደ አዲስ እየተደራጀ የሚገኘው የከተማው አመራርና የሰው ኃይል የከተማውን ነዋሪዎች ይሁንታ አግኝቶ ወደ ሥራ በመግባት፣ ለውጥ የሚያመጡ ሥራዎች ይከናወናሉ ብለዋል፡፡

  ምክትል ከንቲባው አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና መሆኗን ለማረጋገጥ የነዋሪዎቿን ፍላጎት ለማርካት ያስችላሉ ያሏቸውን ዋነኛ ችግሮች መለየታቸውን አስታውቀዋል፡፡

  የከተማው ነዋሪዎችን ያስቸግራሉ የተባሉ ችግሮችን ለመፍታት አዲሱን ካቢኔያቸውን በወጣቶች ያደራጁ መሆኑን፣ ካቢኔውም ከነዋሪዎች ጋር እየተመካከረ እንደሚሠራና ነዋሪዎችም ከአዲሱ አመራር ጋር በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...