Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፓርትበሪዮ ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ ያስመዘገበው ሌሊሳ ፈይሳ ወደ አገር ቤት እንዲመለስ ጥሪ...

  በሪዮ ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ ያስመዘገበው ሌሊሳ ፈይሳ ወደ አገር ቤት እንዲመለስ ጥሪ ተደረገለት

  ቀን:

  ከሁለት ዓመት በፊት ብራዚል ባስተናገደችው የሪዮ ኦሊምፒክ ላይ አትዮጵያ በማራቶን ወክሎ የብር ሜዳሊያ ያስገኘው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ነበር፡፡ አትሌቱ በወቅቱ በአገሪቱ የነበረውን ፖለቲካዊ ሁኔታ ለመቃወም እጆቹን አመሳቅሎ የተቃውሞ ምልክት በማሳየት በዚያው መቅረቱና ቆይቶም ወደ አሜሪካ ማቅናቱ አይዘነጋም፡፡

  ሆኖም በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ በሚታየው ለውጥ የተነሳ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ መደበኛ የአትሌቲክስ ሙያውን ማስኬድ ማከናወን ይችል ዘንድ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከወጣቶችና ስፖርትር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለአትሌት ፈይሳ ጥሪ እንዳደረጉለት አስታውቀዋል፡፡ አትሌቱ ወደ አገሩ ሲመለስ የተለመደውን ፍሬያማ ውጤት ሲያስመዘግብ ማየት የተቋማቱ ፍላጎት ከመሆኑ ባሻገርን የጀግና አትሌት አቀባበል እንደሚደረግለት ተገልጿል፡፡

  ተቋማቱ አትሌት ፈይሳ ወደ አገሩ በሚመለስበት ሁኔታ ላይ ለሳምንታት ሲመክሩ እንደቆዩ ተሰምቷል፡፡ ማክሰኞ ነሐሴ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሪፖርተር በላኩት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁትም፣ አትሌቱ የሪዮ ኦሊምፒክን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም አትሌቲክስ መድረኮች ላይ በመሳተፍ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ረገድ ስሙ ተጠቃሽ ነው፡፡ ይህንኑ አስተዋጽኦውን አብዝቶ ማበርከት ይችል ዘንድ፣ ወደ አገሩ በመመለስም የተለመደውን ውጤት እንዲያስመዘግብ የሦስቱም ተቋማት ማለትም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንዲሁም የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ፍላጎታቸው እንደሆነ በመግለጫው አመላክተዋል፡፡

  መግለጫው በብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር)ና በብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ፊርማ የተሠራጨ ነው፡፡ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2016 በተካሄደው የሪዮ ኦሊምፒክ አንድ የወርቅ፣ ሁለት የብርና አምስት የነሐስ በድምሩ ስምንት ሜዳሊያዎችን ማስመዝገቧ ይታወሳል፡፡ ከሁለቱ የብር ሜዳሊያዎች አንዱን ፈይሳ ሌሊሳ በማራቶን አስመዝግቧል፡፡

  አትሌት ፈይሳ በኢትዮጵያ ይታይ የነበረውን የፖለቲካ ችግር በመቃወም ሁለት እጆቹን በኤክስ (X) ምልክት አመሳቅሎ ውድድሩን መጨረሱ ይታወሳል፡፡ በሌሎች ውድድሮችም ይህንኑ ተቃውሞውን አሳይቷል፡፡ ይህ ምልክት በበርካታ የተቀውሞ ትዕይቶችም ሲዘወተር መቆየቱና ታዋቂነት ማትረፉ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ 

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...