Friday, August 19, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሊሰጥ ነው

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሊሰጥ ነው

  ቀን:

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ የአመራር ለውጥ አካሂዶ ሲጨርስ፣ ተሳስሮ የቆመውን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ለሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና በመስጠት በድጋሚ ሊያሸጋግር መሆኑ ታወቀ፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሥሪያ ቤቶች ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ተግባራዊ ባለማድረጋቸው ብቻ ሳይሆን፣ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች ብቃት ጥያቄ ውስጥ በመግባቱ ጭምር የአዲሱን ካቢኔ ትኩረት ስቧል፡፡

  በዚህ መሠረት የአመራር ለውጥ በማካሄድ ላይ የሚገኘው የከተማው አስተዳደር፣ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች ብቃት በድጋሚ እንደሚፈተሽና በሚመጥናቸው ቦታ እንዲሠሩ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

   የከተማውን ሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች ብቃት ለመለካት በቀድሞው ከንቲባ  ድሪባ ኩማ ይመራ የነበረው ካቢኔ፣ በሐሰተኛ ሰነድ የተቀጠሩ ሠራተኞች ራሳቸውን እንዲያጋልጡ ከዚያም ምሕረት እንደሚደረግላቸው ጊዜ ሰጥቶ ነበር፡፡

  ነገር ግን አለ በሚባለው ደረጃ በሐሰተኛ ሰነድ የተቀጠሩ ሠራተኞች ራሳቸውን ባለማጋለጣቸው፣ ዕቅዱ ብዙም አመርቂ ሳይሆን ቀርቷል ተብሏል፡፡

  ስለሆነም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኙ 105 ሺሕ ሠራተኞች እንዳስፈላጊነቱ የብቃት ማረጋገጫ ፈተናዎች እንደሚወስዱ፣ ፈተናውን የሚወስዱ ሠራተኞችም የሚመጥናቸው የሥራ መስክ እንደሚሰጣቸው ታውቋል፡፡

  አዲሱ ካቢኔ ይህን የወሰነው የከተማው አገልግሎት አሰጣጥ በመጓደሉና ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር እንዲያጋጥም አድርጓል በሚል ምክንያት ሲሆን፣ የተሳሰረውን የአገልግሎት አሰጣጥ በማቀላጠፍ የብቃት ማረጋገጫ ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል በሚል መሆኑ ተጠቁማል፡፡

  የከተማው አስተደደር ሥልጣን ከተረከበ በኋላ በማዕከል ለሚገኙ ቢሮዎችና በክፍለ ከተማ ለሚገኙ ጽሕፈት ቤቶች አመራሮችን ሾሟል፡፡

  የከተማው የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤትም እንዲሁ ለአሥሩም ክፍላተ ከተሞች አዳዲስ የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎችን ሾሟል፡፡

  በአመራር ለውጥ ብቻ የአዲስ አበባ ከተማን አገልግሎት አሰጣጥ ፍላጎት ማሟላት እንደማይቻል ግንዛቤ በመያዙ፣ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች ላይ ትኩረት ተደርጓል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...