Sunday, August 14, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የመጀመሪያው አፍሪካዊ የዓለም ጤና ድርጅት መሪ ለመሆን እንቅስቃሴ ጀመሩ

  ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የመጀመሪያው አፍሪካዊ የዓለም ጤና ድርጅት መሪ ለመሆን እንቅስቃሴ ጀመሩ

  ቀን:

  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት (ደብሊውኤችኦ) ዋና ዳይሬክተር ለመሆን ቅስቀሳ ማድረግ ጀምረዋል፡፡ ሚኒስትሩ አሁን ድርጅቱን እየመሩ ያሉት ማርጋሬት ቻን ሲወርዱ ለመተካት ፍላጎት እንዳላቸው ለዓለም አቀፉ ሚዲያ አሳውቀዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ድርጀቱ አፍሪካዊ መሪ ያልነበረው ሲሆን፣ ዶ/ር ቴድሮስ አፍሪካዊ መሪ መመረጥ እንዳለበት በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

  አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው፣ ዶ/ር ቴድሮስ ጄኔቫ ላይ ለጋዜጠኞች ‹‹ከአህጉራችን የምናፈልቃቸው አዳዲስ ሐሳቦችና የታዳጊ አገር አመለካከቶች ዓለም አቀፉን የጤና ሁኔታ ሊያሻሽሉ ይችላሉ፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በነበሩበት ሰባት ዓመታት የሕፃናት ሞትን ሁለት ሦስተኛ በመቀነስ እንዲሁም የኤችአይቪ/ኤድስ፣ ቲቢና ወባ ሥርጭትን በመቀነስ ውጤታማ እንደነበሩ አክለዋል፡፡

  ሚኒስትሩ እንደተናገሩት፣ እስካሁን ዓለም አቀፉ የጤና ሁኔታ እየታየ ያለው ከተቀረው ዓለም አንፃር ብቻ ነው፡፡ ቢሆንም አፍሪካና ሌሎችም ታዳጊ አገሮች በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ ጫና አለባቸው፡፡

  ‹‹በጣም አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ የኖረ ሰው ኃላፊነቱን የሚወስድበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው፡፡ እኔ አፍሪካ ውስጥ እንደመኖሬ በእነዚህ ከባድ ሁኔታዎች ኖሬያለሁ፤›› ብለዋል፡፡ የ51 ዓመቱ ሚኒስትር፣ የምርጫ ዘመቻቸው በአፍሪካ ኅብረት እየተደገፈ ይገኛል፡፡ የቀድሞው የፈረንሣይ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ፊሊፔ ደስቲ ብሬዚና የፓኪስታን የቀድሞ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሳኒያ ኒሽታር ከዓለም የጤና ድርጅት ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን ቅስቀሳ እያደረጉ ነው፡፡ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር የሚመረጠው በሚቀጥለው ዓመት ሰኔ 2009 ዓ.ም. መሆኑ ታውቋል፡፡ 

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...