Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፓርትፕሪሚየር ሊጉ በጥቅምት ይጀመራል ፌዴሬሽኑ በስፖርታዊ ጨዋነት ላይ አጠንክሮ እየሠራ መሆኑን...

  ፕሪሚየር ሊጉ በጥቅምት ይጀመራል ፌዴሬሽኑ በስፖርታዊ ጨዋነት ላይ አጠንክሮ እየሠራ መሆኑን አስታውቋል

  ቀን:

  ሦስት ነባር ቡድኖችን አውርዶ በምትካቸው አዳዲስ ቡድኖችን ያካተተው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጥቅምት 17 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡ ከስፖርታዊ ጨዋነት ጋር ተያይዞ ከመንግሥትና ከሚመለከታቸው አካላት በመቀናጀት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑንም ተናግሯል፡፡

  አሥራ ስድስት ቡድኖችን የሚያሳትፈው ፕሪሚየር ሊጉ ከተመሠረተ ከሁለት አሥርታት በላይ አስቆጥሯል፡፡ ይሁንና የሊጉ ተሳታፊ ቡድኖች በአገር ውስጥ ከሚያደርጉት የእርስ በርስ ትንቅንቅ የዘለለ በአህጉርም ሆነ በዓለም ደረጃ ያለው ውጤትና ጥንካሬ ይህ ነው ሊባል እንደማይችል የብዙዎች እምነት ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) በነሐሴ ወር ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት የብሔራዊ ቡድን ደረጃ 151ኛ መሆኑ ይታወሳል፡፡

  ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የ2011 ዓ.ም. መርሐ ግብር ይፋ ከማድረጉ ጎን ለጎን ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ማናቸውንም እግር ኳሳዊ እንቅስቃሴዎችን ተከትሎ ሲከሰቱ የነበሩ የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ ሊሠራ እንደሚገባው የሚናገሩ አሉ፡፡ እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ ከሆነ፣ በ2010 ዓ.ም. የውድድር ዓመት በተለይ በአማራና በትግራይ ክለቦች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እልባት ሊያበጅለት ይገባል፡፡

  የብሔራዊ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ገብረሥላሴ በበኩላቸው፣ “ፌዴሬሽኑና መንግሥት በጉዳዩ እየሠሩበት ነው፡፡ እንዴትና በምን ዓይነት አግባብ የሚለውን ዝርዝር መናገር ባያስፈልግም በስፖርታዊ ጨዋነት ላይ ሊወሰዱ የሚገባቸው የዲሲፕሊን መመሪያዎች ላይ ትኩረት ይደረጋል” ብለዋል፡፡

  ይህንኑ አስመልክቶ የሪፖርተር ምንጮች እንደሚናገሩት፣ ባለፉት ዓመታት በስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ሲፈጠሩ ለነበሩ የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል መንስዔዎቹ የፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን መመሪያ እንደሆነና በወቅቱ ትልቁ ቅጣት ተብሎ አጥፊዎች ላይ ሲወሰድ የነበረው የዲሲፕሊን ውሳኔ፣ በተለይ ለክለቦች ከገንዘብ ቅጣት የዘለለ አለመሆኑ፣ ከገንዘብ ቅጣቱ ጎን ለጎን ነጥብ መሰል የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አለማካተቱ ነው፡፡

  በዚሁ መሠረት ከእንግዲህ ግን በስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች አካባቢ ተመሳሳይ ጥፋት በመፈጸም እግር ኳሳዊ ክንውኑንም ሆነ ለዜጎች ማኅበራዊ ትስስር እንቅፋት በሚሆኑ ለማናቸውም ሁከቶች ምክንያት የሚሆን ክለብ ከነጥብ ቅጣት ባሻገር ከሚገኝበት ሊግ ዝቅ ብሎ የሚወዳደርበት የዲሲፕሊን ዕርምጃ የሚወሰድበት አጋጣሚ ሊኖር እንደሚችል ያስረዳሉ፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...