Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -

  አጋዘን

  ቀን:

  በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው አጋዘን በሥፍራው ከሚገኙ አጥቢ እንስሳት በግዙፍነቱ ይታወቃል፡፡ ከትከሻው እስከ እግሩ ስድስት ፊት የሚረዝም ሲሆን፣ ሴቷ ከ800 እስከ 1,300 ፓውንድ ትመዝናለች፡፡ ወንዱ ደግሞ ከ1,200 እስከ 1,600 ፓውንድ ይመዝናል፡፡

  አጋዘን ረዥም፣ ለስላሳና ፈዛዛ ቡናማና ጠቆር ያለ ፀጉር ሲኖረው፣ ጎፈሬያም በመሆኑም ለብርድ አይጋለጥም፡፡ የፊት እግሮቹ ከኋላው በተለየ ረዣዥም ናቸው፡፡ ይህም በደኖችና በቁጥቋጦዋማ ሥፍራዎች እንደልቡ እየዘለለና እየተንጠላጠለ እንዲመገብ ይረዳዋል፡፡

  ጭንቅላቱ፣ አፍንጫውና የላይኛው ከንፈሩ ረዘም ያሉም ናቸው፡፡ ጠንካራ የትከሻ ጡንቻ ሲኖረው ይህም ግርማ ሞገሱን ያጎላዋል፡፡ ወንዶቹ ጠፍጣፋና ከአራት እስከ አምስት ኢንች የሚረዝም ቀንድ አላቸው፡፡

  አጋዘኖች በተለይ ጠዋትና ማታ ቀልጣፋ ቢሆኑም የማየት አቅማቸው ደካማ ነው፡፡ በሌላ በኩል ጥሩ የመስማትና የማሽተት ችሎታ አላቸው፡፡ ቅጠላ ቅጠልና ቅርፊትም ይመገባሉ፡፡

  ሰላማዊ ከሚባሉ እንስሳት የሚመደቡ ሲሆን ከተተናኮሏቸው ግን ቁጡ ይሆናሉ፡፡ ሲል ናሽናል ጂኦግራፊ በድረ ገጹ አስፍሯል፡፡

  Previous articleፓን ኬክ
  Next articleየመስቀል አበባ
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...