Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሠራተኞች ድልድል ሊያካሂድ ነው

  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሠራተኞች ድልድል ሊያካሂድ ነው

  ቀን:

  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲስ ያዘጋጀው ተቋማዊ መዋቅር በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ መህመድ (ዶ/ር) በመፅደቁ፣ በድጋሚ የሠራተኞች ድልድል ሊያካሂድ ነው፡፡

  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ሰኞ መስከረም 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ለሚኒስቴሩ ማኔጅመንት ካውንስል በሰጡት መመርያ፣ ድልድሉ ከሌሎች መመዘኛዎች በተጨማሪ ብቃትና ክህሎት ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ የሠራተኛ ምደባውን ለማካሄድ የማኔጅመንት አባላትና የሠራተኛ ተወካዮች የያዘ ሰባት አባላት ያሉት ኮሚቴ ማቋቋሙን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

  ሚኒስቴሩ ለረጅም ዓመታት በሚሲዮኖች ሲያገለግሉ የቆዩ ከ90 በላይ ሠራተኞችን በመጥራቱ፣ ሠራተኞቹ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ አዲስ አበባ በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ሪፖርት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሠራተኞቹ እስከ 25 ዓመት ድረስ ያገለገሉ ናቸው ተብሏል፡፡

  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የሠራተኞች ድልድሉ በዋናው መሥሪያ ቤትና በ58 ሚሲዮኖች ይካሄዳል፡፡ ‹‹ድልድሉ የሚካሄደው አገራችን ከምትገኝበት ውስጣዊና ውጫዊ ሁኔታ በመነሳት ውጤታማ የውጭ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ ሥራ ለማከናወን፣ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የተሳለጠ ግንኙነት፣ የሰመረ የመረጃ ፍሰትና ወጥነት ያለው ቅንጅታዊ አሠራርና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር ለማድረግ ነው፤›› ሲሉ አቶ መለስ የሠራተኞች ምደባ ያስፈለገበትን ምክንያት ተናግረዋል፡፡

  ከዚህ በተጨማሪ 130 ዲፕሎማቶች አስፈላጊውን ሥልጠና ከወሰዱ በኋላ፣ በተለያዩ አገሮች በሚገኙ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች መመደባቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

  በሰው ኃይል ምደባ መሥፈርት መሠረት በሁሉም ሚሲዮኖች የሚገኙ ዲፕሎማቶች ዳግም ምደባ የሚያካሂድ መሆኑን፣ ይህም ለሚኒስቴሩ የሙያ ክህሎትን ያጠናክራል ተብሏል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...