Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ሥነ ፍጥረትወርቃማው ፍሬ

  ወርቃማው ፍሬ

  ቀን:

  ከፍራ ፍሬ ዘር ውስጥ ተወዳጅ የሆነ ነው አፕሪኮት፡፡ የአርመን ወርቃማ ፍሬ እየተባለም ይንቆለጳጰሳል፡፡ ለበርካታ ሺህ ዓመታት በእስያና በአውሮፓ ሲመረት የቆየው አፕሪኮት፣ አፕሪኮት መጀመሪያ የተገኘው በአርመን እንደሆነ አውሮፓውያን ያምኑ ስለነበር ፍሬውን የአርመን ፖም በማለት መጥራት ጀመሩ። በዎል ጄደብሊው ዶት ኦርግ ድረ ገጽ እንደተጻፈው፣ በዛሬው ጊዜ 50 የሚያህሉ የአፕሪኮት ዝርያዎች በአርመን ሲበቅሉ፣ የሚያፈሩትም ከሰኔ አጋማሽ እስከ ነሐሴ መጨረሻ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው። ከእሳተ ጎሞራ የተገኘውና በተለያዩ ማዕድናት የዳበረው የአርመን አፈር እንዲሁም ፀሐያማ የሆነው የአገሪቱ የአየር ንብረት በዚያ የሚበቅሉት አፕሪኮቶች ልዩ የሆነ ጣዕም እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች የአርመን አፕሪኮቶችን በዓለም ላይ ከሚገኙት በጣም ጣፋጭ አፕሪኮቶች ተርታ ይመድቧቸዋል። የተለመዱት የአፕሪኮት ዝርያዎች መጠናቸው ፕሪም ያህላል፤ ቀለማቸውም ፈዘዝ ያለ ወርቃማ ወይም ደማቅ ብርቱካንማ አሊያም በሁለቱ መካከል ሊሆን ይችላል። አፕሪኮት የላይኛው ሽፋኑ ለስላሳ ሲሆን ውስጡ ግን ጠንከር ያለ ከመሆኑም ሌላ ብዙ ውኃ የለውም፤ ጣዕሙም ጣፋጭ ወይም ጎምዘዝ ያለ ሊሆን ይችላል። አንዳንዶች፣ በጣም የተለመዱት የአፕሪኮት ዝርያዎች በኮክና በፕሪም መካከል የሚገኝ ጣዕም እንዳላቸው ይናገራሉ።

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...