Monday, August 15, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  ሠራተኛው ክቡር ሚኒስትሩ ቢሮ ገባ

  [የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ በጠዋት ቢሯቸው ገባች]

  • ደህና አደሩ ክቡር ሚኒስትር?
  • ደህና አደርሽ?
  • እንግዳ አለዎት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ማንንም አልቀጠርኩም እኮ፡፡
  • የመሥሪያ ቤታችን ሠራተኛ ሊያናግርዎት ፈልጎ ነው፡፡
  • በምን ጉዳይ?
  • አላወቅኩም ግን ሰሞኑን እርስዎን ፍለጋ ሲመላለስ ነበር፡፡
  • እኔ እኮ ቢዚ ነኝ፡፡
  • አውቃለሁ ግን ሲያለቅስብኝ ነው ወደ እርስዎ የመጣሁት፡፡
  • ለምንድነው የሚያለቅሰው?
  • ምክንያቱን መናገር የፈለገው ለእርስዎ ነው፡፡
  • ለምን?
  • እዚህ ያስመደቡኝ እሳቸው ናቸው እያለ ነው፡፡
  • አስገቢው፡፡

  [ሠራተኛው ክቡር ሚኒስትሩ ቢሮ ገባ]

  • ምን ሆነኃል?
  • ጉድ ሠሩኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እሺ አታልቅስ፡፡
  • ተጫወቱብኝ እኮ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምን ሆነህ ነው?
  • ምንድነው የሚውጠኝ ክቡር ሚኒስትር?
  • ንገረኝ እንጂ ምን ሆነሃል?
  • ይኼን ደብዳቤ ይመልከቱት፡፡
  • የምን ደብዳቤ ነው?
  • የቅነሳ ደብዳቤ፡፡
  • ምን አደረግህ?
  • እሱ እኮ ነው ግራ የሚገባው፡፡
  • ደብዳቤው ምክንያት የለውም?
  • መቀነሴን ብቻ ነው የሚናገረው፡፡
  • ምን አጥፍተሃል?
  • ጥፋቴንማ አውቀዋለሁ፡፡
  • ምንድነው ጥፋትህ?
  • ለኢሕአዴግ ታማኝ መሆኔ ነዋ፡፡
  • ምን እያልክ ነው?
  • ክቡር ሚኒስትር እኔን እዚህ ለምን እንዳመጡኝ በሚገባ ያውቁታል፡፡
  • በዋናነትማ ለጥርነፋ ነው ያመጣውህ፡፡
  • ታዲያ አንድ ለአምስት ቢሉ አንድ ለአንድ ስጠረነፍ ምን ይወጣልኛል?
  • በእሱስ አትታማም፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ይኼው የመሥሪያ ቤቱ መላ ሠራተኛ ከፓርቲያችን ጋር በፍቅር እንዲወድቅ ያደረግኩት እኔ አይደለሁ?
  • እ . . .
  • ከታች እስከ ላይ ሠራተኛው በሙሉ በፓርቲያችን እንዲታቀፍ አድርጌ ይኼው በአንድ ሐሳብ ተሳስረን ስንት ዓመታት አለፉ፡፡
  • አሁን ችግሩ ምንድነው?
  • ክቡር ሚኒስትር ይኼው መደመር ምናምን ብለው እኔን በጎን ቀነሱኝ፡፡
  • አታልቅስ በቃ፡፡
  • ይኼን ሁሉ ዓመት የለፋሁበት መና እኮ ነው የቀረው፡፡
  • እንዴ ከዚህ ከተባረርክ ሌላ ቦታ መቀጠር ትችላለህ እኮ?
  • እንዳይመስልዎት ክቡር ሚኒስትር፣ እኔን ማንም አይቀጥረኝም፡፡
  • ለምን አትቀጠርም?
  • ምክንያቱም የእኔ ሙያ እዚህ መሥሪያ ቤት ብቻ ነው የሚያገለግለው፡፡
  • ትምህርት ተምረሃል አይደል እንዴ?
  • እሱማ ተምሬያለሁ፡፡
  • ከተማርክ ታዲያ እንዴት ሌላ ቦታ መቀጠር ያቅትሃል?
  • ክቡር ሚኒስትር ትምህርቴ ለዚህ መሥሪያ ቤት ብቻ ነው የሚያገለግለው፡፡
  • ዲግሪ አለኝ ብለኸኛል አይደል እንዴ?
  • እሱማ አለኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ለመሆኑ ዲግሪህን በምንድነው የሠራኸው?
  • በአብዮታዊ ዴሞክራሲ!

  [ክቡር ሚኒስትሩ በቅርብ የሚያውቁትና በውጭ ካሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በአንዱ የሚሠራ ሰው ደወለላቸው]

  • ሰላም ነህ ወዳጄ?
  • ምን ሰላም አለ ክቡር ሚኒስትር?
  • ምን ሆንክ?
  • የአገሪቱ አልበቃ ብሏቸው ነው?
  • ምንድነው የምትለው?
  • ይኼው እኛም ጋ መጡ እኮ?
  • ማነው የመጣው?
  • ክቡር ሚኒስትር እዚህ ኤምባሲ ያስመደቡኝ እርስዎ አይደሉ እንዴ?
  • ስለማምንብህ እኮ ነው ያስመደብኩህ?
  • እኔስ መቼ አሳፈርኩዎት?
  • እንዲያውም አኩርተህኛል፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር እዚህ ያሉ ኢትዮጵያዊያን በጠቅላላ እኮ ነው ፓርቲያችንን እንዲደግፉት ያደረኩት፡፡
  • እንዴት  አድርገህ?
  • የቆንስላ አገልግሎት ለማግኘት ፓርቲያችንን መደገፍ ግዴታ አድርጌው ነዋ፡፡
  • እ. . .
  • በተለይ የፓርቲያችን ደጋፊዎች አገር ቤት ወሳኝ ቦታ እንዲያገኙ በማድረግ፣ እነሱ እንደ አርዓያ ተወስደው በርካታ ደጋፊዎችን መሳብ ችያለሁ፡፡
  • አውቃለሁ ወዳጄ፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር አብዮታዊ ዴሞክራሲን እንደ እኔ ያስተዋወቀው ማን አለ?
  • እሱን ነገር በደንብ ተረድተኸዋል ግን?
  • ክቡር ሚኒስትር እኔ እኮ ሳይገባኝ ራሱ አስተዋውቄው ውጤታማ ሆኛለሁ፡፡
  • እ. . .
  • ይኼው አገራችን 11 በመቶ እያደገች መሆኗን የዓለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀር መስክረዋል፡፡
  • ለእሱም መቼም የእኔ አስተዋጽኦ አለበት እንዳትለኝ?
  • በዋናነት እኔ አይደል እንዴ ኢንቨስተሮችን የምልከው?
  • እሱ ላይስ እውነት አለህ፡፡
  • በዚያ ላይ የፓርቲያችን ተቃዋሚዎች ድምጥማጣቸው እንዲጠፋ አድርጌያለሁ፡፡
  • ለሴራማ ማን ብሎህ? በመጀመርያስ ለሥራው ያስመለመለህ እሱ ችሎታህ እኮ ነው፡፡
  • ታዲያ ለእኔ ይኼ ይገባል?
  • ምን?
  • ወደ አገር ቤት እንድመለስ ደብዳቤ ተጻፈልኝ እኮ?
  • የምን ደብዳቤ?
  • በቃ ሥራህን ስለጨረስክ ወደ አገር ቤት ተመለስ ተብያለሁ፡፡
  • ወይ ጉድ፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር እንዲህ ዓይነት ደብዳቤ የደረሰኝ እኔ ብቻ እንዳልመስልዎት፡፡
  • ለሌላ ለማን ተሰጠ?
  • የቀድሞ ሥርዓት ደጋፊዎች ሁሉም ደርሷቸዋል፡፡
  • ምን?
  • ክቡር ሚኒስትር ከፅዳት እስከ ዲፕሎማት ወደ አገር ቤት እንድንመለስ ተነግሮናል፡፡
  • ወይ ጣጣ!!
  • አንድ ሳንቀር ሁላችንንም ሊተኩን ነው፡፡
  • ልትመለስ ወሰንክ ታዲያ?
  • እኔማ እዚህ አገር መንግሥትን ለመክሰስ እያስተባበርኩ ነው፡፡
  • በምን ልትከሰው?
  • በጅምላ ቅነሳ!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከሌላ ጡረታ ከወጣ ሚኒስትር ጋር እያወሩ ነው]

  • አካሄዳችን በጣም እያስፈራኝ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እንዴት?
  • ወጣትነታችን የተበላበት ሥርዓት እንዲሁ ሊያከትም?
  • ምን ታደርገዋለህ?
  • ይህ ፈጽሞ ሊሆን አይችልም፡፡
  • ምን ማድረግ እንችላለን?
  • አብዮታዊ ዴሞክራሲ ከሚበላና ከሚጠጣ ነገር ይበልጣል እኮ፡፡
  • እሱማ አውቃለሁ፡፡
  • አገራችን ትልቅ መሆኗን እኮ ያስመሰከርንበት ነው፡፡
  • እንዴት?
  • ያው መቼም ኢትዮጵያ ወራሪን መክታ በማሸነፍ የጥቁር ሕዝብ መሪ ናት፡፡
  • እሱማ ሁሌም የምንኮራበት ታሪካችን ነው፡፡
  • ይህንን ታሪክ አሁን ድረስ ያስመሰከርንበት እኮ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እ . . .
  • አዩ አብዮታዊ ዴሞክራሲን እኛው በራሳችን ፈብርከን ለዓለም በማስተዋወቅ፣ አሁንም የጥቁር ሕዝብ መመኪያ መሆናችንን ያስመሰከርንበት ነው፡፡
  • በዚህስ እስማማለሁ፡፡
  • አገራችንም ቢሆን ይህን ርዕዮተ ዓለምን በመከተል 11 በመቶ በማደግ ዓለምን ጉድ አሰኝታለች እኮ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እሱንማ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀሩ መስከረዋል፡፡
  • ታዲያ ኒዮሊበራሎቹ ሳይቀሩ ያመኑበትን ነገር እንዴት ነው ለመቀልበስ የሚሞከረው?
  • ግን ያው በጉባዔውም እንደተወሰነው በቀጣይ የምንከተለውን ርዕዮተ ዓለም ሊጠና ነው፡፡
  • የኒዮሊብራሎቹን አመለካከት ሊጭኑብን እኮ ነው፡፡
  • ለነገሩ በቀጣይ የምንከተለው ርዕዮተ ዓለም የእነሱ ይመስለኛል፡፡
  • ምን?
  • ሊብራል ዴሞክራሲ፡፡
  • ችግር የለውም ለእሱ መላ ማዘጋጀት ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምን ዓይነት መላ?
  • ለምሳሌ ሕገ መንግሥቱን ቢያዩ ሊብራል ነው ግን አፈጻጸሙ ነው ዋናው፡፡
  • አልገባኝም?
  • ርዕዮተ ዓለማችን ሊብራል ዴሞክራሲ ቢሆን እንኳን አፈጻጸሙን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ማድረግ ነው፡፡
  • እሱን ማድረግ እንዴት እንችላለን?
  • ለምን አንችልም ክቡር ሚኒስትር?
  • ደራሲው አልሰጠንማ፡፡
  • ምኑን?
  • ፓስወርዱን!

  [ክቡር ሚኒስትር ከቢሮ ሲወጡ ጸሐፊያቸው ዴስኳ ላይ ተኝታ አገኟት]

  • አንቺ ሰሞኑን ምን ሆነሻል?
  • ችግር ውስጥ ነኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምን ተፈጠረ?
  • ባሌ በጣም እያስቸገረኝ ነው፡፡
  • አሁንም የፍርድ ቤቱ ጉዳይ አላለቀም?
  • እሱማ አልቆ ነበር፡፡
  • ታዲያ ምን ተፈጠረ?
  • እሱ ያለ አንቺ መኖር አልችልም እያለ ነው፡፡
  • ፍርድ ቤት አፋቷችኋል አይደል እንዴ?
  • አዎ ግን አንድ ጊዜ ዕድል ሰጪ ብሎኝ ነበር፡፡
  • ታዲያ ፀባዩን ካስተካከለ ምን ቸገረሽ?
  • ለነገሩማ እኔም እወደው ነበር፡፡
  • እኮ ለምን ዕድል አትሰጪውም ነበር?
  • ቢስተካከልማ እኔ ምን ቸግሮኝ?
  • ሞክረሽው ነበር?
  • በቃ በሰላም እኖራለሁ ብሎ ቤት ተመልሶ ነበር፡፡
  • ታዲያ ምን ተፈጠረ?
  • ያው የቀድሞው ባህሪ አብሮት ተመለሰ፡፡
  • ታዲያ ምን አስጨነቀሽ?
  • እንዴት አይጨንቀኝ ክቡር ሚኒስትር?
  • የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ለምን አታስፈጽሚውም?
  • አልቻልኩማ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ለምን?
  • ምላሹ እንደ ፖለቲካ ድርጅቱ ድርቅ አለብኝ፡፡
  • ምን ብሎ?
  • አልፈታም!

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  ባንኮች እንዲዋሀዱ እስከ ማስገደድ ሊገባ እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ ጠቆመ

  በአሁኑ ወቅት የባንኮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ችግር የሚሆንና የውጭ...

  ለኬንያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሸጥበት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገበት

  በቅርቡ ሙሉ ለሙሉ ስምምነቱ የተጠናቀቀው የኢትዮጵያና የኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል...

  አዲስ አበባ እንዳይገቡ በተከለከሉ ዜጎች ጉዳይ የኦሮሚያና አማራ ክልሎች ተወያይተው ችግሩ እንዲፈታ አደረጉ

  ለሳምንታት በርካታ ቅሬታ ሲነሳበት የነበረውና ከአማራ ክልል በደብረ ብርሃን...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...

  ለኬንያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሸጥበት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገበት

  በቅርቡ ሙሉ ለሙሉ ስምምነቱ የተጠናቀቀው የኢትዮጵያና የኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሥራ አጥነት ችግሮችን የመፍታት ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም በዋና ጽሕፈት ቤቱ ሕንፃና ቢሮዎች ላይ ያደረገውን ዕድሳት መርቀው በመክፈት ጉብኝት እያደረጉ ነው]

  እጅግ ውብ ዕድሳት ያደረጋችሁት! በእውነቱ በጣም ድንቅ ነው፡፡ አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። በጣም ድንቅ ነው። ዕድሳቱን ያከናወነው ድርጅት ጥሩ ልምድ ያለው ይመስላል? ተቋራጩ ማን እንደሆነ አልነገርኩዎትም እንዴ? የትኛው ተቋራጭ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ በስንዴ የተሸፈኑ ሰፋፊ እርሻዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመገምገም ከስንዴ ምርት ድጋፍና ክትትል ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር እየመከሩ ነው] 

  ክቡር ሚኒስትር እንደነገርክዎት በሁሉም ስንዴ አብቃይ አካባቢዎቻችን ያሉ አርሶ አደሮች ጥሪያችንን ተቀብለው መሬታቸውን በኩታ ገጠም አርሰው በስንዴ ዘር ሸፍነዋል። በጣም ጥሩ ዜና ነው። በጣም እንጂ። የሚገርምዎት...

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሚመሩት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ አጀንዳ አድርጎ በያዘው ወቅታዊ የፀጥታና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት ቢጀመርም በስተመጨረሻ አጀንዳውን ስቶ ስለ መዋደድ እየተጨቃጨቀ...

  በዛሬው መደበኛው መድረካችን አጀንዳ የተለመደው የፀጥታና ደኅንነት ጉዳይ ይሆናል። ሌላ አጀንዳ የምታስይዙት አጀንዳ ከሌለ በቀር ማለቴ ነው። ክቡር ሚኒስትር... እሺ ...ቀጥል አመሰግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። መደበኛ አጀንዳው እንደተጠበቀ...