Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊበክረምቱ ከመደበኛ በላይ ዝናብ የጎርፍ አደጋ እንደሚያስከትል ተጠቆመ

  በክረምቱ ከመደበኛ በላይ ዝናብ የጎርፍ አደጋ እንደሚያስከትል ተጠቆመ

  ቀን:

  ከሰኔ 2008 ዓ.ም. እስከ መስከረም 2009 ዓ.ም. በሚዘልቀው የክረምት ወቅት የአገሪቱ ሰሜናዊ፣ ሰሜን ምዕራብና ሰሜን ምሥራቅ አካባቢዎች በአብዛኛው ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚዘንብና ይህም የጎርፍ አደጋ እንደሚያስከትል፣ ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

  በክረምት ወቅት የሚኖረውን የአየር ሁኔታ አዝማሚያ አስመልክቶ ብሔራዊ የሜቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ያጠናቀረውን መረጃ መሠረት በማድረግ፣ ኮሚሽኑ ሊከሰት የሚችለውን የጎርፍ አደጋ ሥጋት ለመቋቋም ያስችላል ያለውን ቅድሚያ ማስጠንቀቂያም ገልጿል፡፡

  በዚህም መሠረት በመጪው ክረምት የሚኖረው የጎርፍ ክስተት ሥጋት በበልጉ ወቅት ከነበረው የጎርፍ አደጋ ክስተት ጋር ተዳምሮ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመከላከልና ለመቀነስ፣ በጎርፍ አደጋ ሥጋት ውስጥ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች በሚመለከታቸው አካላት የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ መስጠት፣ ከባድ ዝናብ የማግኘት ዕድል ባላቸው ደጋማ አካባቢዎችና ከእነዚህ አካባቢ ሊመጣ በሚችል ጎርፍ ተጠቂ በሆኑ አካባቢዎች መካከል የመረጃ ልውውጥ ማጠናከር፣ በፌዴራልና በክልል የተቋቋሙ የጎርፍ መከላከል ግብረ ኃይሎችን ሥራ አጠናክሮ ማስቀጠል፣ የጎርፍ መከላከያዎችን ማጠናከር፣ ኅብረተሰቡን በተሻሉ ቦታዎች ለማስጠለል የሚያስችል ዕቅድ ማዘጋጀት፣ በጎርፍ አደጋው የሚከሰቱ የእንስሳት በሽታዎች ጉዳት እንዳያደርሱ መከታተልና መኖሩ እንደታወቀ ለቀጣይ ዕርምጃ ሳይዘገይ ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት ማድረግ፣ አስፈላጊ እንደሆነ ዘርዝሯል፡፡

  የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ግንቦት 11 ቀን 2008 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት በክረምቱ ወቅት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ለቅጽበታዊ የጎርፍ አደጋ ሊጋለጥ እንደሚችል ገልጸው ነበር፡፡ የኮሚሽኑ ሪፖርት የበልግ ዝናብ እየተጠናከረ ከመጣበት ከመጋቢት ወር 2008 ዓ.ም. የመጨረሻ ሳምንት አንስቶ ጎርፍ በ134 ሰዎች ላይ የሞት አደጋ ማስከተሉን ይጠቁማል፡፡ በተጨማሪም በ33,446 የቤት እንስሳት፣ በ48,448 ሔክታር ላይ በነበረ የሰብል ምርት፣ በ3,373 የመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት ማድረሱም ተገልጿል፡፡ 195,987 ሰዎች በጎርፍ አደጋው ምክንያት መፈናቀላቸውንም ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡     

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...