የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ)፣ ትናንት ጥቅምት 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የቀረበው ረቂቅ አዋጅን ካፀደቀ በኋላ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ያቀረቧቸውን አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመት አፅድቋል፡፡ ፓርላማው እስካሁን የነበሩትን 28 ሚኒስቴሮች ወደ 19 በማጠፍ በሙሉ ድምፅ ሲያፀድቅ፣ የፕላንና ልማት ኮሚሽን ሃያኛው የካቢኔ አባል እንዲሆንም ወስኗል፡፡ ፎቶዎቹ የፓርላማውን ውሎ ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡