Sunday, August 14, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየሰማያዊ ፓርቲ ልሳን ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ክስ ተመሠረተበት

  የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ክስ ተመሠረተበት

  ቀን:

  – ዓቃቤ ሕግ በቀድሞው የፓርቲው ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የቀረበው ክስ በሕጉ መሠረት የቀረበ ነው አለ

  የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን ‹‹ነገረ ኢትዮጵያ›› ዋና አዘጋጅ አቶ ጌታቸው ሽፈራው፣ የሽብር ድርጊት ወንጀል ክስ ግንቦት 26 ቀን 2006 ዓ.ም. ተመሠረተበት፡፡

  የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ግንቦት 10 ቀን 2008 ዓ.ም. የጻፈው ክስ እንደሚያስረዳው፣ አቶ ጌታቸው የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 7(1)ን ማለት፣ ማንኛውንም ሰው በሽብርተኛ ድርጅት ወይም የሽብርተኝነት ድርጊትን ለመፈጸም ሰው የመለመለ፣ አባል የሆነ፣ ሥልጠና የወሰደ ወይም በድርጅቱ በማንኛውም መልክ የተሳተፈ፣ ከአምስት እስከ አሥር ዓመታት እንደሚያስቀጣ የተደነገገውን ተላልፏል ብሏል፡፡

  በመሆኑም አቶ ጌታቸው፣ በግንቦት ሰባት ውስጥ በመሳተፍ ከድርጅቱ አመራሮች ጋር በድረ ገጽ፣ በፌስቡክና በስልክ ግንኙነት መፍጠሩን ክሱ ይገልጻል፡፡ ተከሳሽ ከድርጅቱ አመራሮች ጋር በፈጠረው ግንኙነት፣ የመረጃ ልውውጥ በማድረግ በውጭ አገር ከሚገኙ የድርጅቱ አመራሮች፣ ለሚጠቀሙበት ሚዲያዎች መረጃዎችን ማስተላለፉንና መሳተፉን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቁሟል፡፡

  ተከሳሹ በተለያዩ ጊዜያት ስለደብረ ማርቆስ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ረብሻና ፖሊስም እነሱን ስለማፈሱ፣ በማረሚያ ቤት ስለሚገኙት እነፍቅረ ማርያም መረጃ በመጠየቅና ሌሎችንም መረጃዎች ከተለያዩ ግለሰቦች እየተቀበለና ኢሕአዴግ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትንና ሌሎችንም እያሰረ መሆኑን፣ ለግንቦት ሰባት ያስተላልፍ እንደነበር በክሱ ተገልጿል፡፡ በአጠቃላይ አቶ ጌታቸው በተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ የድርጅቱ አባላት ጋር በመገናኘትና መረጃ በመሰብሰብ ሲያስተላልፍ የነበረ መሆኑን ዓቃቤ ሕግ ጠቅሶ፣ በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ በማንኛውም መልኩ መሳተፍ ወንጀል ክስ እንደቀረበበት ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው ክስ ያብራራል፡፡

  ክሱ ተነቦለት የክስ መቃወሚያ ካለው ለመጠባበቅ ለሰኔ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ ዓቃቤ ሕግ ሌላው ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው፣ የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ የመጀመርያ መቃወሚያ ላይ የመልስ መልስ ነው፡፡

  አቶ ዮናታን በቅድመ ክስ መቃወሚያው ላይ፣ ዓቃቤ ሕግ በክሱ የጠቀሰበትን የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር አንቀጽ 3 እና 4ን የተቃወመና የወንጀሉን ዝርዝር ሁኔታ እንደማያሟላ ገልጾ ውድቅ እንዲደረግለት የጠየቀ ቢሆንም፣ ዓቃቤ ሕግ ክሱን ያቀረበው ሕጉን ተከትሎና በተሟላ ሁኔታ መሆኑን ጠቅሶ፣ የአቶ ዮናታንን ተቃውሞ ውድቅ በማድረግ ወደ ክርክሩ እንዲገባ ብይን እንዲሰጥለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

  አቶ ዮናታን በኦሮሚያ የተደረገው ብጥብጥ የመልካም አስተዳደር እጦት ችግር እንጂ የኦነግ ተግባር አለመሆኑን በመጥቀስ ያቀረበውን ተቃውሞም ዓቃቤ ሕግ በቂ ምክንያት አለመሆኑን በመግለጽ በዝርዝር ተከራክሮ ወደ ቀጣይ ክርክር እንዲገባ ጠይቋል፡፡ የቀረበው ክስ ግልጽ አለመሆኑን አቶ ዮናታን በመቃወሚያው የጠቀሰና የተቃወመ ቢሆንም፣ ዓቃቤ ሕግ ክሱ ግልጽ መሆኑን በማስረዳት፣ ተቃውሞው ውድቅ ተደርጎ ወደ ዋናው ጉዳይ ገብቶ ለመከራከር እንዲችል ብይን እንዲሰጥለት ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ብይን ለመስጠት ለሰኔ 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጥሯል፡፡ 

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...