Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ሥነ ፍጥረትየሱማሌና የኑቢያ የዱር አህያ

  የሱማሌና የኑቢያ የዱር አህያ

  ቀን:

  የዱር አህያ ከአንገቱ በላይ ትልቅ የሆነ፣ ረጃጅም ጆሮዎች ያሉት፣ ግራጫ ወይም አመድማ ቀለም ያለው፣ ደረቱ፣ ሆዱ፣ እግሮቹና ቂጡ፣ አፉ አካባቢና በዓይኖቹ ዙሪያ ነጭ የሆነ እንስሳ ነው፡፡ አጭር፣ ቡናማ ጋማ፣ አንዳንዴም ከትከሻው በኩል የሚወርዱ መስመሮች ያሉት፣መኻከለኛ ርዝመትና ጫፉ ባለጥቁር ጎፈር የሆነ ጅራት ያለው፣ ከፍታው ወደ አንድ ሜትር ከሩብ፣ ርዝመቱ ወደ ሁለት ሜትር፣ ክብደቱ በአማካይ 275 ኪ.ግ የሚሆን የአህያ አስተኔ ዘመድ አባል ነው፡፡ ሁለት ንዑስ ብቸኛ ዝርያዎች አሉት፡፡ አንዱ የሱማሌ የዱር አህያ ሲሆን፣ የሚገኘው በምሥራቅ ኢትዮጵያና በምሥራቅ ሶማሊያ ብቻ ነው፡፡ ሌላኛው፣ የኑቢያ የዱር አህያ ነው፡፡ የሚገኘውም ከሱዳን ጀምሮ ቀይ ባሕርን ድንበር አድርጎ እስከ የኢትዮጵያው ያንዱጉዲ ራሳ ፓርክ ድረስ ነው፡፡ በተለይ የሱማሌ የዱር አህያ፣ ዝቅ ብለው እግሮቹ ላይ የሚዞሩ ግልጽ የሆነ መስመሮች አሉት፡፡ ቤታዊው አህያ የመጣው የኑብያውን የዱር አህያ ከመሰለው ነው ይላሉ፡፡

  • ሰለሞን ይርጋ (ዶ/ር) ‹‹አጥቢዎች›› (2000)
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...