Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፓርትበአዲስ አበባ ስታዲየም የአየር ብክለት መለኪያ መሣሪያ ተተከለ

  በአዲስ አበባ ስታዲየም የአየር ብክለት መለኪያ መሣሪያ ተተከለ

  ቀን:

  የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የአየር ብክለት መለኪያ መሣሪያ ከአዲስ አበባ ስታዲየም አጠገብ በሚገኘው የአትሌቲክስ ማሟሟቂያ ሜዳ መተከሉ ፌዴሬሽኑ አስታወቀ፡፡ ዓርብ ጥቅምት 23 ቀን 2011 ዓ.ም. የተባበሩት መንግሥታትና የአይኤኤኤፍ ተወካዮች በተገኙበት መሣሪያው ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር ተነግሯል፡፡

  እንደ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሆነ የአየር ብክለት መለኪያ መሣሪያው በዓለም አቀፉ ተቋም አማካይነት ሲተከል፣ በአፍሪካ የመጀመርያ ሲሆን፣ በዓለም ደግሞ ከፈረንሳይ ሞናኮና ከአርጀንቲና ቦነስ አይረስ ቀጥሎ ሦስተኛው ነው፡፡

  የአየር ብክለት መሣሪያ በአሜሪካ ኤምባሲ፣ ብስራተ ገብርኤል አካባቢ በሚገኘው ኢንተርናሽናል ኮሚዩኒቲ ስኩል፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታልና በኢትዮጵያ ሜቲዮሮሎጂ ግቢ ውስጥ ተተክሎ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በእነዚህ መሣሪያዎች መሠረትም የአዲስ አበባ የአየር ብክለት ደረጃ፣ በአማካይ መካከለኛ የብክለት ደረጃ መያዙ ይታወቃል፡፡

  ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲሆን፣ በአሜሪካ ስታንዳርድ ከሆነ ግን ከፍተኛ የብክለት ደረጃ ላይ እንደሚመደብ የአሜሪካ የአካባቢና የአየር ብክለት ባለሙያዎች በአንድ ወቅት ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቆይታ ማስታወቃቸው አይዘነጋም፡፡

  የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ አዲስ አበባና አካባቢዋ በተለይም በአሁኑ ወቅት የአየሯ ሁኔታ ለአትሌቶች ቀርቶ ለመደበኛው ነዋሪ እንኳን እጅግ አስቸጋሪ መሆኑን ተናግሮ፣ አትሌቶች ልምምዳቸውን ከአዲስ አበባ ውጪ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ሲናገር ተደምጧል፡፡ በአዲስ አበባ ስታዲየም አጠገብ በሚገኘው የአትሌቲክስ ማሟሟቂያ ሜዳ የተተከለው ይህ የአየር ብክለት መለኪያ መሣሪያ በዓለም አቀፉ ተቋም ደረጃ ዕውቅና እንዲያገኝ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት  ኃይሌ ጥረት ሳይታከልበት እንዳልቀረ ይነገራል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...