Monday, August 8, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊበኢንሳ ሶፍትዌር ምክንያት የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ ማውጫ ቀን ተራዘመ

  በኢንሳ ሶፍትዌር ምክንያት የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ ማውጫ ቀን ተራዘመ

  ቀን:

  ሥልጣን ከያዘበት ከሐምሌ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በበርካታ ሥራዎች የተጠመደው አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ፣ በኢትዮጵያ መረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ ማውጫ ሶፍትዌር ላይ ችግር መኖሩን በማስተዋሉ፣ የቤቶችን ዕጣ ማውጫ ቀነ ገደብ ለማራዘም መገደዱን አስታወቀ፡፡

  በምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከቀድሞው አስተዳደር በጅምር የተረከባቸውን የ132,700 ቤቶች ግንባታ በማስቀጠል፣ ከእነዚህ ውስጥ 42,300 ያህል የ20/80 እና የ40/60 ቤቶችን ዓርብ ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም. በዕጣ ለማስተላለፍ ዕቅድ ይዞ ነበር፡፡

  ቤቶቹ የውኃ፣ የፍሳሽ፣ የኤሌክትሪክና የመንገድ መሠረተ ልማቶች ሙሉ በሙሉ ባይሟሉሏቸውም፣ ግንባታቸው ግን ከ80 እስከ 90 በመቶ የደረሰ በመሆኑ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ ታቅዶ ነበር፡፡

  ነገር ግን በዘጠነኛው፣ በአሥረኛውና በ11ኛው ዙር የመኖሪያ ቤቶች ዕጣ ወጥቶበት የነበረው በኢንሳ የተሠራው ሶፍትዌር የሕጋዊነት ጥያቄ በማስነሳቱና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የተገባው ውል ስህተት በመሆኑ፣ የዕጣ ማውጫ ጊዜው እንዲራዘም መደረጉ ተገልጿል፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊዎች አቶ ዘሪሁን ዓምደ ማርያም (ኢንጂነር) እና አቶ ጀማል ሃጂ ጥቅምት 28 ቀን 2011 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

  ኃላፊዎቹ እንደገለጹት፣ ኢንሳ የሠራው ሶፍትዌር ሦስት ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ የመጀመርያው የአመልካቾችና የቤቶች ምዝገባ፣ ሁለተኛው ሎተሪ ማውጣት፣ ሦስተኛው ደግሞ የኮንትራት ውል ናቸው፡፡

  ‹‹የአመልካቾች ምዝገባ አሠራር ክፍተት አለበት፡፡ ዳታው በማዕከል አይተዳደርም፡፡ አሥሩም ክፍላተ ከተሞች የተጠቃሚዎችንና የቤቶቹን ዳታ ኦዲት ሊያደርጉት ይችላሉ፤›› ሲሉ አቶ ዘሪሁን በሶፍትዌሩ ላይ የተስተዋሉ ችግሮችን ገልጸዋል፡፡

  እሳቸው ጨምረው እንደገለጹት፣ መረጃዎች በሆነ ሰው እጅ ተቀምጠው የሚገኙ በመሆናቸው፣ የማይገባውን ሰው ያላግባብ ተጠቃሚ ሊያደርግ ይችላል፡፡

  ‹‹የሕጋዊነትና የፍትሐዊነት ጥያቄ ይነሳል፡፡ ሶፍትዌሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እጅ መሆን አለበት፡፡ አስተዳደሩ ሶፍትዌሩን በመረከብ የተወሰኑ ማሻሻያዎች እየተደረጉለት ነው፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

  ሶፍትዌሩ የቆየው ቤት የማስተዳደር ሥልጣን ባልተሰጠው አካል በመሆኑ፣ አስተዳደሩ ሶፍትዌሩን መረከብ ይኖርበታል ብለዋል፡፡

  ቤቶቹ በተባለላቸው የጊዜ ገደብ እንዳይተላለፉ እንቅፋት ሆኗል የተባለው ሌላው ችግር የታየበት ጉዳይ፣ የቤቶቹ ግንባታ ዋነኛ ፋይናንሰር በሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ነው፡፡

  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለይ የ40/60 ቤቶች ግንባታቸው ሲጠናቀቅ ተረክቦ ለተጠቃሚዎች ያስተላልፍ ነበር፡፡ ኃላፊዎቹ እንደገለጹት፣ ቤቶቹን ማስተላለፍም ሆነ የማስተዳደር ሥልጣን የከተማ አስተዳደሩ ነው፡፡

  ‹‹ከባንኩ ጋር የነበሩንን ውሎች አፍርሰናል፡፡ በአሁኑ ወቅት መመርያዎችን በማሻሻል ላይ እንገኛለን፤›› በማለት፣ ቀጣዩ 13ኛ ዙር የቤቶች ዕጣ የሚከተለውን አዲስ አሠራር አብራርተዋል፡፡  

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በዓለም ጂኦ ፖለቲካ መድረክ የኢትዮጵያ ተፈላጊነት

  የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሦስት የአፍሪካ አገሮች...

  በአገር ጉዳይ አንዱ ባለቤት ሌላው ባይተዋር መሆኑ ይብቃ!

  ኢትዮጵያ የታፈረችና የተከበረች አፍሪካዊት አገር ናት፡፡ ለመላው የዓለም ጥቁር...

  ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2015 የሒሳብ ዓመት ተቀማጭ ገንዘቡን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ለማሳደግ እንደሚሠራ አስታወቀ

  በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በተለያዩ ክንውኖቹ ከዕቅድ በላይ ውጤት ማስመዝገቡን...