Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየአፋር ገዥ ፓርቲ ነባር አመራሮቹን እንዲተካ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበለትን ሐሳብ መቀበሉ ተገለጸ

  የአፋር ገዥ ፓርቲ ነባር አመራሮቹን እንዲተካ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበለትን ሐሳብ መቀበሉ ተገለጸ

  ቀን:

  የአፋር ክልላዊ መንግሥት ገዥ ፓርቲ የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ነባር አመራሮቹን በአዲስ አመራሮች እንዲተካና በአገር አቀፍ ደረጃ ከሚካሄደው የፖለቲካ ለውጥ እንቅስቃሴ ጋር የሚጣጣም ፖለቲካዊ ለውጥ በክልሉ እንዲጀመር፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የቀረበለትን ምክረ ሐሳብ መቀበሉ ተገለጸ።

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና የአፋር ብሔራዊ ዲሞክራሲዊ ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አመራሮችን ወደ አዲስ አበባ በመጥራት ዓርብ ኅዳር 7 ቀን 2011 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተው ነበር፡፡ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ዓብይ (ዶ/ር) አስቀምጠውት በነበረው ምክረ ሐሳብ መሠረት፣ የክልሉ መንግሥትና መሪ ፓርቲ አመራሮች  በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቅጥር ግቢ እስከ ሰኞ ኅዳር 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ሲወያዩ መቆየታቸው ታውቋል።

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ኅዳር 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ከእነዚሁ የፖለቲካ አመራሮች ጋር ዳግም ተገናኝተው መወያየታቸውን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቃል አቀባይ ቢሮ በዕለቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

  በዚህ ውይይትም በአገር አቀፍ ደረጃ በመካሄድ ላይ ያለውን ለውጥ በክልል ደረጃ እንዴት መካሄድ እንዳለበት ትኩረት ሰጥተው መወያየታቸውን፣ ለውጡንም የበለጠ ለማሳካት እንዲቻል ነባር የፓርቲ አመራሮች በአዲስ አመራሮች እንዲተኩ በመነጋገር ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን መግለጫው ያትታል፡፡

  ከዚህም በተጨማሪ የክልሉን ሰላምና ፀጥታ በበለጠ በማጠናከር ሕዝቡ የልማት ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ እንዲቻል ሁሉም አመራሮች በጋር ለመሥራት፣ የክልሉን ወጣቶችን ይበልጥ በማሳተፍ የሕዝቡን የልማትና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ለመመለስ በመስማማት፣ አመራሮቹ ቃል መግባታቸውን መግለጫው ጠቁሟል፡፡

  ጠቅላይ ሚኒስትሩ የክልሉን ፖለቲካዊ ጉዳዮች በተመለከተ የክልሉን የመንግሥትና የፓርቲ አመራሮች ወደ አዲስ አበባ በመጥራት ለማወያየት የተገደዱት፣ በአመራሮቹ መካከል አለመግባባትና አለመተማመን በመከሰቱ ነው ተብሏል፡፡ አለመግባባቱ በክልሉ ግጭትና የፖለቲካ አለመረጋጋት በማስከተሉ ምክንያት መሆኑንም የኢሕአዴግ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የአጋር ድርጅቶችና የሲቪል ማኅበራት አስተባባሪ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ለመገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።

  የክልሉ ፕሬዚዳንት ሐጂ ሥዩም አወል በበኩላቸው፣ በድርጀቱ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ ከፍተኛ አመራሮች ሥልጣን ለቀው ወጣቶች እንደሚተኩና እሳቸውም ሥልጣን ለማስረከብ ፈቃደኛ መሆናቸውን ለመገናኛ ብዙኃን ሰኞ ኅዳር 10 ቀን 2011 ዓ.ም. በይፋ ተናግረዋል። ይኼንኑ ዕውን ለማድረግም ኅዳር 23 ቀን 2011 ዓ.ም. የአብዴፓ ድርጅታዊ ጉባዔ እንዲካሄድ ከውሳኔ ላይ መደረሱ ታውቋል።

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...