Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  ክቡር ሚኒስትሩ ከአንድ አክቲቪስት ነኝ ባይ ጋር ተገናኝተው እያወሩ ነው

  [ክቡር ሚኒስትሩ በቅርቡ ከታሰሩ ወዳጆቻቸው መካከል አንዱን ሊጠይቁት እስር ቤት ይሄዳሉ]

  • ሰላም ወዳጄ፡፡
  • ከየት ተገኙ ክቡር ሚኒስትር?
  • ተው እንጂ ወዳጄ?
  • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
  • አንተን የመሰለ ወዳጄ እስር ቤት ገብቶ ሳልጠይቅ የምከርም ይመስልሃል?
  • ምን ይታወቃል ብለው ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • በየሳምንቱ እየመጣሁ ብጠይቅህ ደስ ይለኛል፡፡
  • ለነገሩ የእርስዎም ፋይል ከተገላበጠ በየሳምንቱ መምጣት አይጠብቅብዎትም፡፡
  • ምን እያልክ ነው?
  • ያው እኔን ይቀላቀሉኛል ብዬ ነዋ፡፡
  • እኔ እኮ እንዳንተ አልዝረከረክም፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር በሕግ ከለላ ሥር ስላለሁ ወንጀለኛ መሆኔ እስኪረጋገጥብኝ ድረስ ንፁህ መሆኔን እንዳይዘነጉ፡፡
  • እየተዋወቅን?
  • ክቡር ሚኒስትር እርስዎስ ቢሆን ስለተደመሩ እንጂ ሳይዝረከረኩ ቀርተው ነው?
  • እኔም እስክከሰስ ንፁህ ነኝ፡፡
  • ስለዚህ ሁለታችንም ያለንበት ቦታ ተለያየ እንጂ ያው ነን፡፡
  • እኔ ግን አንድ ጥያቄ አለኝ?
  • ምን ክቡር ሚኒስትር?
  • ሁላችሁም አቋም ይዛችሁ ነው እንዴ እስር ቤት የገባችሁት?
  • የምን አቋም ነው?
  • ጠበቃ መቅጠር ስለማንችል መንግሥት ያቁሙልን የምትሉት ነዋ?
  • ክቡር ሚኒስትር የእኔን ፀባይ መቼም ያውቁታል፡፡
  • ማለት?
  • እኔ ባገኘሁት አጋጣሚ አንጠፍጥፌ ነው የምጠቀመው፡፡
  • እ. . .
  • ከእርስዎ ጋር ስንገናኝ ያዘዝኩን ምግብና መጠጥ መቼ አስተርፌ አውቃለሁ?
  • ለነገሩ ለዚህም ያበቃህ ይኸው ፀባይህ ነው፡፡
  • የትኛው ፀባዬ?
  • ስትበላ ጥርግርግ አድርገህ ነው እኮ፡፡
  • ምን ችግር አለው?
  • እኔ ስበላ በመጠኑ ነው የምበላው፣ አንተ ግን በሬ በአንድ ጉርሻ መዋጥ ነው የምትፈልገው፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር የፈለገ ነገር ቢመጣ እኔ ነፃ ወጪ ነኝ፡፡
  • በምን ሒሳብ ነው ነፃ የምትወጣው?
  • ምንም ሀብት በስሜ የለም፡፡
  • ምን?
  • ያለኝን ነገር ሁሉ አሸሽቼ እዚህ ምንም የለኝም፡፡
  • ይኼ ነፃ የሚያወጣ ይመስልሃል?
  • ማስረጃ ከሌለ ምን ይመጣብኛል?
  • ስማ በሚዲያ እንደሰማነው በርካታ መረጃዎች አሉ፡፡
  • ለማንኛውም እኔ እዚሁ ተመችቶኛል፡፡
  • የአገራችንን እስር ቤት እኮ እናውቀዋለን፡፡
  • ምን ሆነ እስር ቤቱ?
  • ስንት ቶርቸርና ግፍ የሚደረግበት አይደል እንዴ?
  • እንግዲህ በድሮ ሥርዓት እንደዚያ ሊሆን ይችላል፡፡
  • አሁንስ?
  • አሁንማ ከገባሁ እንኳን ዝንብ አርፎብኝ አያውቅም፡፡
  • እንዴት?
  • እንዲያውም ውጭ ያተረፍኩት ድካም፣ ሴራ፣ ክፋት ምናምን ነው፡፡
  • ምን እያልክ ነው?
  • እዚህ መጽሐፌን እያነበብኩ ተመችቶኛል፡፡
  • ምን ትቀልዳለህ?
  • ስነግርዎት ለእኔ ጥሩ ቫኬሽን ነው፡፡
  • እ. . .
  • እኔ የምመክርዎት አንድ ነገር ነው፡፡
  • ምን?
  • ቦታ ሳይሞላ. . .
  • እ. . .
  • እጅዎን ይስጡ!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከአንድ አክቲቪስት ነኝ ባይ ጋር ተገናኝተው እያወሩ ነው]

  • ክቡር ሚኒስትር አገሪቱ ላይ ምን እየተካሄደ ነው?
  • ምን  ተካሄደ?
  • እናንተ እያላችሁ አገር እንደዚህ መቀለጃ ትሁን?
  • የምን ቀልድ ነው?
  • ለዚህች አገር ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን የከሰከሱ ሰዎች ሲቀለድባቸው እንዴት ዝም ትላላችሁ?
  • ምንድነው የምታወራው?
  • ለአገሪቱ ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉ ሰዎች ግፍና በደል እየተፈጸመባቸው ነው፡፡
  • ኧረ ሰውዬ ተረጋጋ፡፡
  • ይኼንንማ እስከ መጨረሻው የምታገለው ጉዳይ ነው፡፡
  • ምን ልታደርግ?
  • በተገኘው አጋጣሚ ኡኡታዬን አሰማለሁ፡፡
  • ተልባ ቢንጫጫ በአንድ ሙቀጫ አሉ፡፡
  • እንዳይመስልዎት ክቡር ሚኒስትር በተለያዩ ሙቀጫዎች ነው የምንጫጫው፡፡
  • አልገባኝም?
  • ሲያስፈልግ በሶሻል ሚዲያ፣ ሲያስፈልግ ደግሞ በሜንስትሪሙ መንጫጫቴን እቀጥላለሁ፡፡
  • ሌላስ?
  • ካልቻልኩ ደግሞ በማይክራፎን መንገድ ላይ ኡኡታዬን አሰማለሁ፡፡
  • ውሻ በበላበት ይጮኸል ነው ነገሩ?
  • እንዳይሳሳቱ ክቡር ሚኒስትር?
  • እንዴት?
  • እኔ የምጮኸው እንዲያውም ስላልበላ ነው፡፡
  • አልገባኝም?
  • በደህና ጊዜ በልቼ ቢሆን ኖሮ አሁን አልንጫጫም ነበር፡፡
  • ብሶብሃል ልበል?
  • ክቡር ሚኒስትር ልክ ተራዬ ሊደርስ ሲል እኮ ነው የተያዙት፡፡
  • የምን ተራ?
  • እኔ የምበላበት ተራ ነዋ፡፡
  • ሰው ዓይን አውጥቷል ልበል?
  • ክቡር ሚኒስትር የቀድሞው ሥርዓት ተመልሶ እኔ ልብላና ከዚያ እንደፈለገው ይሁን፡፡
  • ወይ  ጉድ ከእኛም የባሰ ሰው አለ ማለት ነው?
  • እናንተማ በልታችሁ ጠግባችሁ ነው፣ እኛ እኮ የድርሻችንን አልወሰድንም፡፡
  • እ. . .
  • እናንተ ሆዳችሁ ሞልቶ ነው፣ እኛ በባዶ ሆዳችን ነው የምንጮኸው፡፡
  • አንተ ጥሩ ትምህርት አለህ፣ ለምንድነው ሠርተህ የማትበላው?
  • እንደዚህ እያላችሁ ሸወዳችሁን፣ ልክ የእኛ መብያ ተራ ሲደርስ መታጠፍማ አያዋጣም፡፡
  • በነገራችን ላይ ብዙ ሰዎች እየታዘቡህ ነው፡፡
  • ለምንድነው የሚታዘቡኝ?
  • አንተ አክቲቪስት ነኝ ካልክ ለሕዝብ ነው እንጂ መታገል ያለብህ እንዴት ግፍ ለሠሩ ሰዎች ትከራከራለህ?
  • እንዳይሳሳቱ ክቡር ሚኒስትር?
  • እንዴት?
  • They are innocent until proven guilty.
  • እሱን እንኳን ተወው፡፡
  • እርስዎ አንድ ላይ ታግለው እነዚህን ሰዎች ወንጀለኛ ማድረግ ነበረብዎት?
  • መቼም አንተ መረጃ አለህ ብዬ ስለማስብ ሰዎቹ የሠሩትን አልነግርህም፡፡
  • ቢሆንም ሁሉንም ነገር ያደረጉት ለአገር ጥቅም ነው እንጂ ለራሳቸው ሲሉ አይደለም፡፡
  • አውሮፕላንና መርከብ የገዙት ለአገር ጥቅም ነው?
  • እነሱ አውሮፕላንና መርከብ ባይገዙ አገሪቱ 11 በመቶ ታድግ ነበር?
  • ለማንኛውም ለጤና ያድርግልህ፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር በዚህ ወቅት ከእርስዎ የምንፈልገው ድጋፍ እንዲያደርጉልኝ ብቻ ነው፡፡
  • የምን ድጋፍ?
  • ለአክቲቪዝም ሥራዬ መጠነኛ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉልኝ ነዋ፡፡
  • እኔ ደመወዜ አነስተኛ ስለሆነ ልደግፍህ አልችልም፡፡
  • አዲሱ ስታይል እየተጠቀሙብኝ ነው?
  • ለማንኛውም ይኼ አካሄድህ ስለማያዋጣ ብትተወው ይሻልሃል፡፡
  • በፍፁም አልተወውም፡፡
  • ያለበለዚያማ መቀላቀልህ አይቀርም፡፡
  • ከማን ጋር ነው የምቀላቀለው?
  • ከገቡት ጋር!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከአማካሪያቸው ጋር እያወሩ ነው]

  • ክቡር ሚኒስትር ሰሙ?
  • ምኑን?
  • ገቢ ተደረጉ እኮ?
  • ማን ነው ገቢ የተደረገው?
  • ሁለት መቶ የሚሆኑ ሰዎች ታሰሩ፡፡
  • ከየት ነው የሰማኸው ደግሞ?
  • እሱ ብቻ እንዳይመስልዎት 100 ቢሊዮን ብርም ተመዝብሯል፡፡
  • ከየት ነው የተመዘበረው?
  • ከአገርና ከሕዝብ ነዋ፡፡
  • ስማ ይኼን ወሬ ለመልቀም ሥራህን ትተህ ከተማዋን ስትዞር ነበር?
  • ክቡር ሚኒስትር እርስዎ እኮ በድንጋይ ዘመን ነው የሚኖሩት፡፡
  • ምን እያልክ ነው?
  • እኛ እኮ መረጃ እጃችን ላይ ነው ያለው፡፡
  • እጃችን ላይ ነው ስትል ደኅንነት ቢሮ ገባህ እንዴ?
  • መረጃው ሁሉ ስልኬ ላይ ነው፡፡
  • የደወለልህ ሰው ነበር?
  • ክቡር ሚኒስትር አሁን የጀነሬሽን ጋፕ እንዳለን ተጋለጠ፡፡
  • የምን የጀነሬሽን ጋፕ ነው?
  • ሶሻል ሚዲያ ላይ ያለዎትን ፕረዘንስ ይጨምሩ ያልኩዎት እኮ ለዚህ ነው፡፡
  • መረጃውን ከፌስቡክ ነው የሰማሁት እንዳትለኝ?
  • ምን ችግር አለው?
  • የተጻፈ ሁሉ እውነት ነው ያለህ ማነው?
  • ክቡር ሚኒስትር ጽሑፉን እኮ ብዙ ሰዎች ሼር አድርገውታል፡፡
  • ስለዚህ እውነት ነው ማለት ነው?
  • እውነት ባይሆንማ ሰዎች አይቀባበሉትም ነበር፡፡
  • ለመሆኑ ፌስቡክ ላይ በርካታ የሐሰት አድራሻ ያላቸው ሰዎች የተለያዩ ጽሑፎች እንደሚጽፉ አታውቅም?
  • እሱማ አውቃለሁ፡፡
  • ብታውቅማ ያልተጣራ መረጃ ዝም ብለህ ባላናፈስክ ነበር፡፡
  • መረጃ አይናቅም ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እንዳንተ ግን የሥራ ፈቶችን መረጃ ማናፈስ በኋላ ትርፉ ኪሳራ ነው፡፡
  • ለምን ክቡር ሚኒስትር?
  • እንደዚህ ዓይነት የሐሰት ዘገባ የሚያሠራጩትን ካበረታታህ አገር ላይኖረን ይችላል፡፡
  • እ. . .
  • ለማንኛውም እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን መከተል አቁም፡፡
  •  ለምን?
  • ምክንያቱም እነሱ አንድ ነገር ስለሆኑ፡፡
  • ምን?
  • ፀረ አገር!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከአንድ ሀቀኛ ሚኒስትር ጋር እያወሩ ነው]

  • ክቡር ሚኒስትር ሰሞኑን ጠፍተዋል፡፡
  • ያው አለቃችን ኮንትራት አስፈርመው አይደል ሥራ ያስጀመሩን፡፡
  • ልክ ነው፡፡
  • ስለዚህ በኮንትራቱ መሠረት ሥራችንን ለማጠናቀቅ ደፈ ቀና እያልን ነው፡፡
  • ሰሞኑን የተከሰተውን ነገር መቼም ሚዲያ ላይ እየተከታተሉ ነው?
  • ያልጠበቅነው ነገር እኮ ነው እየሆነ ያለው አይነኬዎቹ እኮ ነው የተነኩት፡፡
  • ከዚህም በላይ የሚነኩ ይኖራሉ፡፡
  • በዚህ አካሄድማ የግሉ ዘርፍ ቢፈተሽ ራሱ በርካታ ችግሮች እንዳሉ እርግጠኛ ነኝ፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ስኳር ብለው አሸዋ፣ ስንዴ ብለው ኮረት ሲገባልን ነበር እኮ?
  • በጣም ነው የሚገርመው፣ ገና ከዚህም የባሰ ግፍ እንሰማለን ማለት ነው?
  • ክቡር ሚኒስትር ገና ብዙ ጉዶች ይወጣሉ፡፡
  • ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ቁጭ ብለን መነጋገር አለብን፡፡
  • በየቱ ጉዳይ?
  • በዚህ ከቀጠልን የአገሪቱ እስር ቤቶች አይበቁንም፡፡
  • ምን እያሉ ነው?
  • አሁን እንደገባኝ ይህ ጉዳይ የእያንዳንዳችንን ቤት ሊያንኳኳ ይችላል፡፡
  • ሕዝብ የበደለማ ለፍርድ መቅረብ አለበት፡፡
  • አሁን ችግሩ የማረሚያ ቤት እጥረት ነው፡፡
  • ምን ይደረግ ታዲያ?
  • እኔ የመፍትሔ ሐሳብ አለኝ፡፡
  • ምን ዓይነት?
  • የመጀመርያው እስር ቤት መከራየት ነው፡፡
  • ከየት ነው የምንከራየው?
  • ከጎረቤት አገሮች?
  • እሺ፡፡
  • ሁለተኛው ደግሞ ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎችንና የተለያዩ መጋዘኖችን ወደ ማረሚያ ቤት መቀየር ነው፡፡
  • እሺ፡፡
  • ሦስተኛውና እኔ የማምንበት ነው፡፡
  • ምንድነው?
  • የኢንዱስትሪ ፓርክ ሞዴልን መከተል አለብን ባይ ነኝ፡፡
  • ትንሽ ቢያብራሩት?
  • አዳዲስ ፓርኮችን መገንባት አለብን፡፡
  • የምን ፓርክ?
  • የታራሚዎች ፓርክ!

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  አዲስ አበባና ኦሮሚያ ወሰን ለማካለል ተስማሙ

  ኮዬ ፈጬ፣ ቱሉዲምቱ፣ ጀሞ ቁጥር 2 ወደ ኦሮሚያ ለቡ፣ ፉሪና...

  ባንኮች እንዲዋሀዱ እስከ ማስገደድ ሊገባ እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ ጠቆመ

  በአሁኑ ወቅት የባንኮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ችግር የሚሆንና የውጭ...

  በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት መካከል የተጀመረው የድርድር ሒደት አሳታፊ እንዲሆን ተጠየቀ

  የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት፣  በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...

  ሰበበኞች!

  ዛሬ የምንጓዘው ከሜክሲኮ ወደ አየር ጤና ነው፡፡ ዛሬም፣ ነገም...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [ክቡር ሚኒስትሩ ወዳጃቸው ከሆነ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ጋር ሻይ ቡና እያሉ በኬንያ ስለተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየተጫወቱ ነው]

  ኬንያ በዚህ ደረጃ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ታደርጋለች ብዬ አላሰብኩም ነበር ክቡር ሚኒስትር። አዎ። ጥሩ ዝግጅት አድርገውበታል። ቢሆንም... ቢሆንም ምን ክቡር ሚኒስትር?  እባክህ ክቡር ሚኒስትር የምትለውን ነገር አቁም። ወዳጅ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሥራ አጥነት ችግሮችን የመፍታት ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም በዋና ጽሕፈት ቤቱ ሕንፃና ቢሮዎች ላይ ያደረገውን ዕድሳት መርቀው በመክፈት ጉብኝት እያደረጉ ነው]

  እጅግ ውብ ዕድሳት ያደረጋችሁት! በእውነቱ በጣም ድንቅ ነው፡፡ አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። በጣም ድንቅ ነው። ዕድሳቱን ያከናወነው ድርጅት ጥሩ ልምድ ያለው ይመስላል? ተቋራጩ ማን እንደሆነ አልነገርኩዎትም እንዴ? የትኛው ተቋራጭ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ በስንዴ የተሸፈኑ ሰፋፊ እርሻዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመገምገም ከስንዴ ምርት ድጋፍና ክትትል ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር እየመከሩ ነው] 

  ክቡር ሚኒስትር እንደነገርክዎት በሁሉም ስንዴ አብቃይ አካባቢዎቻችን ያሉ አርሶ አደሮች ጥሪያችንን ተቀብለው መሬታቸውን በኩታ ገጠም አርሰው በስንዴ ዘር ሸፍነዋል። በጣም ጥሩ ዜና ነው። በጣም እንጂ። የሚገርምዎት...