Sunday, August 14, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናበሞያሌ የተቀሰቀሰው ግጭት እየተባባሰ ነው

  በሞያሌ የተቀሰቀሰው ግጭት እየተባባሰ ነው

  ቀን:

  ሰሞኑን በሞያሌ ከተማ ለዘመናት አብረው በኖሩት የኦሮሞና የሶማሌ ተወላጆች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ከመረጋጋት ይልቅ እየባሰበት መምጣቱን፣ የሁለቱም ተወላጆች ወደ አጎራባች ኬንያ መሰደድ መቀጠላቸውን ሪፖርተር ያነጋገራቸው ምንጮች ገለጹ።

  ባለፈው ሳምንት በሁለቱ ወገኖች ማለትም በቦረና ኦሮሞና ገሪ ተብሎ በሚጠራው የሶማሌ ጎሳ መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ከኦሮሞ በኩል 13 ሰዎች ሲገደሉ፣ ከገሪ ደግሞ 21 ሰዎች መገደላቸውን የሁለቱም ክልሎች መንግሥታት በተናጠል ባወጡት መግለጫ አስታውቀው ነበር።

  በርካታ ሰላማዊ ነዋሪዎች የተቀሰቀሰውን ግጭት በመሸሽ ባለፈው ሳምንት ወደ ኬንያ የጀመሩት ስደት፣ በከፍተኛ ቁጥር ተባብሶ መቀጠሉን እማኞች ለሪፖርተር ገልጸዋል። በአካባቢው የተቀሰቀሰው ግጭት የአስተዳደር ወሰን ጥያቄን መነሻ እንዳደረገ ቢገለጽም፣ ባለፋት ሁለት ቀናት ከሁለቱም ወገኖች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች የተሳተፋበትና ከባድ የጦር መሣሪያ ጭምር ጥቅም ላይ የዋለበት ግጭት በመካሄድ ላይ መሆኑን ምንጮች አረጋግጠዋል።

  በሞያሌ ከተማም ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ሕንፃዎችና የመንግሥት ተቋማት በጥቃት ወደ ፍርስራሽ እየተቀየሩ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ኬንያ ለመሸሽ እንዳልቻሉ፣ በዚህም ምክንያት መኖሪያ ቤታቸውን በመልቀቅ በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ለመጠለል መገደዳቸውን ገልጸዋል።

  የመከላከያ ሠራዊቱ በአሁኑ ወቅት እያደረገ ያለው ጥረት የጎሳ መሪዎችን በማነጋገር ችግሩን ለመፍታት እንደሆነ የሚገልጹት የአካባቢው የዓይን እማኞች፣ ከዚህ በተጨማሪ ግጭቱን ለማስቆም ጣልቃ መግባት እንዳለበት ይጠይቃሉ፡፡

   የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባወጣው መግለጫ ግጭቱን የቀሰቀሱት የሁለቱን ክልሎች መረጋጋት የማይሹ ኃይሎች እንደሆኑ በመግለጽ፣ ችግሩን ከመሠረቱ ለመቅረፍ መንግሥት በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን አስታውቆ ነበር።

   ሪፖርተር ያነጋገራቸው ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ ከፍተኛ የፌዴራል መንግሥት ኃላፊ፣ በሞያሌ የተቀሰቀሰው ግጭት በሁለቱ ወገኖች መካከል ሲነሳ የቆየው የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ እንዳልሆነ አስረድተዋል።

  ኃላፊው ትክክለኛ ምክንያቱን በግልጽ ለማስረዳት ባይፈልጉም ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ግጭት መሆኑን ግን ጠቁመዋል።

   የብሔራዊ ፀጥታና ደኅንነት ምክር ቤት በሞያሌ የተቀሰቀሰውን ግጭት አስመልክቶ በቅርቡ እንደሚሰበሰብና ውሳኔ እንደሚያሳልፍም ኃላፊው ጠቁመዋል።

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...