Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፓርትደንብና ሥርዓት የናፈቃቸው ማዘውተሪያዎች ተማፅኖ

  ደንብና ሥርዓት የናፈቃቸው ማዘውተሪያዎች ተማፅኖ

  ቀን:

  የኢትዮጵያ እግር ኳስ የሙያ መተያያ መድረክነቱ እየቀረና እየተረሳ፣ የአመፅና የብጥብጥ ሜዳ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ዘርፉን የሚያስተዳድሩ መንግሥታዊም ሆነ የስፖርቱ አመራሮች ከላይ እስከ ታች ችግሩን እያስታመሙ ከጊዜያዊ የማስታገሻ መፍትሔ የዘለለ፣ ትርጉም ያለውና በሥርዓተ ሕግ የሚመራ የመፍትሔ ዕርምጃ ሲወስዱ አልታዩም፡፡

  በዚህም ሳቢያ ሄድ መለስ እያለ የሚያገረሽበት የሜዳ ውስጥ ነውጥ የሚገታው ጠፍቷል፡፡ በአዲሱ የመንግሥት አስተዳደር ከሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ጀምሮ በተዋረድ የሚገኙ  መንግሥታዊ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ከስፖርቱ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግንኙነት ያላቸው ሙያተኞች፣ የክለብ አመራሮችና ደጋፊዎች በጉዳዩ መወያየት ብቻ ሳይሆን መፍትሔ ያስቀመጡባቸው መድረኮች በርካታ ናቸው፡፡ እነዚህ ውይይቶችና ስምምነቶች ታዲያ ወደ ማዘውተሪያዎች መውረድና ተግባራዊ መሆን ስለምን ተሳናቸው? የሚል ጥያቄ ማስነሳታቸው አልቀረም፡፡

  ፖለቲካዊ ኃይሉም ከመድረክ ዲስኩር ያለፈ ተግባራዊ ለውጥ ማሳየት ተስኖት በማዘውተሪያዎች የክለብ ድጋፍን ሽፋን ያደረገ የተመልካቾች ግብግብ መቋጫ ማጣቱ እያነጋገረ ይገኛል፡፡ ከመንግሥት ቋት ሚሊዮኖችን እየጠየቀ ያለው እግር ኳስ የስፖርት ቤተሰቡ በሚፈልገው ልክ ማደግ ሲገባው፣ እየወረደ በሚገኝበት በዚህ ወቅት በተለይ ከስፖርታዊ ጨዋነት ጋር ተያይዞ መድረኮች ላይ የሚነገረውና ሜዳ ውስጥ በተግባር የሚታየው ለየቅል ሆኖ እየታየ ነው፡፡ የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደሎች ዓይነትና ይዘታቸው ይለያይ ይሆናል እንጂ እግር ኳሱ ባደገባቸው ማለትም በአውሮፓ፣ በደቡብ አሜሪካና በሌሎችም አገሮች እንዳለ በርካታ ማሳያዎችን መመልከት ይቻላል፡፡ ‹‹በእንቅርት ላይ. . . ›› እንዲሉ አድሮ ቁልቁል የሆነው  እግር ኳስ፣ የባሰ ወደ መቀመቅ ከመውረዱ በፊት ሰላማዊ የውድድር መድረክ ሊመቻችለት እንደሚገባ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፌዴሬሽን አመራሮች ይናገራሉ፡፡

  ‹‹እግር ኳሱ በአንድ ራስ ሁለት ምላስ ያላቸው የክለብ አመራሮችና ደጋፊዎች ችግር ውስጥ ነው፡፡ ይህ ሲባል የተቋሙ ወቅታዊ አቋም በሁሉ ረገድ እንከን የሌለበት ነው ማለት አይደለም፣ ክፍተቶች አሉ፤›› የሚሉት አመራሮቹ ተወደደም ተጠላ እግር ኳሱ ከአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት ለዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ደንብና መመርያዎች ተገዥ ሊሆን እንደሚገባ መተማመን ላይ መድረስ እንደሚያስፈልግ ያምናሉ፡፡

  ሜዳ ውስጥ ችግሮች በሚፈጠሩበት ወቅት ፕሮግራም የወጣላቸው ጨዋታዎች የሚቋረጡበትና እንዲቀጥሉ የሚደረግበት የመመርያ ማዕቀፎች በግልጽ መቀመጣቸውን የሚያክሉት የፌዴሬሽኑ አመራሮች፣ ባለፈው እሑድ ታኅሣሥ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የቅዱስ ጊዮርጊስና የሐዋሳ ከተማ  ቡድኖች በአዲስ አበባ ስታዲየም ሊደረግ ታቅዶ በደጋፊዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት እንዲቋረጥ መደረጉ ውጥረቱን ከማርገብ አኳያ ተገቢ ቢሆንም በሕግ አግባብ ግን ትክክል እንዳልሆነ ጭምር ያምናሉ፡፡

  ምክንያቱም በቀጣይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይሁን በክልል ሜዳዎች ጨዋታው ከመጀመሩ አስቀድሞ ደጋፊዎች ግጭት ቢፈጥሩና እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስና ሐዋሳ ከተማ ሁሉ ግጭቱ በፀጥታ ኃይል በቁጥጥር ሥር እንዲውል ቢደረግ፣ አንደኛው ቡድን አልጫወትም ቢል የፌዴሬሽኑ ውሳኔ ምን ሊሆን ነው? የሚል ሌላ መዘዝ ይዞ እንደማይመጣ ማረጋገጫ እንደሌለ ሥጋታቸውን ይናገራሉ፡፡ በዕለቱ ሊደረግ የነበረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በማግሥቱ ሰኞ ታኅሣሥ 8 በዝግ ስታዲየም ተከናውኖ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

  ሌሎችም ሪፖርተር ያነጋገራቸው የስፖርቱ ቤተሰቦች፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በማዘውተሪያዎች የሚታየውን ሥርዓት አልበኝነት መከላከል ይቻል ዘንድ በመፍትሔነት የሚያነሱት፣ የተጋጣሚ ቡድን ደጋፊዎችን ቁጥር መለየትና ጠንካራ የፀጥታ ኃይል መመደብ ብቻ ሳይሆን ችግር ፈጣሪ ደጋፊዎችን በአግባቡ መለየት የሚችል ካሜራ እንዲጠቀም ጭምር ይመክራሉ፡፡ ይህ የማይሆን ለሆነ ደግሞ ሥጋት የሚስተዋልባቸውን ጨዋታዎች በዝግ ስታዲየም ማከናወን የግድ እንደሚለው ይናገራሉ፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...