Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ለግምገማ አዳማ ይከትማሉ

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ለግምገማ አዳማ ይከትማሉ

  ቀን:

  ተንሰራፍቶ የቆየውን ሕገወጥነት በማስተካከል ሥራ ተጠምደው የቆዩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ ባለፉት አምስት ወራት ያከናወኑዋቸውን ሥራዎች ለመገምገም ከረቡዕ ታኅሳስ 17 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ አዳማ ከተማ ይከትማሉ፡፡

  የከተማ አስተዳደሩ በማዕከል፣ በክፍላተ ከተማና በወረዳ የሚገኙ ከአንድ ሺሕ በላይ መካከለኛና ከፍተኛ አመራሮች ጋር በሚቀጥሉት አራት ቀናት ግምገማዊ ሥልጠና ያካሂዳል ተብሏል፡፡

  የግምገማዊ የሥልጠናው ዓላማ አዲሱ የከተማው አስተዳደር ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ እስከ ኅዳር 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ ያከናወናቸውን የለውጥ ሥራዎች አፈጻጸም፣ ያጋጠሙ መልካም ዕድሎችና መሻሻል ያለባቸውን ጎኖች በመገምገም፣ ለውጥ የሚያመጡ ሥራዎች ላይ አቋም ለመያዝ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

  ከዚህ በተጨማሪ በቀጣዮቹ ሰባት ወራት ትኩረት ተሰጥቷቸው ለሚከናወኑ ሥራዎች መመርያ እንደሚሰጥ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

  በምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የሚመራው የከተማው አስተዳደር፣ በከተማው ነዋሪዎች ተቀባይነት ያገኘባቸውን በርካታ ሥራዎች በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

  ከእነዚህ ውስጥ ለዓመታት ታጥረው የቆዩ ቦታዎችን ማስመለሱ፣ በሕገወጥ መንገድ የተያዙ የመንግሥት ቤቶች ማስመለሱና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች መስጠቱ፣ የንፁህ ውኃና የትራንስፖርት አቅርቦት ለማሻሻል የወሰዳቸው ዕርምጃዎች፣ አረንጓዴና የሕዝብ መናፈሻ ቦታዎች ለማስፋፋት የያዘው አቋም፣ በፖለቲካና በማኅበራዊ ጉዳዮች ከኅብረተሰቡ ጋር ለመወያየት ቅርብ መሆኑ ተጠቃሾች ናቸው፡፡

  ምንጮች እንደገለጹት፣ ከአዳማው ግምገማዊ ሥልጠና በኋላ በተለይ በሚቀጥሉት ሰባት ወራት የመሠረተ ልማት አቅርቦት ለማሻሻል፣ የከተማውን ገቢ ለማሻሻል፣ አገልግሎት አሰጣጡንና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡   

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...