Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት...

  የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት በአማካሪነት ተመደቡ

  ቀን:

  የሕወሓትና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ፣ በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት በአማካሪነት መመደባቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ።

  አቶ አስመላሽ ከኢሕአዴግና ከሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነታቸው በተጨማሪ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር በመሆን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሲሠሩ እንደነበር ይታወሳል።

  በቅርቡ ተካሂዶ ከነበረው የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በኋላ አቶ አስመላሽ በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት በአማካሪነት እንዲያገለግሉ መመደባቸውን፣ በአሁኑ ወቅትም ሥራ መጀመራቸውን እንደሚያውቁ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል።

  አቶ አስመላሽ ላለፉት በርካታ ዓመታት በፓርላማ በመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትርነት ሲሠሩ የነበረ ቢሆንም፣ ካለፉት አራት በላይ ወራት ይኼንን ኃላፊነታቸውን ሲወጡ አልነበሩም።

  ምንጮች እንደገለጹት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከጥቂት ሳምንታት በፊት ለፓርላማው በላከው ደብዳቤ፣ የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ሆነው ሲሠሩ የነበሩትን አቶ አስመላሽ ከኃላፊነት ማንሳቱን አስታውቋል።

  በማከልም በአቶ አስመላሽ ምትክ የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር እስኪሾም ድረስ፣ ቀደም ሲል በፓርላማው የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሆነው የተሾሙት የኦዴፓ አባል አቶ ጫላ ለሚ የመንግሥት ተጠሪ ኃላፊነትን በውክልና እንዲሠሩ መወሰኑን ምንጮች ተናግረዋል። አቶ አስመላሽ በመንግሥት ተጠሪነት ኃላፊነታቸው ምክንያት በፓርላማው ቅጥር ግቢ ውስጥ ይጠቀሙበት የነበረውን ቢሮ አስረክበው እንደወጡ፣ ከፓርላማው ሕንፃ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ቢሮ መያዛቸውን ለማወቅ ተችሏል።

  ከወራት በፊት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳን የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርገው ለማሾም ተገኝተው የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ነባር የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትሮችን መልሰው እንዳይሾሙባቸው አንዳንድ የፓርላማው አባላት ጠይቀው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

  ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ተነስቶላቸው ለነበረው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ መንግሥት የመንግሥትን ጥቅም ሊያስከብሩ ይችላሉ ብሎ ያመነባቸውን እንደሚመድብ ተናግረው ነበር።

   በአሁኑ ወቅት በፓርላማው የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ሆኖ የተሾመ ባይኖርም፣ ላለፉት በርካታ ዓመታት የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሲሠሩ የነበሩ አራት የፓርላማ አባላት ተነስተው በምትካቸው ሌሎች ተሹመዋል።

  ኦዴፓን በመወከል የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አቶ ጌታቸው በዳኔ ተነስተው በአቶ ጫላ ለሚ ሲተኩ፣ ደኢሕዴንን በመወከል የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ በነበሩት አቶ አማኑኤል አብርሃም ምትክ ደግሞ አቶ መስፍን ቸርነት (አምባሳደር) ተተክተዋል።

  ሕወሓትን በመወከል የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ በነበሩት አቶ አፅብሃ አረጋዊ ምትክ አቶ ገብረ እግዚአብሔር አርዓያ የተተኩ ሲሆን፣ አዴፓን በመወከል የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን ለረዥም ዓመታት ሲያገለግሉ በነበሩት አቶ መለስ ጥላሁን ምትክ ደግሞ አቶ ጫኔ ሽመካ መተካታቸውን ለማወቅ ተችሏል። ላለፉት በርከት ያሉ ወራት ሕወሓትን የሚወክል ሰው በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ውስጥ አለመኖሩን የጠቆሙት ምንጮች፣ የአቶ አስመላሽ በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት መመደብ ይኼንን ክፍተት እንደሚሞላ ጠቁመዋል።

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...