Wednesday, August 10, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልቀጣዩን የከተሞች ፎረም አሶሳ ታዘጋጃለች

  ቀጣዩን የከተሞች ፎረም አሶሳ ታዘጋጃለች

  ቀን:

  ዘጠነኛውን የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ እንድታስተናግድ በጅግጅጋ ከተማ በተደረገው ውድድር ተመርጣለች። ከሰባት ክልሎች ከቀረቡ 12 ከተሞች መካከል በተደረገ ውድድር አሶሳ ብልጫውን ያገኘችው ከመጨረሻ ዙር ተወዳዳሪዎች ወላይታ ሶዶና ጅማ ከተሞችን በመቅደም ነው። አሶሳ ለ2013 ዓ.ም. አዘጋጅነት  ለመመረጥ የቻለችው የቀረበውን የውድድር መስፈርት በማሟላቷ ነው፡፡ መስፈርቱም የከተማ በቂ የሰነድ ዝግጅት፣ ፍትሐዊነት፣ ወቅታዊ ሁኔታ፣ ታዳሚዎችን የማስተናገድ አቅምና መስህብ እንዲሁም የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎች መሆናቸው ተመልክቷል። ባለፈው ሐሙስ የካቲት 14 ቀን 2011 ዓ.ም. በተጠናቀቀውና ‹‹መደመር ለኢትዮጵያ ከተሞች ብልፅግና›› በሚል መሪ ቃል በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተካሄደው ስምንተኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም በተሻለ ዝግጅት ሐዋሳ፣ ሻሸመኔና አዳማ ከተሞችአንደኛ እስከ ሦስተኛ ወጥተዋል። ፎቶዎቹ (በግራ) አሶሳ ቀጣዩን የከተሞች ፎረም እንድታዘጋጅ የተሰጣትን የዕውቅና ሰርትፍኬትና በዘንድሮው የከተሞች ፎረም ብልጫ ያገኘችው ሐዋሳ ከተማ አሸናፊነቷ ሲበሰር ተወካዮቿ ደስታቸውን ሲገልጹ ያሳያሉ፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ‹‹በድርቅ ምክንያት የሚቀርብልን የዕርዳታ ጥሪ ተበራክቷል›› አቶ አብዲሳ መሐመድ፣ በኦሮሚያ የኢንተርናሽናል ሪስኪዩ ኮሚቴ ሥራ አስኪያጅ

  ኢንተርናሽናል ሪስኪዩ ኮሚቴ (አይአርሲ) በኢትዮጵያ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ድንገተኛ...

  የመጻሕፍት ቡፌ

   ሕፃናትና ወጣቶች የትምህርት ዕረፍታቸውን ከትምህርት አጋዥ በተጨማሪ ልብ ወለድ፣...

  የእናት ጡት ወተት የመጀመርያው የሕይወት ክትባት

  የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በዓለም ላይ ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶችን አስከትሏል፡፡ ከዚህ...

  ቻይናና ታይዋን የተወዛገቡበት የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት

  የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን ለመጎብኘት...