Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልየቅድመ ሰው ዘሯ ሉሲን ለኢትዮጵያ ሰላምና ፍቅር

  የቅድመ ሰው ዘሯ ሉሲን ለኢትዮጵያ ሰላምና ፍቅር

  ቀን:

  ‹‹ኢትዮጵያዊነት የከበረ ማንነታችን መገለጫ፣ የጀግንነታችን ከፍታና የአንድነታችን ምልክት ነው፤ የሚያምርብን ፍቅርና አብሮነታችን ነው ኢትዮጵያውያን የተሳሰሩና በታሪክ የተቆራኙ ናቸው…››

  ይህን ኃይለ ቃል ያስተጋቡት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ‹‹ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር›› የተሰኘው ፕሮጀክትን የካቲት 14 ቀን 2011 ዓ.ም. የሉሲን ቅሪተ አካል ወደ አፋር ስትሸኝ በፓርላማቸው ካሰሙት ዲስኩር የተወሰደ ነው፡፡

   የሉሲ ቅሪተ አካል ከሌሎች አገራዊ ባህላዊ ቅርሶች ጋር በመሆን  በዘጠኙ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ በመዘዋወር ለየኅብረተሰቡ በማስጎብኘት ሰላም ፍቅርና አንድነትን ለመስበክ የታለመ ፕሮጀክት ነው፡፡

  አፈ ጉባዔ ታገሰ፣ በዲስኩራቸው፣ ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያውያን የአንድ ‹‹የሉሲ ልጆች›› መሆናቸውን በማሳወቅ በአገሪቱ ሰላምና ፍቅር እንዲነግሥ የማድረግ ዓላማን ያነገበ ነው ብለዋል።

  ይሁን እንጂ በተጓዳኝም በታሪክና በሃይማኖት ተቀባይነት የሌላቸው የአገሪቱን ሰላም የሚፈታተኑ አመለካከቶችን ለማስወገድ ጉዞው ዓይነተኛ መሣሪያ እንደሆነም አፈ ጉባዔው ሳይናገሩ አላለፉም።

  ‹‹አንድነታችንን የሚፈታተኑትን ዘረኝነትና አግላይነት ተግባራት ልንከላከል ይገባል›› ሲሉም አስረግጠው ተናግረዋል።

  ‹‹ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር›› ባለፈው ሐሙስ ወደ አፋር ክልል የተጓዘች ሲሆን በቀጣይም ወደ ሌሎች ክልሎች እንደሚደረግና በየክልሎቹ አምስት ቀናት ቆይታ እንደሚኖራት ታውቋል።

  ‹‹ሉሲ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንን ከዓለም ጋር የምታስተሳስር ገመድ ነች፤›› ያሉት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሒሩት ካሰው (ዶ/ር) የፕሮጀክቱ ትልም ‹‹ኢትዮጵያውያን ተነጣጥለን ሥራ የማንሠራ ተነጣጥለን መኖር የማንችል መሆናችንንም ለማሳየት ነው፤›› ብለዋል፡፡ ሚኒስትሯ በሉሲ ጉዞ ኢትዮጵያውያንን እርስ በርስ እንዳይለያዩ ያስተሳሰሯቸው ባህላዊ እሴትና ቅርሶችም ሉሲን አጅበው ይጓዛሉ ሲሉ በፓርላማው ገልጸዋል።

  ሉሲ ከአገር ውስጥ ጉዞዋ በተጨማሪ በኤርትራ፣ ጂቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳንና ሱዳን፣ ኬንያና ኡጋንዳ የሚካሄድ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

  ጉዞ ሉሲን በጋራ ያዘጋጁት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የሰላም ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ናቸው።

  የሉሲ 44ኛ ዓመት

  ከአርባ አራት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ በለውጥ ማዕበል ውስጥ ነበረች፡፡ የየካቲት 1966 .. ሕዝባዊ ንቅናቄ ተከትሎ የጦር ኃይሎች፣ የክብር ዘበኛ፣ የፖሊስ ሠራዊትና የብሔራዊ ጦር አስተባባሪ ኮሚቴ ዘውዳዊ ሥርዓቱን መስከረም 2 ቀን 1967 .. ገረሰሰ፡፡ ሥልጣኑንም ሲጨብጥ የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ተብሎ ተሰየመ፡፡ ታሪክ መመዝገቡም ቀጠለ፡፡ በዚያው ዓመት ቅዳሜ ኅዳር 14 ቀን በእስር ላይ የነበሩትን የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ከፍተኛ የሲቪልና ወታደራዊ ሹማምንትን በመግደል ዓለምን አስደነገጠ፡፡

  መርዶው በተነገረ በማግስቱ (ኅዳር 15 ቀን 1967 ዓ.ም.) ዓለምን ያስደመመ፣ የሰው ልጆችን አመጣጥ በተመለከተ ቀደም ሲል የነበረውን አስተሳሰብ የቀየረና ኢትዮጵያ የቅድመ ሰው ዘር መገኛ መሆኗን ያበሰረ አንድ ግኝት በቁፋሮ ተገኘ፡፡

  በሳይንሳዊ ስሟ ‹‹አውስትራሎፒቲከስ አፋራንሲስ›› በመባል የምትታወቀውና 3.2 ሚሊዮን ዓመት ባለዕድሜዋ ሉሲ በአፋር አዋሽ ወንዝ አቅራቢያ ሀዳር በተሰኘ ቦታ የተገኘው ቅሬተ አካሏ አንድ ሜትር 10 ሳንቲ ሜትር ቁመት ነበረው። 40 በመቶውን አካል የሚሸፍኑ ቁርጥራጭ ቅሬተ አካላቷም አብረዋት ነበር የተገኙት።

  44 ዓመት በፊት አሜሪካዊው ዶናልድ ጆንሰንና ፈረንሳዊው ማውረስ ታይብ ቅሬተ አካሏን ካገኙ ከሰዓታት በኋላ ምሽት ላይ አረፍ ብለው ካዳመጡት 1960ዎቹ የቢትልሶች ዘፈን ‹‹Lucy in the Sky with Diamond›› (በግርድፉ ሲመለስ ሉሲ ባለአልማዛዊው ሰማይ) መጠርያውን ሉሲ እንዳገኘች ይነገርላታል፡፡

  ኢትዮጵያ የጥንተ ሰው ዘር መገኛ እንደሆነች ዓለም ያረጋገጠባት ሉሲ 1999 .. ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና የአሜሪካው ሂውስተን የተፈጥሮ ሳይንስ ሙዚየም ባደረጉት ስምምነት መሠረት በአሜሪካ የአምስት ዓመት ቆይታ አድርጋለች፡፡ ሉሲ በሂውስተን፣ ቴክሳስ፣ ሲያትልና ካሊፎርኒያ ተዘዋውራ 350 ሺሕ በላይ በሚቆጠሩ ሰዎች መጐብኘቷና 1.5 ሚሊዮን ዶላር ገቢም ለኢትዮጵያ ማስገኘቷ ታውቋል፡፡

  ማንይንገረው ሸንቁጥ ‹‹ባለ አከርካሪዎች›› በተሰኘው መጽሐፋቸው፣ በአገርኛ አጠራር ድንቅነሽ የተባለችው ሉሲን እንዲህ ገልጸዋታል፡፡ ሉሲ በቀላል አማርኛ በሁለት እግሯ የምትሄድ ኤፕ (ቺምፓንዚ) መሰል አካል ነች፡፡ የጭንቅላቷ መጠን ከኤፕ ያልተሻለ ሆኖ ሲገኝ በሁለት እግሯ መንቀሳቀሷ ደግሞ ለሰው የተሻለ ቅርብ ያደርጋታል፡፡

  የሉሲን ቅሪተ አካል የተለየ ያደረገው በጊዜው ከተገኙትም ሆነ አሁን ከሚገኙት አንፃር ሲታይ 40 በመቶ የሚሆነው የአካል ክፍሏም መገኘት ነው፡፡ ሉሲ ጾታዋ ታውቆ በሴት ስም የምትጠራው የዳሌዋ አጥንት በመገኘቱ ነው፡፡

  በቅርቡ ደግሞ ይፋ የሆነው ራሚደስ ቅሬተ አካል ወደ 4.25 ሚሊዮን ዕድሜ ሲያስመዘግብ ከሉሲና ከሌሎች ቅሬተ አካል ጋር ተዳምሮ በአዝጋሚ ለውጥ ሒደት ውስጥ የመጣውን የሰው ዘር ቤተሰብ (ቅድመ ሰው ዝርያዎችን) ያስተናገደች አገር መሆኗን ያስረግጣል፡፡

  በቅርቡ ሉሲ መሣሪያ ትጠቀም እንደነበረ በጥናት መረጋገጡ ከዚህ በፊት ይታሰብ የነበረውና መሣሪያ መጠቀም የተጀመረው በሆሞ ሀቢለስ (Homo habilus) ዘመን (1.5 ሚሊዮን ዓመት በፊት) የሚለውን መረጃ ወደ ኋላ 3.2 ሚሊዮን ዓመት በፊት ይወስደዋል ማለት ነው፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...