Sunday, August 14, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  - Advertisement -

  ፌርማታ ፅሁፎች

  16ኛው የኢትዮጵያ ባህል ስፖርት ውድድር በአምቦ

  ትኩስ ፅሁፎች

  16ኛው የኢትዮጵያ ባህል ስፖርት ውድድር በምዕራብ ሸዋ ዞን በአምቦ ከተማ አዘጋጅነት  ከየካቲት 16 ቀን 2011 . ጀምሮ ለዘጠኝ ቀናት እየተካሄደ ነው፡፡ ‹‹የባህል ስፖርት ተሳትፏችን ለሰላምና ለአንድነታችን›› በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ውድድር ከአራት ክልሎች አማራ፣ ኦሮሚያ ደቡብና ሐረሪ፣ እንዲሁም ሁለቱ ከተሞች አዲስ አበባና ድሬዳዋ የተወጣጡ 440 ተወዳዳሪዎች በመካፈል ላይ ናቸው፡፡ እንደ የኢትዮጵያ ባህል ስፖርት ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በላይ ኃይሉ መግለጫ፣ እስከመጨረሻው ሰዓት እንደሚወዳደሩ ሲጠበቁ የነበሩት አፋርና ትግራይ ሳይገኙ ቀርተዋል፡፡ በዚህ ውድድር ላይ በብሔራዊው ፌዴሬሽን ሕግና ደንብ አውጥቶላቸው ወደ ውድድር በገቡ 11 የባህል ስፖርት ዓይነቶች ፉክክር ይደረግባቸዋል፡፡ በዘንድሮው የአምቦ የባህል ስፖርት ውድድር በቀስትና በኮረቦ ድብልቅ ጾታ (ወንድና ሴት ተደባልቀው የሚጫወቱበት) ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ፎቶዎቹ የውድድሩን ከፊል ገጽታዎች የሚሳዩ ናቸው፡

  16ኛው የኢትዮጵያ ባህል ስፖርት ውድድር በአምቦ

  16ኛው የኢትዮጵያ ባህል ስፖርት ውድድር በአምቦ

  - Advertisement -
  - Advertisement -

  ተጨማሪ ለማንበብ

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች