‹‹ቀጣዩ ትውልድ የመደመርን ሥርዓት፣ የይቅርታን እና የፍቅርን ባህል ጠንቅቆ እንዲያውቅና በተግባር ላይ እንዲያውለው፣ ኢትዮጵያዊነትን እንዲለማመድ ማድረግ ነው፤›› የሚል ዓላማ መሰነቁን የሚገልጸው መሰንበቻውን የኅትመት ብርሃን ያየው የሣህሉ አድማሱ የጨለማው መጋረጃ ሲቀደድ መጽሐፍ ነው፡፡ ከፊት ሽፋኑ ግርጌ ‹‹በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር›› የሚል ንዑስ ርዕስ ያለው መጽሐፉ ካሉት 16 ክፍሎች አንዱ የመደመርን ጥንተ ታሪክ ተዘግቦበታል፡፡ በ80 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡