Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፓርትእግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዋሊያ ቢራ ጋር አዲስ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራረመ

  እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዋሊያ ቢራ ጋር አዲስ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራረመ

  ቀን:

  በኢትዮጵያ በስፖንሰርሺፕ የገበያ ድርሻ ካላቸው ተቋማት ውስጥ ቢራ በመጥመቅና በመሸጥ ላይ የሚገኙ ተቋሞች የጎላ ሚና ሲጫወቱ ቆይተዋል፡፡ ተቋማቱ ‹‹እኔ የተሻልኩ ነኝ›› የሚለውን የፕሮሞሽን ሥራዎቻቸውን ወደ ኅብረተሰቡ የሚያወርዱበት አግባብ ትውልዱን እያበላሸ መሆኑን ከግምት በማስገባት የቢራ ማስታወቂያዎች በተለይም በኤሌክትሮኒክስ መገኛኛ ብዙኃንና ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው አደባባዮች ማስታወቂያዎች እንዳይሰቀሉ በአዋጅ መከልከሉ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ይሁንና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዋሊያ ቢራ ጋር አዲስ የስፖንሰርሺፕ ውል ስምምነት አድርጓል፡፡

  ረቡዕ መጋቢት 11 ቀን 2011 .. በካፒታል ሆቴል የተከናወነውን የስፖንሰርሺፕ ስምምነት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንቱ አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ በዋሊያ ቢራ በኩል ደግሞ የሄንከን ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ዩጂን ፈርመዋል፡፡ ከሁለቱ ኃላፊዎች በተጨማሪ በሄንከን ኢትዮጵያ የማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ኃላፊዎችና በተመሳሳይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአቶ አበበ ገላጋይ የሚመራው የማርኬቲንግ ክፍል ባለሙያዎችም በስምምነቱ ተገኝተዋል፡፡

  ስምምነቱን አስመልክቶ አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ ‹‹ዋሊያ ቢራ የኢትዮጵያን እግር ኳስ ለመደገፍ የቆረጠ ብቸኛው አጋር ነው፤›› ብለው ምክንያቱን ሲያብራሩ ደግሞ፣ ‹‹ስምምነቱ ዋሊያ ቢራ ከዚህ ቀደም የሚያገኘውን ጥቅም የሚያሳጣው ቢሆንም፣ ካምፓኒው እግር ኳሳችንን ለመደገፍ ካለው ፅኑ እምነት በመነሳት የወሰነው ነው፤›› ብለዋል፡፡ 

  በኢትዮጵያ እግር ኳስና የዋሊያ ቢራ አክሲዮን ማኅበር መካከል የተደረገው የብቸኛ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት፣ በዋናነት የቢራ ምርትን አስመልክቶ የወጣውን አዋጅ መሠረት አድርጎ ለመሥራት ሲሆን፣ በዚህ አጋጣሚም ኩባንያው ማግኘት የሚገባውን ጥቅም እንዲያስጠብቅ ተደርጎ መዘጋጀቱንም ጭምር አቶ ኢሳያስ ተናግረዋል፡፡

  ለሦስት ዓመታት የሚቆየው የውል ስምምነት ከዚህ በፊት ከነበረው የወንዶቹ ዋናውን ቡድን አጋርነት በተጨማሪ በአዲሱ ስምምነት የሴቶቹን ብሔራዊ ቡድን የሚያካትት ሆኗል፡፡ ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የዋሊያን ምርት የሚያስተዋውቁት በልምምድ ቦታና ሥፍራ በሚለብሱት ማሊያና ቱታ፣ ቦርሳና ተያያዥ መገልገያዎች እንደሚሆንም ተብራርቷል፡፡ ዋሊያ ቢራ ስለሚያገኛቸው ተጨማሪ ጥቅማ ጥቅሞችን አስመልክቶ አቶ ኢሳያስ፣ በቀጣይ የአዋጁ ዝርዝር አፈጻጸም በሚወጣበት ጊዜ እንደሚብራራ ነው ያስረዱት፡፡ 

  የገንዘቡ መጠን ከአራት ዓመት በፊት የነበረው 56 ሚሊዮን ብር እንደሚሆንና በየሦስት ወሩ ዋሊያ ቢራ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኖች 3.5 ሚሊዮን ብር የሚከፍል ይሆናልም ተብሏል፡፡ የሄንከን ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ዩጂን በበኩላቸው፣ በስምምነቱ ደስተኛ ስለመሆናቸው ነው የተናገሩት፡፡ 

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...