ብርከ ደንዳና ውሔ ወፍ ቀላ ያለ አሸዋማ ቀለም ያላቸው ትላልቅ ውሔ ወፎች፡፡ ከላይ አካላቸው ቀለም አሸዋ መሳይ ሆኖ ረዣዥምና ቀጫጭን ጥቋቁር ምልክቶች ይታዩበታል፡፡ ከታች ግን ፈካ ያለ ሽሮ ቀለም ነው፡፡ የዓይናቸው አካባቢው በነጭና በጥቁር የተኳለ ይመስላል፡፡ መንቆራቸው አጠር ብሎ ቀጥ ያለና ወፍራም ነው፡፡ እንደዚሁም እግራቸው ረዘም ብሎ ከጉልበት አካባቢ ወፈር ያለ ነው፡፡ በውኃ አካባቢ በሚገኝ ድንጋያማና ዛፍ ያልበዛበት ሥፍራ ይገኛሉ፡፡ በመሠረቱ የማታ ወፎች ስለሆኑ ቀን በግራራማ ቁጥቋጦዎች ውስጥ ይውላሉ፡፡
- ከበደ ታደሰ ‹‹የኢትዮጵያ መካከለኛው ስምጥ ሸለቆ ወፎች የኪስ መጽሐፍ›› (2000)
- ፎቶ ብሬት ሃርት