Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  እኔ የምለዉየሚታየው ሁሉ ሚራዥ የሚሆንባት አገር. . .!

  የሚታየው ሁሉ ሚራዥ የሚሆንባት አገር. . .!

  ቀን:

  በቁምላቸው አበበ ይማም

  በቀትር በአስፋልት፣ በምድረ በዳ በመኪና ወይም በእግር ስንጓዝ ከርቀት ውኃ ይታየንና እየቀረብን፣ እየተጠጋን ስንሄድ ግን ውኃውን አናገኘውም፡፡ እንደገና ራቅ ብሎ ግን ያታየናል፡፡ ስንጠጋው አሁንም ውኃውን አናገኘውም፡፡ ጀንበር ጠልቃ ወይም ጉዞአችንን ጨርሰን እስክናቆም ድረስ አዙሪቱና ዑደቱ በዚህ ሁኔታ ይቀጥላል፡፡ ይህን ክስተት ነጮች ሚራዥ (Mirage) ይሉታል፡፡ ይህ ክስተት ሁለት ዋና ዋና መገለጫ ባህሪያት አሉት፡፡ የመጀመሪያ ባህሪው የሚታይ እንጅ የማይጨበጥሁለተኛው ደግሞ ሲጓዙ ቢውሉ የማይደረስበትበቀረቡትና በተጠጉት ቁጥር የሚርቅ 
  መሆኑ ነው፡፡

  በእያንዳንዳችን ሕይወት ከፍ ሲልም በማኅበረሰብና በአገር ደረጃ ከርቀት ስናያቸው ያሉና የሚጨበጡ የሚመስሉንነገር ግን ቀርበን ስንመለከታቸው የማናገኛቸውና የማንጨብጣቸው በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ እንዲሁም የደረስንበትና የተቃረብነው የሚመስለን ግን በተጠጋነው ቁጥር የሚርቀን የሕይወት ቅንጣት አለ፡፡ በሕይወታችን ስንት ከርቀት የሚታየንስንቀርብ የምናጣውና የማንጨብጠው ነገር አለ፡፡ የአገራችን ልማት፣ ዕድገት፣ አንድነትና ሰላምም ከጥንት ጀምሮ እስካሁን እንዲሁ እንደሆነብን ይሰማኛል፡፡ ከርቀት ያየነው ይመስለንና ስንደርስ አናገኘውም፡፡ ተስፋ ያደረግነውንና ያለምነውን  አንጨብጠውም፡፡ ደረስንበት፣ ጨበጥነው ስንል ይርቀናል፡፡
   

  ችግሩ የት ላይ ነው? ከተስፋችን፣ ከህልማችን . . .? ወይስ ከመንገዳችንና መንገዳችን ከጀመርንበት ሰዓት ትክክለኝነት? በዚህ ማንጠሪያነት የእስከ ዛሬውን መንገዳችንን፣ ተስፋችን እያሰላሰልን፣ እያመዛዘን ወደ ሰሞነኛው፣ ተረኛውወቅታዊው ሚራዥ እናመራለን ባለፉት 27 ዓመታት እንደ ዜጋም፣ እንደ አገርም፣ እንደ አገዛዝም የለመድነው ሚራዥ ገጥሞናል፣ ተፈራርቆብናል፡፡ ወደ ፊትም ይጠብቀናል፡፡ እነዚህን በሙሉ ለመተንተን የጋዜጣው ዓምድም ሆነ የእናንተም ጊዜ አይፈቅድም፡፡ ስለሆነም በጥንታዊ ሚራዥ ማጠንጠኛነት ሰሞነኛውን ሚራዥ እንመለከታለን፡፡ ከዚያ በፊት የቃሉን አመጣጥ (ሥረወ ቃል) ‹‹Etymology›› እንመልከት፡፡ ‹‹Mirage›› የሚለው ቃል ስምሲሆን፣ መጀመሪያ ጥቅም ላይ የዋለው እ.ኤ.አ 1803 ነው፡፡ ከላቲኑ ‹Mirari› ወይም ከፈረንሣይኛው ‹Mirer› የተወሰደ ነው፡፡

   ሦስት ሺሕ ዘመን በላይ የሆነው ጥንታዊ ታሪካችንም ሆነበአገረ መንግሥት ያካበትነው የ1,700 ዓመታት ልምምዳችን ከሞላ ጎደል በሚራዥ የተከበበ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በለፀግን፣ ዘመንን፣ ከፍ ከፍ አልን፣ ተነሳን፣ ተፋቀርን፣ ተከባበርን፣ ተቀባበልን፣ ታረቅን፣ አንድ ሆን ስንል  የምንሸራተት፣ የምንደኸይ፣ ኋላ የምንቀር፣ የምንወርድ፣ የምንወድቅየምንጣላ፣ የምንናናቅ፣ የምንገፋፋ፣ የምንጣላ፣ የምናቄም፣ የምንለያይና የምንከፋፈል ጉዶች ነን ፡፡

  ዛሬም ከዚህ አዙሪትና ቀለበት አልወጣንም፡፡ ነገም በቀላሉ የምንወጣ አይመስልም፡፡ ይህ አባዜ፣ መከራጠባሳና የታሪክ ክስተት ከሌሎች አገሮች ይለየናል፡፡ ለእነዚህ አገሮች በአንድ ወቅት ገጥመዋቸው የተሻገሩት ሲሆን፣ እኛ ግን እዚያው የምንማስንበት መሆናችን ነገሩን ልዩና እንቆቅልሽ ያደርገዋል፡፡
  ሦስተኛው እስከ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን በነበረው የአክሱም ሥልጣኔ ወርቃማ ዘመን ከሮማ ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነት እስከ መመሥረትግዛታችንም ሰፊ እንደነበር የድንጋይ ላይ ጽሑፎችና የተለያዩ ድርሳናት ይጠቁማሉ፡፡ ግዛታችን በደቡብ ዓረቢያ እስከሚገኙት ሂምያር፣ ራይዳን ሳብና ሐለንእንዲሁም ፀያም፣ ቤጋ፣ ባህረ ነጋሽ፣ ምሥራቅ ሱዳን፣ ኑብያንና ፔንትን ያካተተ እንደነበር ይወሳል፡፡ ከባቢሎን፣ ከፋርስ፣ ከቤዛንታይን፣ ከሮም መንግሥታት ጋር የሚገዳደርና የሚፎካከር መንግሥት ነበር፡፡ የአክሱም ዘመነ መንግሥት የራሱ መርከብ፣ መገበያያ ገንዘብና እንደ አዶሊስ ያለ ወደብ የነበረው ታላቅ መንግሥት ነበር፡፡

  ክርስትና ወደ አገራችን የገባው አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በንጉሥ ኢዛና ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ ንጉሡን ያጠመቁት የመጀመሪያው ጳጳስ ከቤዛንታይን የመጡ ነበሩ፡፡ የንጉሥ ኢዛና ክርስትናን መቀበል ከቤዛንታይን ጋር ተፈጥሮ የነበረው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከፍታ ማሳያ ነው፡፡ ይህ ግንኙነት በአገሪቱ ባህል፣ ኪነ ጥበብ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተራክቦ ላይ ጉልህ አሻራውን ትቶም አልፏል፡፡

  ወደ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ስንመጣ የንጉሥ ኢዛና ዘመን እጅግ ገናና ስለነበር፣ ቀይ ባህርን ተሻግሮ የደቡብ ዓረብን ንጉሥ ተቆጣጥሮ ነበር፡፡ በጊዜው አዶሊስ ለአክሱም መንግሥት የወጪና የገቢ ንግድ ማዕከልና የባህር ኃይል መናኸሪያ ነበረች፡፡አክሱም የምዕራባዊና ምሥራቃዊ የቀይ ባህር ዳርቻዎቹን መቆጣጠሩ ለታላቅነቱ ግንባር ቀደም ምክንያት ነበር፡፡ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ በውስጣዊ ሽኩቻና በፋርሳዊ መንግሥት የአክሱም ሥልጣኔ ተንኮታኮተ፡፡ የአክሱም መንግሥት ትውልድም ሆነ ቀጣይ ትውልዶች፣ እንዲሁም አገሪቱ የማይደረስበትንና የማይጨበጠውን የሚራዥ ጉዞ የጀመሩት ከዚያ ሩቅ ዘመን አንስተው ነው፡፡ እንደ ሚራዥ ታላቋና ገናናዋ  ኢትዮጵያ ከሩቅ ትታያቸዋለች ግን አይደርሱባት፣ አይጨብጧትም፡፡

  የነብዩ መሐመድን መወለድ ተከትሎ እስልምና በመስፋፋቱ በፋርስ፣ቤዛንታይንና በአክሱም ቁጥጥር ሥር የነበረው ቀይ ባህር ቀስ በቀስ በእስልምና በሚመራው ኃይል ቁጥጥር ሥር ዋለ፡፡ እስልምና መስፋፋት ሲጀመር የነብዩ መሐመድ ተከታዮች ስሐባዎች ወደ ሐበሻ ምድር ተሰደው ሲመጡ፣ መልካም አቀባበል እንደተደረገላቸው በቅዱስ ቁርዓን ተገልጿል፡፡ ነብዩ መሐመድም ‹‹ሐበሾችን ካልነኳችሁ አትንኳቸውበሐበሻ ላይም ወታደር እንዳይዘመት፤›› ብለው አዝዘዋል ይባላል፡፡ ይህን የታሪክ አንጓ ያነሳሁት በዚያ ዘመን አይደለም ለአገሬውለባዕዳንናእንግዳ ሃይማኖት ተከታዮች መጠጊያ፣ መጠለያ የነበሩ የምንጅላት፣ ምንጅላት፣ ምንጅላት እንዳልነበሩን ዛሬ ይኼ ደግነታችው፣ ሩህሩነታቸው እንደ ሚራዥ ከሩቅ የሚታየን ግን የማንደርስበትና የማንጨብጠው ሆኗል፡፡ ከውጭ የመጣን በፍቅር ልናስጠጋና ልናስጠልል ይቅርና የተዋለድነውን፣ የተጋመድነውን የራሳችንን ክፋይ ትግራዋይ፣ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ሶማሌ፣ ወላይታ፣ ጉራጌ፣ . . . እያልን እየገፋን እንገኛለን ፡፡ ፍቅር፣ ሰላም፣ አንድነት ሚራዥ ሆኖብናል፡፡

  ከሩቅ የምናየው ግን የማንደርስበት፣ ከአክሱም ዘመነ መንግሥት መንኮታኮት በኋላ የተተካው  የዛጉዌ መንግሥት በኪነ ሕንፃ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ በነበረበት ዘመን፣ ዛሬ ድረስ የሰው ልጅ የሚደነቅባቸውን የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያት ትቶልን አልፏል፡፡ እንደ አክሱም ሥልጣኔ ሁሉ የዛጉዌ ረቂቅና ምጡቅ የኪነ ሕንፃ ጥበብ ግን ለዛሬው ትውልድም ሆነ ለቀደመው እንደ ሚራዥ የሚታይ ግን የማይደረስበት ሆኖበታል፡፡ ክቡር ቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ ከፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ጋር ላሊበላን በጎበኙበት ወቅትውቅር አብያተ ክርስቲያናቱ ከተፈለፈሉ 741 ዓመታት በኋላ እንኳን ‹‹ . . . ትውልድ የጀመረውን ማስቀጠል አይደለምጠግኖ ማቆየት እንኳ ተስኖን ለጥገና የሰው እጅ ማየታችን. . .እንዳስቆጫቸው ሲናገሩ በገደምዳሜ የሰማሁ ይመስለኛል፡፡

  በመጨረሻም ቀደም ሲል ያየናቸው የሚራዥ ድምር ውጤቶች ማዕከላዊ መንግሥቱንም ሆነ የግዛት አንድነቱን ክፉኛ ስላዳከሙት ለውጭ ኃያላን ወረራና ለዘመነ መሳፍንት ዳረጉት፡፡ በእነዚያ የታሪክና የሥልጣኔ ገድላት እንዳላለፍን እንደገና ከባዶ ጀማሪ ሆነን አረፍነው፡፡ በእንቅርት ላይ እንዲሉ የግራኝ ወረራ፣ የኦሮሞ መስፋፋት አገሪቱን ይብስ አዳከማት፡፡ ይኼን ተከትሎም ማዕከላዊ መንግሥቱ የተዳከመየየአካባቢው መሳፍንት የገነኑበትዘውድ ተይዞ የሚዞርበት ዘመነ መሳፍንት ተተካ፡፡ ማዕከላዊ መንግሥት ተዳክሞመሳፍንቱና መኳንንቱ በእርስ በርስ ጦርነት ተጠምደው በነበሩበት ወቅትአፄ ቴዎድሮስ ተቀናቃኞቻቸውን ሁሉ ረተው ደርስጌ ላይ ዘውድ ጫኑ፡፡

  ይሁንና አንድ ኢትዮጵያን በመገንባትና ሥልጣኔን በማስፈን ዘመናዊ አስተዳደርና ጦር የመገንባት ህልማቸው እንደ ሚራዥ የሚታይ፣ ግን የማይደረስበትና የማይጨበጥ ሆኖ መቅደላ ላይ በአሳዛኝ ሁኔታ ተቋጨ፡፡

  ከዋግ ሹም ጎበዜ አጭር የንግሥና ዘመን በኋላ በእግራቸው የተተኩት በዝብዝ ካሣ ወይም አፄ ዮሐንስ አራተ የንግሥና ዘመን እንደ አፄ ቴዎድሮስ በውስጥ የሥልጣን ሽኩቻና በጣሊያን፣ በግብፅና በደርቡሾች ጥቃትና ወረራ የተተበተበ ነበር፡፡ የንግሥና ዘመናቸውን በወከባ ያለ ዕረፍት ያሳለፉት አፄ ዮሐንስ የአገረ መንግሥት ግንባታ ጥረታቸው እንደ ሚራዥ የሚታይ እንጅ የማይደረስበት፣ የማይሳካ ሆኖ በአሳዛኝ ሁኔታ መተማ ላይ ከደርቡሾች ጋር ባካሄዱት ጦርነት ሕይወታቸው በማለፉ ተደመደመ፡፡

  አፄ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ለመሆን ከነበራቸው ጉጉት የተነሳየተፈጠረውን የኃይል ክፍተትና የጣሊያንን እገዛ በመጠቀም ነገሡ፡፡ ዙፋናቸውን ለማደላደል ይረዳቸው ዘንድም የውጫሌን ውል ከጣሊያን ጋር ተፈራረሙ፡፡ በዚህ መዘዘኛ ውል ንጉሡ ኤርትራን መስዋዕት ከማድረጋቸው ባሻገር፣ የአገሪቱን አጠቃላይ ሉዓላዊነት አደጋ ላይ በጣለው አንቀፅ 17 መግፍኤነት የዓድዋ ጦርነት ተካሄደ፡፡ ንጉሡ የዓድዋን ጦርነት በድል ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ በአገር ውስጥም በውጭም ተቀባይነታቸው ስለጨመረ በአፄ ቴዎድሮስ ተወጥኖ፣ በአፄ ዮሐንስ ትንሽ ገፍቶ የነበረው የአገረ መንግሥት ግንባታ ከሞላ ጎደል በእሳቸው ዘመነ ህልው ሆነ፡፡ አገሪቱ ከዘመናዊ አስተዳደርና ከቴክኖሎጂ ጋርም መተዋወቅ ጀመረች፡፡ ሆኖም በሚፈልጉት ደረጃ ዳር ሳያደርሱት ሞት ቀደማቸው፡፡

  በመጀመሪያም ልጅ እያሱ፣ በኋላም ንግሥት ዘውዲቱ አንዳንድ ለውጦችን ቢያክሉበትም እንደ አጀማመሩ ውጤታማ አልነበረም፡፡ ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ወደ ዙፋኑ ከመጡ በኋ በአንፃራዊነት ዘመናዊ አስተዳደሩና ትምህርቱ ቢጎላበትምዘመኑንም፣ ዜጋውንም የሚዋጅ ስላልነበር በደርግ ተተክቷል፡፡ ደርግ የአገረ መንግሥት ግንባታውን በተሻለ ደረጃ ደርሶ የተረከበው ቢሆንም፣ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትም ሆነ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ይበልጥ ለማሳደግ የተሻለ አጋጣሚ ቢፈጠርለትም በመረጠው አምባገነናዊ አገዛዝ ከውስጥም፣ ከውጭም ጠላት በማፍራቱና በማራባቱ አገሪቱ ወደሌላ የሚራዥ አዙሪት ተዘፈቀች፡፡ አንድ ትውልድ ተጨፈጨፈባት፣ የተካበው ሁሉ ተናደ፡፡ በመጨረሻም የባህር በር አልባ ሆነች፡፡

  በኃይል ሥልጣን የያዘውሕወሓት/ኢሕአዴግ መንግሥትም የዴሞክራሲያዊ ሥርዓትና የአገረ መንግሥት ግንባታውን በአፈናና በማንነት ላይ በተመሠረተ አገዛዙ ለማቃናትና ለማረም እንዳይመች አወሳስቦ ተስፋችንን፣ ህልማችን የልምዣት አደረገው፡፡ ከአክሱም ዘመነ መንግሥት እስከ ዛሬ የአገረ መንግሥት ግንባታችን አልተጠናቀቀም፡፡ እነ አሜሪካ 250 ዓመታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለዓለም መመኪያ የሚሆን አገር መንግሥት አቁመው እኛ ግን ገና ጥደን እያለቀስን ነው፡፡

  ማጠቃለያ
  የዕድገታችን፣ የሰላማችን፣ የፍቅራችን ነገርም ከላይ በሁሉም አገዛዞች እንደተመለከትነው ሚራዥ ሆኖ ቀርቷል፡፡ አዙሪቱን ሰብሮ መውጣት ዛሬም ተስኖናል፡፡ የሚያሳዝነው ካለፉት 12 ወራት ወዲህ ከዚህ አዙሪት ለመውጣት የፈነጠቀው ተስፋ እዚህም እዚያም ፈተናዎች እየገጠሙት ነው፡፡አገረ መንግሥት ህዳሴው፣ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታው፣ ከድህነትና ከኋላ ቀርነት አዙሪት የመውጣት ጥረቱ፣ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ውጥኑ፣ የዴሞክራሲ ተቋማት ጅማሮ፣ የዕርቅና የሰላም ተስፋው፣ ወዘተ . . . ማንነትና ዘውግ ላይ የተመሠረተውለቲካችን እያደነቃቀፈው ነው፡፡

  በሶማሌና በኦሮሚያ፣ በኦሮሚያና በደቡብ፣ በኦሮሚያ፣ቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በአማራና በትግራይበአማራና በአፋርበአፋርና በሶማሌ፣ እንዲሁም በአዲስ አበባና በኦሮሚያ የተቀሰቀሱ የአስተዳደር ወሰን ጥያቄዎችበጎሳዎች መካከል የተፈጠረ አለመተማመንና መጠራጠርየሥራ አጥነቱ፣ የዋጋ ግሽበቱና የኑሮ ውድነቱየታሪክ እስረኝነቱ መፅናቱአገራችንና ሕዝባችን አሻግረው የሚያዩትን ነገር ሁሉ ሚራዥ አድርጎባቸዋል፡፡

  በተለይ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑና ለፌዴራል መንግሥት ለመታዘዝ ሲያመነታሸኔ ኦነግ ትጥቅ አልፈታም ከማለት አልፎ በምዕራብ ወለጋ የቀሰቀሰው ግጭትበአማራና በትግራይ የአስተዳደር ወሰኖች የተፈጠረ ውጥረትኦዴፓ በቅርቡ በአናቱ  በአዲስ አበባ ከተማ ላይ የባለቤትነት ጥያቄ ማንሳቱወዘተ . . . እንደ አገር የተሰነቀውን ተስፋ ወደ ሚራዥነት አውርዶታል፡፡ የመጠራጠር፣ የመጠላለፍ፣ የመበሻሸቅ ፖለቲካው እንደገና ማንሰራራትና ቀና ቀና ማለት ጀምሯል፡፡

  ከዚህ አልፎ በአገሪቱ ሰማይ ሥር የሥጋት ዳመና ዳምኗል፡፡ ከዚህ የሥጋት ዳመና ፈጥነን መውጣት ካልቻልን አደጋው የከፋ ይሆናል፡፡ ሚራዡን እንኳ ማየት ይናፍቀናል፡፡ ማታ ዓይነት የተስፋ ጭላጭ ከእነ አካቴው ልናጣ እንችላለን፡፡ ይኼ ሟርት አልያም ጨለምተኝነት አይደለም፡፡ በዚያ ሰሞን በአዲስ አበባ ላይ የተነሱ ጉዳዮች ምን ያህል ለውጡን ወደ ኋላ እንደመለሱ ለተመለከቱ ሥጋቱና ፍርኃቱ የሚጨበጥና የሚዳሰስ ነው፡፡ 

  ታዲያ ከዚህ የሚራዥ መርገም እንዴት ነው መውጣት የምንችለው? መፍትሔው ቀላል ባይሆንምማንነታችንን፣ ሃይማኖታችንን፣ መደባችንን ወደ ጎን ትተንአጥራችንን አፍርሰን፣ ድልድይ ሠርተን፣ የግል ፍላጎታችንን አቆይተን፣ ከስሜታዊነትና ከግብታዊነት ወጥተን፣ ትልቁንና አገራዊ ከፍታን አልመንነገ ዛሬ ሳንል እንወያይበት፣ እንነጋገርበት፣ እንመካከርበት፡፡

  ከአዘጋጁጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው fenote1971@gmail.com ማግኘት ይቻላል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...