Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ባልትናዶሮ ዳቦ

  ዶሮ ዳቦ

  ቀን:

  አስፈላጊ ግብዓቶች

  • ዶሮ 
  • ሽንኩርት 
  • አዋዜ (በርበሬ)
  • ቅቤ
  • ሎሚ ( ለማጠቢያ )
  • ኮረሪማ 
  • ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል 
  • ጨው

  ለዳቦው

  • የስንዴ ወይም የፉርኖ ዱቄት 
  • እርሾ  
  • ስኳር (ካስፈለገ) 
  • ጨው
  • ዘይት 
  • ነጭ አዝሙድ   
  • ጥቁር አዝሙድ 

  አዘገጃጀት

  1. ዶሮው  ፀጉሩ  እንዲለቅ  በፈላ ውኃ እየነከሩ  መግፈፍና  ብልቶቹን  አውጥቶ  በሎሚ  መዘፍዘፍ፡፡ 
  2. ሽንኩርት  በደቃቁ  መክተፍና  መጣድ  ውኃውን  ጨርሶ  ጠቆር  ሲል  አዋዜና  ቅቤ  ጨምሮ  ማቁላላት፡፡ 
  3. የተፈጨ  ነጭ  ሽንኩርት ዝንጅብልና ኮረሪማ  ጨምሮ  ሞቅ  ያለ  ውኃ  ጠብ  እያደረጉ  ማቁላላት፡፡  
  4. የተዘፈዘፈውን  ዶሮ  አጥቦ፣ አለቅለቆና  አድርቆ ቁሌቱ ውስጥ መጨመር፡፡
  5. ዶሮው ውኃ  እንዳይኖረው   ከቁሌቱ  ጋር  ካበሰልነው  በኋላ  ጨውን  አስተካክሎ  ማውጣት፡፡

  ለዳቦው 

  1. እርሾውን ለብ ባለ ውኃ ብርጭቆ ውስጥ መበጥበጥ፡፡
  2. ኩፍ ሲልልን ዱቄት፣ ስኳር፣ ጨው፣ ዘይት፣ ነጭ አዝሙድና ጥቁር አዝሙድ በደንብ  አዋህዶ ማቡካት እናም ኩፍ እስኪል መጠበቅ፡፡
  3. ኩፍ ሲል መጋገርያው ላይ ግማሹን ሊጥ መዘርጋትና በስሎ የተዘጋጅውን ዶሮ መገልበጥ፡፡  
  4. ከዚያም ቀሪውን ሊጥ እላዩ ላይ ገልብጦ በጥንቃቄ መሸፈንና ማብሰል
    • ሰዋስው
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...