Thursday, August 11, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -

  ድኩላ

  ቀን:

  ድኩላ  መካከለኛ መጠን ያለው፣ ከሰሐራ በስተደቡብ በአብዛኛዎቹ ሥፍራዎች የሚገኝ እንስሳ ነው፡፡ የወንዶቹ ክብደት ከ40 እስከ 80 ኪሎ ግራም ሲሆን፣ ሴቶቹ ደግሞ ከ25 እስከ 60 ኪሎ ግራም ይመዝናሉ፡፡ ቀንድ ያላቸው ወንዶቹ ብቻ ናቸው፡፡ ቀንዳቸው አንድ ጥምዝ ብቻ ነው ያለው፡፡ ቀጥ ያለ ይመስላል፡፡

  የድኩላ ዓይነቴዎች ብዛት እስከ ዘጠኝ ይደርሳል፡፡ በኢትዮጵያ ቢያንስ ሁለት ዓይነት ድኩላዎች ይገኛሉ፡፡ አንዱ የምኒልክ ድኩላ የሚባለው ሲሆን፣ በባሌ ተራራዎችና በሌሎች ከፍተኛ ሥፍራዎች ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ የዚያ ብቻ ንዑስ ብቸኛ ዝርያ ነው፡፡ ሌላኛው ግን፣ በሌሎች አገሮችም የሚገኝ ዓይነት ነው፡፡

  ድኩላ በደኖች ጥግ የሚኖር እንስሳ ነው፡፡ የፀጉሩ ቀለም ከዕይታ ለመከለል የሚያመች ነው፡፡ ከተሸሸገበት የሚወጣው፣ የተሻለ ምግብ ሲያገኝ ወይም ሌሎች ድኩላዎችን ሲያይ ነው፡፡ ጨሌ ሣር የሚበላ ቢሆንም በአብዛኛው ቅጠል በል ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ውኃ አጠገብ ነው የሚገኘው፡፡

  • ሰሎሞን ይርጋ (ዶ/ር) ‹‹አጥቢዎች›› (2000)
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት ጀመረ

  ሦስተኛ ዙር ሙሌት በዛሬው ዕለት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ...

  የክላስተር አደረጃጀት ፖለቲካዊ ውዝግብ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይባል የነበረውን አደረጃጀት...

  በወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው ከፍተኛ ሀብት ጥቅም ላይ እየዋለ አይደለም ተባለ

  በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው የተቀማጭ ገንዘብ መጠን...